TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ትኩረት ለምዕራብ ጎንደር ዞን!

በአማራ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ 108 ሰዎች መካከል ሰማንያ ሰባቱ (87) ከምዕራብ ጎንደር ዞን ናቸው።

በሁሉም አካላት ይህ የሀገሪቱ ክፍል 'ልዩ ትኩረት' ተሰጥቶ ካልተሰራበት በሀገር ደረጃ የሚከፈለው ዋጋ እጅግ በጣም ከፍተኛ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአሜሪካ የስራ አጦች ቁጥር ቀነሰ!

በአሜሪካ ቢዝነሶች እንቅስቃሴ እየጀመሩ በመሆናቸው እና የሰራተኛ ቅጥር በመጀመሩ የሥራ አጦች ቁጥር በፈረንጆቹ ሚያዚያ ወር ከነበረው 14.7 በመቶ ወደ 13.3 በመቶ ዝቅ ብሏል - #BBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ሆነው የሚቆዩበትን ጊዜ ለተጨማሪ 30 የስራ ቀናት ማራዘማቸውን EBC ዘግቧል።

ፍርድ ቤቶቹ ከሰኔ 1 ቀን 2012 ጀምሮ እስከ ሀምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ለተጨማሪ 30 የስራ ቀናት በከፊል ዝግ ሆነው አንደሚቆዩ ተወስኗል https://telegra.ph/EBC-06-05

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HalaZeyed

ግብፅ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓት 1,348 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የአርባ (40) ሰዎች ህይወት አልፏል።

በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 31,115 ደርሰዋል። በቫይረሱ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 1,116 ከፍ ብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኢትዮጵያና ጎረቤት ሀገራት...

በኢትዮጵያ ፣ ኬንያ ፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ በአጠቃላይ 17,678 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።

በጠቀስናቸው 7 ሀገራት በቫይረሱ ምክንያት የ550 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 4,900 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።

በኢትዮጵያና በጎረቤት ሀገራት ይለውን የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ ከ CARD ጋር በመተባበር ባዘጋጀነው ምስል ከላይ መመልከት ትችላላችሁ።

እናመሰግናለን!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 169 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል! ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 5,798 የላብራቶሪ ምርመራ 169 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,805 ደርሷል፡፡ ቫይረሱ የተገኘባቸው 111 ወንድ እና 58 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 78 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 168 ኢትዮጵያውያን እና…
ዓዲ ሓሩሽ የስደተኞች ካምፕ!

በትግራይ ክልል በሚገኘው 'የኤርትራ ስደተኞች ካምፕ' አንዲት ስደተኛ በኮሮና ቫይረስ መያዟ መረጋገጡን የክልሉ ጤና ቢሮ አሳውቋል።

ትላንት በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጠ 4 ሰዎች መካከል አንዷ ኤርትራዊት ስደተኛ መሆኗን የክልሉ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች መቆጣጠር አስተባባሪ አቶ ሳሙኤል አረጋይ ለVOA ተናግረዋል።

አቶ ሳሙኤል እንደተናገሩት ቫይረሱ የተገኘባት በዓዲ ሓሩሽ የስደተኞች ካምፕ ነዋሪ የሆነችው የ16 ዓመት ሴት መሆኗን ነው የገለፁት።

ባለፈው ሳምንት ከሌሎች 26 የሚሆኑ ሰዎች ጋር በመሆን ወደ ፀበል ቦታ ተጉዛ እንደነበረም ለሬድዮ ጣቢያው ገልፀዋል።

ቫይረሱ የተገኘባት ወደ አክሱም የኮሮና ማዕከል ለመውሰድ እየተሰራ መሆኑና ከእሷ ጋር ግንኙነት የነበራቸውን ሰዎች በመለየት ወደ ማቆያ ማዕከል እየገቡ እንደሆነ ተናግረዋል።

ስደተኞች ካምፕ ለኮሮና መስፋፋት ተጋላጭ ከሆኑ ቦታዎች አንዱ በመሆኑ ይህንን መሰረት በማድረግ በዓዲ ሓሩሽ የስደተኞች መጠለያ በብዛት ሰዎች የመመርመር ስራ ይከናወናል ብለዋል።

ውጤቱንም በማየት አስፈላጊ ውስኔዎች ከሚመለከታቸው መንግስታዊ ተቋማት ጋር በመሆን ይሰራል ሲሉ #ለVOA ገልፀዋል።

የፌዴራል መንግሥት የስደተኞችና የስደት ተመላሾች ኤጄንሲ በበኩሉ በፌዴራሉ መንግሥት በሚመለከታቸው መሥሪያ ቤት በይፋ በስደተኞች ካምፕ ላይ በኮሮና የተያዘ ሰው እንዳለ የተገለፀ ነገር የለም ሆኖም ግን በስደተኞች መጠለያ ቫይረሱ ለመከላከል ከገባም ለመቆጣጠር እየተሰራ ነው ብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዓለም ጤና ድርጅት!

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ከዚህ በፊት ስለአፍናጫ እና አፍ መሸፈኛ ጭምብል አጠቃቀም አውጥቶት የነበረውን መመሪያ መለወጡን #BBC ዘግቧል።

WHO ቀደም ብሎ የህክምና ጭምብል መጠቀም ያለባቸው የጤና ሠራተኞች፣ የኮሮና ቫይረስ ህሙማንና የህሙማኑ እንክብካቤ የሚያደርጉ ሰዎች ብቻ ሊሆኑ እንደሚገባ መክሮ ነበር።

ድርጅቱ አሁንም የህክምና ጭምብል በስፋት በሁሉም ሰው መጠቀም #የለበትም ብሏል። ነገር ግን ከተለያዩ ጨርቆች የሚዘጋጁ እንዲሁም እጥረት የማይኖርባቸውን አስፈላጊ ከሆነም 'ቤት ውስጥ ማዘጋጀት' የሚቻሉትን ጭንብሎችን መጠቀም ይቻላል ብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮቪድ-19 በሜክሲኮ እና ብራዚል...

በሜክሲኮ እና ብራዚል የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ በከፍተኛ ደረጃ እየተሰራጨ ነው ፤ በየዕለቱ በቫይረሱ ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርም እየጨመረ ነው።

ሃሙስ ዕለት በሁለቱ ሀገራት በድምሩ 1,824 (ሜክሲኮ 816 እና ብራዚል 1,008) ሰዎች ህይወት አልፏል። እንዲሁም 34,578 (ከሜክሲኮ 4,442 እና ብራዚል 30,136) ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#PMOEthiopia

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 84ኛ መደበኛ ስብሰባ የ2013 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት 476,012,952,445 ብር እንዲሆን ውሳኔ አሳልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በኢትዮጵያ ተጨማሪ 129 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።" - ዶክተር ሊያ ታደሰ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 129 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5,500 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሃያ ዘጠኝ (129) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1934 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው 75 ወንድ እና 54 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 90 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 124 ሰዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ የተቀሩት የደቡብ አፍሪካ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ የአሜሪካ፣ የኤርትራ እና ሱዳን ዜጎች ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 101 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 10 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 6 ሰዎች ከሶማሌ ክልል፣ 5 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 5 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 1 ሰው ከሐረሪ ክልል እና 1 ሰው ከጋምቤላ ክልል ናቸው።

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት አስራ ዘጠኝ (19) ሰዎች (2 ከትግራይ ክልል፣ 6 ከአፋር ክልል፣ 1 ከሶማሌ ክልል እና 10 ከአዲስ አበባ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 281 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 20 ደረሰ!

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የ80 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ነዋሪ ህይወት አልፏል። ሟቿ ወደ ሆስፒታል ለሌላ ህክምና በመጡ በአንድ ሰዓት ወስጥ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል። በአስክሬን ምርመራም የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሃያ (20) ደርሷል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

ኢትዮጵያ ውስጥ በኮቪድ-19 መያዛቸው ከተረጋገጠ 1,934 ሰዎች መካከል ሃያ ሰባት (27) ሰዎች 'በፀና መታመማቸውን' የጤና ሚኒስቴር ሪፖርት ያስረዳል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AMHARA

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው 235 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው አስር (10) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።

አስሩም (10) ወንድ ሲሆኑ ከምዕራብ ጎንደር ዞን ናቸው። የእድሜ ክልላቸው ከ24 እስከ 50 ዓመት ውስጥ ይገኛል። ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውና #መተማ ለይቶ ማቆያ ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ ናቸው።

አጠቃላይ በአማራ ክልል ያለው የቫይረሱ ስርጭት ፦

• ምዕ/ጎንደር - 97 ሰዎች
• ማ/ጎንደር - 1 ሰው
• ጎንደር ከተማ - 3 ሰዎች
• ደሴ ከተማ - 2 ሰዎች
• ባህር ዳር ከተማ - 4 ሰዎች
• አዊ ብሄረሰብ- 3 ሰዎች
• ሰ/ሸዋ - 2 ሰዎች
• ሰ/ወሎ - 3 ሰዎች
• ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን - 1 ሰው
• ደ/ጎንደር - 1 ሰው
• ምስ/ጎጃም (ድንበር ተሻጋሪ) - 1 ሰው

እስካሁን ድረስ በአማራ ክልል 2,792 የላንራቶሪ ምርመራ ተደርጓል ፤ አንድ መቶ አስራ ስምንት (118) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከነዚህ መካከል 23 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Oromiyaa

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተከናወነው የላብራቶሪ ምርመራ 350 ሲሆን ከእነዚህ መካከል ነው አምስት (5) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ41 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሱሉልታ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

ታማሚ 2 - የ34 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዳማ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

ታማሚ 3 - የ40 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዳማ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

ታማሚ 4 - የ52 ዓመት ኢትዮጵያዊ የምዕራብ ሸዋ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

ታማሚ 5 - የ40 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሆለታ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HARARI

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው ሃያ አራት (24) የላቦራቶሪ ምርመራ ነው አንድ (1) ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙ የተረጋገጠው፡፡

ዛሬ በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠው የ32 ዓመት ኢትዮጵያዊ ሲሆን፤ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌለውና የሽንኮር ወረዳ ነዋሪ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አሳውቋል።

በአጠቃላይ በሐረሪ ክልል ደረጃ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር አስራ አራት (14) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TIGRAY

በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ስልሳ አምስት (65) ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተደረገው 251 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው አምስት (5) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

አንድ ሰው የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው፤ የተቀሩት 4 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት (ንክኪ) ያላቸው ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia