TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳዳር አቶ #ሚሊዮን_ማቲዮስ ለክልሉ #ሰላምና #ፀጥታ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
ሃላሌ!! #ይርጋለም!!

የአገር ሸማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና ወጣቶች የተገኙበት የሰላም ኮንፈረንስ #በይርጋለም ከተማ ተካሂዷል፡፡

ወጣቶች ጥያቄያቸው ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ የሲዳማ "ሃላሌ" ባህላዊ ስርዓት ተከትለው በሰላማዊ መንገድ እንዲጠይቁ የሲዳማ አገር ሸማግሌዎች አሳስበዋል፡፡

"ኤጄቶዎች" ወይም የሲዳማ ወጣቶችና አገር ሸማግሌዎች የጋራ የሰላም ኮንፈረንስ ማካሄድ ከጀመሩ በኋላ ለውጥ መታየቱን የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ #ሚሊዮን_ማቲዮስ አስታውቋል፡፡

"ኤጄቶዎች" የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ የሚረጋገጥበትን ህዝበ ውሣኔ እንዲያስፈፅም የክልሉ ምክር ቤት ለምርጫ ኮሚሽን ቢስታውቅም ዘግይቷል ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀዋሳ

"ከሀምሌ 11 ጋር ተያይዞ ስጋት ውስጥ የሚጥሉ ነገሮች የሉም" አቶ #ሚሊዮን_ማቲዮስ/የደቡብ ክልል ፕሬዘዳንት/
.
.
የሲዳማ የክልልነት ጥያቄን አስመልክቶ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎችን ስጋት ላይ የሚጥሉ ጉዳዮች እንደሌሉ፤ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን በቅርበት እየተከታተሉ እንደሆነ የደቡብ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ ተናገሩ። ከሀምሌ 11 ጋር በተያያዘም ዜጎችን ስጋት ላይ የሚጥል ምንም ነገር የለም ብለዋል።

ክቡር ፕሬዘዳንቱ የተናገሩትን ቃል በቃል ከዚህ በታች እንድታነቡት ፅፌላችኃለሁ፦

"የሀዋሳ ከተማን ነዋሪ ወደስጋት ሊጥሉ የሚችሉ ጉዳዮችን በቅርበት እየተከታተልን ከህዝቡ ጋር በመሆን ምላሽ ለመስጠት ሰፊ ስራዎችን ስንሰራ ነው የቆየነው። አሁንም ቢሆን በዚህ ጉዳይ ላይ በተለይም ከሲዳማ አንፃር የተነሳውን ጥያቄ ተንተርሶ ስጋት ውስጥ የሚያስገቡት ነገሮች እንዳሉ ሚደመጡ ነገሮች አሉ ግን ደግሞ የሲዳማ ህዝብ ጥያቄውን ሰላማዊ በሆነ መልኩ ሲያቀርብ ነው የቆየው ይሄ በተለያየ ሂደት አልፎ አሁን የደረሰበት ደረጃ የደረሰ በመሆኑ አሁን ባለንበት ሁኔታ የከተማችንን ፀጥታ የሚያውክ ነገር ይፈጠራል ብለን የምንጠብቀው ነገር የለም። ከሀምሌ 11 ጋር ተያይዞ ስጋት ውስጥ የሚጥሉ ነገሮች የሉም የሚል ነገር ነው እየገለፅኩ ያለሁት።"

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia