TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 170 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6,187 የላብራቶሪ ምርመራ 170 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2,506 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 93 ወንድ እና 77 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ2 እስከ 115 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 81 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 57 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 13 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 7 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 7 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 3 ሰዎች ከሐረሪ ክልል እንዲሁም 2 ሰዎች ከደቡብ ክልል ናቸው።

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት ሃያ ሁለት (22) ሰዎች ከአዲስ አበባ ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 401 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 35 ደረሰ!

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የሶስት ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል። የመጀመሪያ የ115 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ፣ሁለተኛ የ35 ዓመት ወንድ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪ እና ሶስተኛ የ84 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ናቸው።

ሁሉም ሟቾች ህይወታቸው አልፎ ለአስክሬን ምርመራ በሆስፒታል በተደረገ ምርመራ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ተገኝቶባቸዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸውና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 35 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደቡብ ክልል ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች፦

- ከሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ የሌለው ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያለው (በቅርቡ ከአዲስ አበባ የመጣ)

- ከስልጤ ዞን ዳሎቻ ወረዳ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ የሌለው ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያለው (በቅርቡ ከአዲስ አበባ የመጣ)

ከሲዳማ ዞን በቫይረሱ የተገኘበት ይርጋለም ለይቶ ማቆያ ፤ ከስልጤ ዳሎቻ ወረዳ የተገኘው ዳሎቻ ለይቶ ማቆያ በነበሩበት ወቅት ናሙና እንዲወሰድላቸው የተደረጉ ናቸው። ከእነሱ ጋር ንክኪ የነበራቸውን ሰዎች የመለየቱ ስራ በመሰራት ላይ ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TIGRAY

በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ሰማንያ ስምንት (88) ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተደረገው 297 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው ሰባት (7) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

ከሰባቱ (7) መካከል አንድ (1) የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው ፣ አምስት (5) ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት (ንክኪ) ያላቸው እንዲሁም አንድ (1) የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኦሮሚያ ክልል ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ፦

- ሁለት (2) ሰዎች ከቡራዩ (የ25 ዓመት ሴትና የ28 ዓመት ወንድ)፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌላቸው፤ የ25 ዓመቷ ሴት በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙናት የነበራት እንዲሁም የ28 ዓመት ወንዱ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

- ሱሉልታ 2 ሰዎች (የ27 ዓመት ሴትና የ50 ዓመት ወንድ) ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የላቸው ፤ ሁለቱም ከማህበረሰቡ የተገኙ።

- ሰበታ 2 ሰዎች (የ35 ዓመትና የ36 ዓመት ወንዶች) ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌላቸው። የ36 ዓመቱ ወንድ በከማህበረሰቡ የተገኘ ሲሆን የ35 ዓመቱ ወንድ በአስክሬን ምርመራ ነው ቫይረሱ እንደተገኘበት የተረጋገጠው።

- ዱከም 1 ሰው (የ40 ዓመት ሴት) ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የላትም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘች።

Via @tikvahethAFAANOROMOO

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሐረሪ ክልል ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ፦

ሶስቱም በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ የ14 ዓመት (ሴት) ፣ የ30 እና 52 ዓመት ወንዶች ሲሆኑ ሁሉም መኖሪያቸው 'ሃኪም ወረዳ' መሆኑን ለማውቅ ተችሏል። በሐረሪ ክልል አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሃያ ሶስት (23) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AMHARA

ዛሬ በአማራ ክልል በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ 13 ሰዎች ሲሆኑ አስራ ሁለት (12) ሰዎች ከመተማ እንዲሁም አንድ (1) ሰው በአዘዞ ለይቶ ማቆያ ማዕከላት ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ ናቸው። ከፆታ አኳያ ሲታዩ ሁሉም ወንዶችና ከ17 እስከ 50 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

አጠቃላይ በአማራ ክልል ያለው የቫይረሱ ስርጭት ፦

• ምዕ/ጎንደር - 118 ሰዎች
• ማ/ጎንደር - 1 ሰው
• ጎንደር ከተማ - 4 ሰዎች
• ደሴ ከተማ - 2 ሰዎች
• ባህር ዳር ከተማ - 4 ሰዎች
• አዊ ብሄረሰብ- 3 ሰዎች
• ሰ/ሸዋ - 2 ሰዎች
• ሰ/ወሎ - 5 ሰዎች
• ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን - 1 ሰው
• ደ/ጎንደር - 1 ሰው
• ምስ/ጎጃም (ድንበር ተሻጋሪ) - 1 ሰው

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኦሮሚያ ክልል ?

ዛሬ ከኦሮሚያ ክልል (ሰበታ) በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ እንደተገኘበት የተገለፀውን የ35 ዓመት ወጣትን ጨምሮ አጠቃላይ በክልሉ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አምስት (5) ደርሷል።

ወረርሽኙ አሁን ካለው በላይ ጉዳት እንዳያደርስና የሰዎችን ህይወት እንዳይቀጥፍ ፣ የህክምና ስርዓቱንም በከፋ ደረጃ እንዳያቃውስ የጤና ባለሞያዎችን ምክር ማዳመጥ እንዲሁም መመሪያዎችን ማክበር ያስፈልጋል።

መዘናጋታችንና ቸልተኝነታችን ዋጋ እንዳያስከፍለን!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SRHB

ዛሬ በሱማሌ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ሃምሳ ሰባት (57) ናቸው። ይህ ወረርሽኙ ከገባ ጊዜ አንስቶ ከክልሉ የተመዘገበ ክፍተኛ ቁጥር ነው።

በዛሬው ዕለት በቫይረሱ እንደተያዙ ከተረጋገጠ 57 ሰዎች ሃምሳ አምስቱ (55) የውጭ ጉዞ ታሪክ ያላቸውና በደዋሌ ለይቶ ማቆያ የሚገኙ ናቸው።

አንድ (1) ሰው የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው ከጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ ሲሆን አንድ (1) ሰው ከጅግጅጋ ከተማ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌለውና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያለው ነው።

በአጠቃላይ በሱማሌ ክልል በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሰባ ሶስት (173) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 1,859 ደርሰዋል! 

በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ሰኔ 3/2012 ዓ/ም ድረስ በተደረጉ የላብራቶሪ ምርመራዎች 1,859 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ባለፉት 24 ሰዓት ቫይረሱ የተገኘባቸው 81 ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከል የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው የሉም። 10 ሰዎች በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው የተቀሩት 71 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው ናቸው።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በአዲስ አበባ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰማንያ አንድ (81) ሰዎች ክፍለ ከተማ ፦

• አዲስ ከተማ - 27 ሰዎች
• ቦሌ - 12 ሰዎች
• ጉለሌ - 15 ሰዎች
• ልደታ - 2 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 7 ሰዎች
• የካ - 4 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 8 ሰዎች
• አራዳ - 4 ሰዎች
• ቂርቆስ - 2 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 0
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 0

አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ 1,859 ሰዎች ክፍለ ከተማ እንደሚከተለው ቀርቧል ፦

• አዲስ ከተማ - 467 ሰዎች
• ቦሌ - 287 ሰዎች
• ጉለሌ - 237 ሰዎች
• ልደታ - 203 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 167 ሰዎች
• የካ - 106 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 89 ሰዎች
• አራዳ - 86 ሰዎች
• ቂርቆስ - 81 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 64 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 72 ሰዎች

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮቪድ-19 የተያዙት የUSA የጦር ሰራዊት አባላት...

የጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተክትሎ የጥቁር ሕይወት ዋጋ አለው (ብላክ ላይቭስ ማተር) በሚል ከተካሄደው ተቃውሞ በኋላ በርካታ የጦር ሰራዊት እና የአየር ኃይል አባላት በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸውን ጦሩ አስታወቀ፡፡ ጦሩ ለሥራቸው ደህንነት ሲባል ምን ያህል አባላት በኮቪድ-19 እንደተያዙ እንደማይገልጽ ተናግሯል - #BBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በሳዑዲ አረቢያ...

በሳዑዲ አረቢያ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 112,288 ደርሷል።

ሀገሪቱ ባለፉት 24 ሰዓታት 3,717 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውና የ36 ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቃለች።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrGemechuGudina

በኦሮሚያ ክልል ፣ ምዕራብ ወለጋ ዞን "መንዲ ከተማ" ነዋሪ የሆነ ወጣት በስህተት ቫይረሱ የለብህም ከተባለ ከቀናት በኋላ የተነገረው ውጤት የሌላ ሰው መሆኑ ተገልጾ እሱን ጨምሮ ከእርሱ ጋር ንክኪ አላቸው የተባሉ በርካታ ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ ገብተዋል https://telegra.ph/B-06-11-2

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በእጅጉ እየጨመረ ነው ፤ የሰዎች ህልፈትም እየተመዘገበ ይገኛል። ከምን ጊዜውም በላይ በክልል ከተሞች የሚደረገው ጥንቃቄ ካልተጠናከረ የሚከፈለው ዋጋ ከፍተኛ ነው።

ከፍተኛ ኬዝ የተመዘገበባቸው 3 ክልሎች ፦

- ሱማሌ ክልል በቫይረሱ የተያዙ 173፣ ሞት 0፣ ያገገሙ 36

- ኦሮሚያ ክልል በቫይረሱ የተያዙ 148፣ ሞት 5፣ያገገሙ 23

- አማራ ክልል በቫይረሱ የተያዙ 142፣ ሞት 0 ፣ ያገገሙ 29

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ20 ሺህ በላይ ሆነዋል!

በኢትዮጵያ ፣ ኬንያ ፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ በአጠቃላይ 20,497 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።

ከኤርትራ ውጭ በስድስቱ (6) ሀገራት የ651 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ በአጠቃላይ 6,396 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።

በኢትዮጵያና በጎረቤት ሀገራት ይለውን የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ ከ CARD ጋር በመተባበር ባዘጋጀነው ምስል ከላይ መመልከት ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ምልክቶችን በምናሳይበት ጊዜ በጤና ተቋም ህክምና የማግኘት ጥቅሞች!

(በዶ/ር መክብብ ካሳ COVID-19 RRT)

1.ምርመራ በማድረግ ትክክለኛ ህመማችን ምን እንደሆነ ለማወቅና ተገቢውን ህክምና ለማግኘት።

2. ምናልባት ቫይረሱ ከተገኘብን ተጨማሪ ምርመራዎች በማድረግ ያስከተለብንን ጉዳቶች(Complications)አውቆ ተጨማሪ ህክምና ለማድረግ እና የሰውነት አካላቶቻችን እንዳይጎዱ(organ damage) አንዳያስከትል በአጭሩ ለመግታት።

3. በቫይረሱ ተይዣለሁ በሚል ምክንያት ሊከሰት የሚችል የአእምሮ ጭንቀት በባለሙያዎች እገዛ ለመቀነስ፡፡

4. ቅርብ የሆነ ክትትል ስለሚደረግሎት ቶሎ ከህመምዎ ለማገገም ይረዳዎታል፡፡

5. ከጤና ተቋማትም ሆነ ከአስገዳጅ ለይቶ ማቆያዎች ባለመሸሽዎ ቤተሰብዎን ፣ ማህበረሰቡን እንዲሁም የጤና ስርአቱ ላይ ወደፊት ሊፈጠር የሚችል ጫናን ይቀንሳሉ፡፡

• አጠራጣሪ ምልክቶች ሲያጋጥሞት ካሉበት ሆነው ይደውሉ!

• ኮቪድ-19ን በፍራቻ ሳይሆን በእውቀት አናሸንፈው!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia