TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከአዲስ አበባ ያመለጠው የኮቪድ-19 ታማሚ ተያዘ!

በላይ ጋይንት ወረዳ ከአዲስ አበባ ያመለጠ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መያዙን የወረዳዉ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት አስታውቋል።

የኮሮና ቫይረስ ተጠቂው ከአዲስ አበባ ለይቶ መከታተያ አምልጦ ወደ ወረዳው የሄደ ሲሆን ግለሰቡ ከአዲስ አበባ እስከ ደብረታቦር በትራንስፖርት እንደተጓዘ ተገልጿል።

በኃላም በ28/09/2012 ዓ/ም ደብረታቦር ላይ የየትኛው ወረዳ እንደሆነ ባልታወቀ አምቡላንስ እርዳታ በመጠየቅ ተሳፍሮ ላይጋይንት ወረዳ የደሮ ቀበሌ ድረስ መግባቱነው የተገለፀው።

በእግሩ ወደ ታች ጋይንት ወረዳ ልዩ ስሙ በረንታ ከሚባለዉ አካባቢ በ29/09/2012 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት አካባቢ በነፋስ መዉጫ ከተማ አስተዳደር ፣ በላይ ጋይንት ወረዳና በታች ጋይንት ወረዳ የፀጥታ አካለትና አመራሮች ክትትል ግለሠቡ ሊያዝ ችሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በመላው ዓለም የኮቪድ-19 ሟቾች ከ400 ሺህ አለፈ!

በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው ከተረጋገጠ 6,920,564 ሰዎች መካከል የ400,131 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ከፍተኛ ሞት ቁጥር የተመዘገበባቸው ሶስቱ የዓለም ሀገራት አሜሪካ (111,726 ሰዎች)፣ ዩናይትድ ኪንግደም (40,565 ሰዎች) ፣ ብራዚል (35,211 ሰዎች) ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኢትዮጵያና ጎረቤት ሀገራት...

በኢትዮጵያ ፣ ኬንያ ፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ በአጠቃላይ 18,215 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።

በጠቀስናቸው 7 ሀገራት (ከኤርትራ ውጪ) በኮቪድ-19 ምክንያት የ572 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 5,202 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።

በኢትዮጵያና በጎረቤት ሀገራት ይለውን የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ ከ CARD ጋር በመተባበር ባዘጋጀነው ምስል ከላይ መመልከት ትችላላችሁ።

እናመሰግናለን!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ በኮቪድ-19 የተያዙ የጤና ተቋም ሰራተኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።

ዶክተር ሊያ ባለፉት 2 ሳምንታት 81 የጤና ተቋም ሰራተኞች (የጤና ባለሞያዎችን ጨምሮ) በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸውን አሳውቀዋል።

እስካሁን 97 የጤና ተቋም ሰራተኞች (የጤና ባለሞያዎችን ጨምሮ) በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል። ከነዚህ መካከል 55% የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።

በቫይረሱ ከተያዙት 97 የጤና ተቋም ሰራተኞች መካከል ዘጠና አንዱ (91) ከአዲስ አበባ ከተማ ናቸው።

የምልክት ሁኔታቸው ሲታይ 86% የሚሆኑት ምልክት ያላሳዩ ሲሆኑ 14% የሚሆኑት ምልክት ያሳዩ ናቸው።

በተጨማሪ ባለፈው አንድ ወር ወደጤና ተቋማት ለሌላ ህክምና መጥተው ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ ተጋላጭ የሆኑ የጤና ተቋማት ሰራተኞች 2,340 ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 1,727 በመጋቢት ወር ነው ተጋላጭ መሆናቸው የተገለፀው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrYaredAgidew

ትላንት ምሽት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ አንዲት እናት በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምክንያት ህይወታቸው ማለፉ ከጤና ሚኒስቴር እና ከኤካ ኮተቤ ሆስፒታል እውቅና ውጭ ሲሰራጭ ነበር።

በፌስቡክ እንዲሁም በየተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨውን መረጃ ተከትሎ የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ዶክተር ያሬድ አግደው ተከታዩን መልዕክት አስተላልፈዋል ፦

በትናንትናው ዕለት በሞት የተለየችንን እናት ለማትረፍ ባለሞያዎቻችን የሚቻላቸውን አድርገዋል ፤ ነገር ግን ህይወቷን ማትረፍ አልቻልንም። ሁላችንም ለቤተሰብ መፅናናትን እንመኛለን።
.
የዝችን እናት ሞት ተከትሎ ለሁሉም ቤተሰብ መርዶ #ባልተነገረበት ሁኔታ መረጃውን የማህበራዊ ሚዲያ ላይ የለጠፉ ገፆች መኖራቸው በጣም ያሳዘነን ክስተት ነው።
.
ይህን የታካሚዎቻችንን ሚስጥራው መረጃ ቤተሰብ ላይ የሚያደርሰውን ጫና ባላገናዘበ መልኩ ለጋዜጠኞች የሚያቀብሉ ባለሞያዎች ካሉ ለወደፊቱ እርማት እንደሚወስዱ እንጠብቃለን።
.
ጋዜጠኞች ባህላችንን አገናዝበን የደረሰንን መረጃዎች በጥንቃቄ እና ሀላፊነት በተሞላበት መልኩ እድናስተላልፍ በትህትና እጠይቃለው።

(ዶክተር ያሬድ አግደው - ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በኢትዮጵያ ተጨማሪ 86 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል።" - ዶክተር ሊያ ታደሰ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 86 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6,092 የላብራቶሪ ምርመራ 86 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2,020 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው 51 ወንድ እና 35 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ7 እስከ 82 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 66 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 7 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 7 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከደቡብ ክልል፣ 1 ሰው ከአማራ ክልል እና 1 ሰው ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ናቸው።

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት ስልሳ ሶስት (63) ሰዎች (46 ከአዲስ አበባ፣ 13 ከሱማሌ ክልል፣ 3 ከኦሮሚያ ክልል እና 1 ከአማራ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 344 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 27 ደረሰ!

ከዚህ ቀደም በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና ላይ እያለች በሰላም እምደተገላገለች የተገለፀችውን እናት ጨምሮ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የ7 ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸውና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሃያ ሰባት (27) ደርሷል።

ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

1. የ34 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በህክምና ማዕከል ህክምና ላይ የነበረች።

2. የ56 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤በህክምና ማዕከል ህክምና ላይ የነበረች።

3. የ55 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው።

4. የ36 ዓመት ኢትዮጵያዊ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘበት።

5. የ65 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።

6. የ33 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባት።

7. የ26 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 86 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ! ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6,092 የላብራቶሪ ምርመራ 86 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2,020 ደርሷል፡፡ ቫይረሱ የተገኘባቸው 51 ወንድ እና 35 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ7 እስከ 82 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን…
#Oromiyaa

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተከናወነው የላብራቶሪ ምርመራ 330 ሲሆን ከእነዚህ መካከል ነው ሰባት (7) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ59 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዳማ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የሌላቸው፤ ከማህበረሰቡ የተገኙ።

ታማሚ 2 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊት የቢሾፍቱ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የላትም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘች።

ታማሚ 3 - የ38 ዓመት ኢትዮጵያዊ የቡራዩ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

ታማሚ 4 - የ32 ዓመት ኢትዮጵያዊ የቡራዩ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

ታማሚ 5 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሰሜን ሸዋ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

ታማሚ 6 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊት የጅማ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የላትም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘች።

ታማሚ 5 - የ36 ዓመት ኢትዮጵያዊ የገላን ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

Via @tikvahethAFAANOROMOO (Biiroo Fayyaa Oromiyaa)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SNNPR

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ መንግሥት 217 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከነዚህ መካከል አራት (4) በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በክልሉ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 24 ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ18 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሲዳማ ዞን (በንሳ ወረዳ) ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌለው፣ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው።

ታማሚ 2 - የ20 ዓመት የሲዳማ ዞን (በንሳ ወረዳ) ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌለው፣ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው።

ታማሚ 3 - የ20 ዓመት የሲዳማ ዞን (በንሳ ወረዳ) ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌለው፣ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው።

ታማሚ 4 - የ41 ዓመት የሲዳማ ዞን (በንሳ ወረዳ) ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌለው፣ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AMHARA

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው 239 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው አንድ(1) ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙ የተረጋገጠው።

በዛሬው ዕለት ቫይረሱ የተገኘበት የ28 ዓመት ኢትዮጵያዊ ሲሆን በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ለይቶ ማቆያ ክትትል ሲደረግለት የነበረ ነው።

አጠቃላይ በአማራ ክልል ያለው የቫይረሱ ስርጭት ፦

• ምዕ/ጎንደር - 97 ሰዎች
• ማ/ጎንደር - 1 ሰው
• ጎንደር ከተማ - 3 ሰዎች
• ደሴ ከተማ - 2 ሰዎች
• ባህር ዳር ከተማ - 4 ሰዎች
• አዊ ብሄረሰብ- 3 ሰዎች
• ሰ/ሸዋ - 2 ሰዎች
• ሰ/ወሎ - 4 ሰዎች
• ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን - 1 ሰው
• ደ/ጎንደር - 1 ሰው
• ምስ/ጎጃም (ድንበር ተሻጋሪ) - 1 ሰው

እስካሁን ድረስ በአማራ ክልል 3,031 የላንራቶሪ ምርመራ ተደርጓል ፤ አንድ መቶ አስራ ዘጠኝ (119) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከነዚህ መካከል 23 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TIGRAY

በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ሰባ ሁለት (72) ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተደረገው 352 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው ሰባት (7) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

ከሰባቱ (7) መካከል አምስቱ (5)የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆኑ፤ የተቀሩት 2 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት (ንክኪ) ያላቸው ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DireDawa

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስ በማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን ስርጭት ለመረዳትና በሚገኘው ውጤት መሰረት የመከላከል ስራውን ይበልጥ ለማጠናከር እንዲቻል ከህብረተሰቡ ናሙና በመውሰድ ምርመራ በመካሄድ ላይ የሚገኝ ሲሆን እስካሁን ከህብረተሰቡ ተወስደው ከተላኩት ናሙናዎች መካከል ዛሬ አንድ የ18 ዓመት ወጣት በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት...

ባለፉት 24 ሰዓት በሀገራችን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሟቾች እና ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ተመዝግበዋል።

ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በአንድ ቀን የሰባት (7) ሰዎች ህይወት ማለፉ ሪፖርት አልተደረገም።

እንዲሁም ከዚህ ቀደም በአንድ ቀን ውስጥ ስልሳ ሶስት (63) ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ማገገማቸው ሪፖርት አልተደረገም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 1,510 ደርሰዋል! 

በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ግንቦት 30/2012 ዓ/ም ድረስ በተደረጉ የላብራቶሪ ምርመራዎች 1,510 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ባለፉት 24 ሰዓት ቫይረሱ የተገኘባቸው 66 ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 2 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 4 ሰዎች በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው የተቀሩት 60 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው ናቸው።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በአዲስ አበባ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ስልሳ ስድስት (66) ሰዎች ክፍለ ከተማ ፦

• አዲስ ከተማ - 18 ሰዎች
• ጉለሌ - 6 ሰዎች
• ልደታ - 5 ሰዎች
• ቦሌ - 9 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 5 ሰዎች
• የካ - 1 ሰው
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 3 ሰዎች
• ቂርቆስ - 6 ሰዎች
• አራዳ - 4 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 3 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 6 ሰዎች

አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ 1,510 ሰዎች ክፍለ ከተማ እንደሚከተለው ቀርቧል ፦

• አዲስ ከተማ - 410 ሰዎች
• ጉለሌ - 201 ሰዎች
• ልደታ - 196 ሰዎች
• ቦሌ - 160 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 141 ሰዎች
• የካ - 85 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 68 ሰዎች
• ቂርቆስ - 67 ሰዎች
• አራዳ - 64 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 48 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 70 ሰዎች

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በሀገራችን ባለፉት 7 ቀናት ብቻ 848 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ እንደተያዙ እንዲሁም 16 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው ማለፉን ዶክተር ሊያ ታደሰ አሳውቀዋል።

ነገር ግን በሕብረተሰቡ ዘንድ አሁንም በሽታውን ለመከላከል የሚረዱ የመከላከያ ዘዴዎች ከመተግበር አኳያ እጅግ ብዙ #ክፍተቶች እየተስተዋሉ መሆኑን ገልፀዋል።

ዶክተር ሊያ ሁሉም የሕብረተሰብ አካል፣ ክልሎች ፣ የከተማ አስተደሮችና የሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶችና ሌሎች አካላት የበሽታው ስርጭት ተስፋፋቶ ከአቅም በላይ ከመድረሱ እና ለከፋ ችግር ከመዳረጋችን በፊት የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት ከምንጊዜውም በላይ ሕብረተሰቡን ባማከል እና ባሳተፈ መልኩ አስፈላጊውን የመከላከል ስራ እንዲተገብሩ #በአፅንኦት አሳስበዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia