TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AMHARA

ዛሬ በአማራ ክልል በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ 22 ሰዎች ሲሆኑ ሃያ (20) ሰዎች ከመተማ፣ አንድ (1) ሰው ከወልዲያ እንዲሁን 1 ሰው ከአብርሃጅራ ለይቶ ማቆያ ማዕከላት ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ ናቸው።

ከፆታ አኳያ ሲታዩ ሃያ (20) ወንድ እና ሁለት (2) ሴት ሲሆኑ ከ18 እስከ 35 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

የተገላጭነት ሁኔታ ፦

• የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው - 21
• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው - 1

አጠቃላይ በአማራ ክልል ያለው የቫይረሱ ስርጭት ፦

• ምዕ/ጎንደር - 139 ሰዎች
• ማ/ጎንደር - 1 ሰው
• ጎንደር ከተማ - 4 ሰዎች
• ደሴ ከተማ - 2 ሰዎች
• ባህር ዳር ከተማ - 4 ሰዎች
• አዊ ብሄረሰብ- 3 ሰዎች
• ሰ/ሸዋ - 2 ሰዎች
• ሰ/ወሎ - 6 ሰዎች
• ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን - 1 ሰው
• ደ/ጎንደር - 1 ሰው
• ምስ/ጎጃም (ድንበር ተሻጋሪ) - 1 ሰው

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደቡብ ክልል ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች፦

ታማሚ 1 - የ18 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሲዳማ ዞን ቦና ወረዳ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ የሌለው ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያለው።

ታማሚ 2 - የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሲዳማ ዞን ቦና ወረዳ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ የሌለው ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያለው።

ታማሚ 3 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሲዳማ ዞን ቦና ወረዳ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ የሌለው ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያለው።

ታማሚ 4 - የ50 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሲዳማ ዞን ቦና ወረዳ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ የሌላቸው ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው።

ዛሬ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ከተረጋገጠው አራቱ (4) ሰዎች መካከል ሶስቱ (3) ይርጋለም ህክምና ማዕከልና አንድ ሰው ሀዋሳ ህክምና ማዕከል እንዲቆዩ ተደርገዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SRHB

በሱማሌ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው ሃያ ስድስት (26) ሰዎች ሲሆኑ ሁሉም የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ (ጅቡቲ) ያላቸውና ከደዋሌ ለይቶ ማቆያ ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#THRI

ዛሬ በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ አራቱ (4) ሰዎች መካከል ሁለቱ (2) የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው የተቀሩት ሁለቱ (2) ደግሞ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኑነት ያላቸው እንደሆኑ ከትግራይ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ሰምተናል።

በትግራይ ክልል ደረጃ በአጠቃላይ በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 92 የደረሱ ሲሆን ከነዚህ መካከል 8 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና አግግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሐረሪ ክልልና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ፦

- በሐረሪ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዟ የተረጋገጠው የሀኪም ወረዳ ነዋሪ የሆነች የ37 ዓመት ሴት ስትሆን በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረች ናት።

- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኮቪድ-19 የተያዘው ግለሰብ ከአዲስ አበባ ወደ አሶሳ በተደረገው በረራ በአሶሳ ህዳሴ ኤርፖርት በተወሰደው የናሙና ምርመራ የተገኘ ሲሆን ግለሰቡ የጉዞ ታሪክም ሆነ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለሌው ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከትምህርት ሚኒስቴር ለሀገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎች የተሰጠ ማሳሰቢያ!

(የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር)

የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በመቋረጡ ሀገር አቀፍ የብሔራዊ ፈተና /ምዘና/ የሚሰጥበት ጊዜ በትምህርት ሚኒስቴር እንዲሁም በኤጀንሲው አለመገለፁ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ የተለያዩ አካላት ሀሰተኛ ማህበራዊ ድረገፆች የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ስምና ሎጎ ተጠቅመው ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን እያሰራጩ እንደሚገኙ ተደርሶበታል።

ስለዚህ ውድ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትምህርት የሚጀመርበትን እና ሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና /ምዘና/ የሚሰጥበትን ጊዜ ወደፊት የሚገልፅ መሆኑን እያሳወቀ ተማሪዎች ከወቅታዊው በሽታ ለራሳችሁ እና ለቤተሰባችሁ ጥንቃቄ በማድረግ የመማሪያ መፅሀፍትንና ደብተሮቻችሁን እያነበባችሁ እንድትቆዩ እናሳስባለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DrEbbaAbate

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል። ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶች ቢቀመጡም ወረርሽኙ 'ወደ ህብረተሰቡ' ውስጥ መግባቱ በቀዳሚነት እንደሚጠቀስ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrMatshidisoMoeti 

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ '#አፍሪካ' ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶክተር ማሺዲሶ ሞዌቲ እንዳሉት በቂ ምርመራ እየተደረገ ባለመሆኑና የመከላከያ አቅርቦቶችም በቂ ባለመሆናቸው ቫይረሱ ከዋና ዋና ከተማዎች አልፎ በገጠር አካባቢዎችም ስሩን እየሰደደ ነው።

ነገር ግን የቫይረሱ ስርጭት አሁንም ቢሆን ከቁጥጥር ውጭ እንዳልሆ እና የሚመዘገቡ ሞቶች በመንግሥታት ቁጥጥር እየተደረገባቸው መሆኑን ዋና ዳይሬክተሯ ዶክተር ማሺዲሶ ሞዌቲ መናገራቸውን #BBC ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MekelleUniversity

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዓይደር ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኮቪድ-19 ምርመራ ትላንት በይፋ ጀምሯል።

ምርመራው የትግራይ ክልል የጤና ምርምር ኢንስቲትዩት የሚላክን ሳምፕል ብቻ ስለሚሰራ የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪ በአካል ወደ ዓይደር መምጣት እንደማይችል ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 1,946 ደርሰዋል! 

በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ሰኔ 4/2012 ዓ/ም ድረስ በተደረጉ የላብራቶሪ ምርመራዎች 1,946 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ባለፉት 24 ሰዓት ቫይረሱ የተገኘባቸው 87 ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከል የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው 2 ሰዎች፣ 4 ሰዎች በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው የተቀሩት 81 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው ናቸው።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በአዲስ አበባ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰማንያ ሰባት (87) ሰዎች ክፍለ ከተማ ፦

• አዲስ ከተማ - 23 ሰዎች
• ቦሌ - 3 ሰዎች
• ጉለሌ - 14 ሰዎች
• ልደታ - 5 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 10 ሰዎች
• የካ - 8 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 6 ሰዎች
• አራዳ - 8 ሰዎች
• ቂርቆስ - 7 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 2
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 1

አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ 1,946 ሰዎች ክፍለ ከተማ እንደሚከተለው ቀርቧል ፦

• አዲስ ከተማ - 490 ሰዎች
• ቦሌ - 290 ሰዎች
• ጉለሌ - 251 ሰዎች
• ልደታ - 208 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 177 ሰዎች
• የካ - 114 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 95 ሰዎች
• አራዳ - 94 ሰዎች
• ቂርቆስ - 88 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 66 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 73 ሰዎች

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የታማሚዎች ቁጥር ጉዳይ ?

ዛሬ በፌደራል ደረጃ በወጣው ሪፖርት በአዲስ አበባ ከተማ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 104 ተብሎ የተገለፀ ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ የወጣው ሪፖርት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 87 እንደሆነ ይገልፃል። በሪፖርቱ ላይ ምንም የተሰጠ ማብራሪያ የለም፤ በጤና ሚኒስቴር በኩልም የተገለፀ ነገር የለም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኬንያ 72 የጤና ባለሙያዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል!

በኬንያ እስካሁን በትንሹ 72 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የሀገሪቱን የጤና ሚኒስቴር ጠቅሶ ሲጂቲኤን /CGTN/ ዘግቧል፡፡

የጤና ዋና አስተዳዳሪ ጸኃፊ ዶክተር ረሺድ አማን በግንባር ቀደምነት ሲሳተፉ የነበሩ 72 የጤና ባለሙያዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን አስታውቀዋል፡፡

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል አስራ ዘጠኙ በተለያዩ የህክምና መስጫ ተቋማት ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ዶክተር ረሺድ አማን ተናግረዋል።

(AlAin/CGTN)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በሀገራችን የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ታማሚ ከተገኘ ዛሬ ሶስተኛ (3) ወሩን አስቆጥሯል።

በመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ብዛት 250 የነበረ ሲሆን ባለፈው አንድ ወር ብቻ 2,420 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

ይህም ማለት ባለፈው 1 ወር ውስጥ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ከመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት ጋር ሲነፃፀር በ10 እጥፍ ጨምሯል።

በመሆኑም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ ያለውን ከፍተኛ የሆነ የወረርሽኙ መስፋፋት ግምት ወስጥ በማስገባት ከመቼውም ጊዜ በላይ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባናል።

መከላከል ከመታከም ይቀላል ፣ ቤት መቆየትም ሆስፒታል ከመተኛት ይሻላል ፣ የአፍና የአፍንጫን መሸፈኛ አድርጎ መተንፈስ በማሽን ከመተንፈስ ይልቃል።

ስለሆነም እነዚህን አንዲሁም ሌሎችን የቫይረሱን መከላከያ መንገዶች ሳንዘናጋ በመተግበር እራሳችንንና የምንወዳቸውን ከኮሮና ቫይረስ በሽታ እንጠብቅ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AFRICA

በመላው አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 216,479 ደርሷል፤ ከነዚህ መካከል 5,744 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 99,828 ሰዎች አገግመዋል።

ከፍተኛ የሰው ቁጥር በቫይረሱ የተያዘባቸው 5 ሀገራት ደቡብ አፍሪካ 58,568 ሰዎች ፣ ግብፅ 38,284 ሰዎች፣ ናይጄሪያ 13,873 ሰዎች ፣ አልጄሪያ 10,589 ሰዎች እና ጋና 10,358 ሰዎች ናቸው።

ኢትዮጵያና ጎረቤት ሀገራት ...

በኢትዮጵያ ፣ ኬንያ ፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ በአጠቃላይ 21,023 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።

ከኤርትራ ውጭ በ6ቱ ሀገራት የ674 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ በአጠቃላይ 6,651 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጤና ባለሞያዎች ለኮቪድ-19 እንዳይጋለጡ አስተዋፅኦ እናድርግ!

የሀገራችን የጤና ባለሞያዎች ለኮቪድ-19 እንዳይጋለጡ የማህበረሰቡ አስተዋጽኦ ከፍተኛውን ድርሻን ይይዛል።

እንደኛ ባለሀገር ውስጥ አንድ የጤና ባለሞያ በኮሮና ቫይረስ ቢያዝ የጤና ስርዓቱ ላይ የሚፈጠረው ጫና እጅግ ከፍተኛ ነው።

እስካሁንም በርካታ የሀገራችን ጤና ባለሞያዎች በቫይረሱ በመያዛቸው የህክምና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሆነዋል።

በርካቶቹ ደግሞ በቀጥታ ለቫይረሱ ተጋላጭ በመሆናቸው ሳቢያ ወደ ለይቶ ማቆያ በመግባታቸው ከስራ ገበታቸው ርቀዋል።

ማህበረሰቡ እንዴት የጤና ባለሞያዎችን ከኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነት ሊጠብቃቸው ይችላል? ዶክተር ፍቃደስላሴ ሄኖክ ተከታዩን ምክር አስተላልፈዋል ፦

"ማህበረሰቡ ጤናው ከተጠበቀ ወደ ሆስፒታል አይመጣም ፤ ወደ ሆስፒታል ካልመጣ የጤና ባለሞያው ተጋላጭ አይሆንም።

ስለዚህ ማህበረሰቡ የሚነገረውን፣ የሚሰጠውን የግንዛቤ ማስጨበጫ መስማት ፣ የማህበራዊ ትስስር ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ፣ የህዝብ ትራንስፖርት ላይ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ፣ አስገዳጅ ካልሆነ በቀር ከቤት አለመውጣት ይሄን በማድረግ የግልን ጤና መጠበቅ ያስፈልጋል።

የግል ጤና ሲጠበቅ የቤተሰብ ጤና ፣ የማህበረሰብ ጤና ፣ የሀገር ጤና ይጠበቃል። የራሳችንን ጤና መጠበቅ ከቻልን እንደማህበረሰብ አባል ትልቅ ውለታ ነው።"

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
"በኢትዮጵያ ተጨማሪ 245 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል።" - ዶክተር ሊያ ታደሰ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia