TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrEbbaAbate

የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ጣቢያዎች የማደራጀቱ ሥራ መጠናከሩ ለኢዜአ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት የጣቢያዎቹ ቁጥር 20 መድረሳቸውን እና የመመርመር አቅማቸው እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል። ይህም በአገር አቀፍ የምርመራ አቅምን ያሳድገዋል ብለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrEbbaAbate

ከሰሞኑን 'የጊኒ ዎርም በሽታ' በተከሰተባቸው የጋምቤላ ክልል ቀበሌዎች ከ1 ሺህ 400 በላይ አባዎራዎችን ተደራሽ ያደረገ የቤት ለቤት ቅኝት መካሄዱን የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ ተናግረዋል ፤ የበሽታውን ምልክት በማሳየት የተጠረጠሩ 91 ሰዎች ደግሞ ለይቶ ማቆያ ማዕከል መግባታቸውን ጨምረው ገልፀዋል - #ENA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrEbbaAbate

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ከቫይረሱ ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ቅኝት የማድረግ ስራ ዋነኛ ተግባር መሆኑን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ ገልፀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተደረገ ቅኝት ከቫይረሱ ጋር ንክኪ ከነበረው አንድ ሰው ጋር ንክኪ የነበራቸው 32 ግለሰቦች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ በወረዳው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በተደረገ ድንገተኛ ምርመራ አርባ (40) 'የህግ ታራሚዎች' ይገኙበታል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DrEbbaAbate

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል። ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶች ቢቀመጡም ወረርሽኙ 'ወደ ህብረተሰቡ' ውስጥ መግባቱ በቀዳሚነት እንደሚጠቀስ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia