በብራዚል የሟቾች ቁጥር ከ31,000 በላይ ሆኗል!
በብራዚል በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞቱ ሰዎች 31,309 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ የ1,232 ሰዎች ህይወት አልፏል።
በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 558,237 የደረሰ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 27,263 በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው በትላንትናው ዕለት ነው።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

በኤርትራ 2 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተሰምቷል!
በአስመራ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የመጀመሪያው ዙር የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምርመራ በትላትናው ዕለት ተጠናቋል።
4,659 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን ከነዚህ መካከል 4,658 ሰዎች ከቫይረሱ ነፃ ሲሆኑ አንዲት ሴት በቫይረሱ መያዟ ተረጋግጧል።
ከእሷ ጋር ንክኪ ያላቸው አስራ ሶስት (13) ሰዎች ተለይተው ወደ ለይቶ ማቆያ የገቡ ሲሆን ከነዚህ መካከል #ባለቤቷ በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል።
በቀጣይ ድንበር አካባቢ ባሉ ከተሞች እንዲሁም መንደሮች ሰፋ ያለ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እንደሚደረግ የኮቪድ-19 ለመከላከል የተቋቋመው ግብረ ኃይል አሳውቋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 142 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 4,120 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ አርባ ሁለት (142) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,486 ደርሷል፡፡
ቫይረሱ የተገኘባቸው 84 ወንድ እና 57 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ7 እስከ 78 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 140 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ሁለቱ (2) የፖርቹጋል እና የጅቡቲ ዜጎች ናቸው።
ቫይረሱ የተገኘባቸው 126 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 2 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 7 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 6 ሰዎች ከአማራ ክልል እና 1 ሰው ከሶማሌ ክልል ናቸው።
ተጨማሪ መረጃ ፦
በትላንትናው 15 ሰዎች (9 ከሶማሌ ክልል እና 6 ከአዲስ አበባ) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 246 ደርሰዋል።

በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 17 ደረሰ!
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የሶስት ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል።
የመጀመሪያዋ የ71 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፣ ሁለተኛ የ46 ዓመት ወንድ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪ እና ሶስተኛ የ40 ዓመት ወንድ የደቡብ ክልል ነዋሪ ናቸው።
የመጀመሪያዋ ግለሰብ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆኑ ሁለቱ (2) ህይወታቸው አልፎ ለአስክሬን ምርመራ በሆስፒታል በተደረገ ምርመራ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
በአጠቀላይ በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ ሰባት (17) ደርሷል።

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ዕለታዊ መግለጫ (ግንቦት 26/2012 ዓ/ም በCARD እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተዘጋጀ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse
በሕብረተሰቡ ውስጥ ባለው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ስርጭት ምክንያት ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ነው።
ለዚህም ማሳያ የመጀመሪያው ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙ ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 2 ወራት ውስጥ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ጋር ሲነፃፀር ባለፉት 2 ሳምንታት ውስጥ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር በ300 መቶኛ ጨምሯል።
በዚህ ምክንያት የታካሚዎች ቁጥር በመጨመሩ እንደ 'ሚሊኒየም አዳራሽ' አይነት ለይቶ ማከሚያዎች ታካሚዎችን እንዲቀበሉ ማድረግ ተጀምሯል።
ስለዚህ ህብረተሰቡ የእጅ ንፅህናውን በመጠበቅ ፣ በቤት በመቆየት ካልተቻለ ደግሞ ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ባለመገኘት እንዲሁም ከማንኛውም ሰው በ2 ሜትር አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እራሱን እና የሚወዳቸውን ሁሉ ከቫይረሱ እንዲጠብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

በጤና ተቋማት የሚሰሩ 65 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል!
በኢትዮጵያ እስካሁን ባለው ሂደት 49 የጤና ባለሙያዎችና 16 ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።
ባለሙያዎቹ በአብዛኛው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የጤና ተቋማት እየሰሩ መሆናቸውን በመግለጽ።
የጤና ባለሙያዎችና የጤና ተቋማት ሠራተኞች የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እያደረጉት ላለው ተጋድሎም ምስጋና አቅርበዋል።
መንግሥት የጤና ተቋማት ሠራተኞችን ተጋላጭነት ለመቀነስ ከሚያደርገው ሥራ በተጨማሪ ኅብረተሰቡ ራሱን በመጠበቅ የባለሙያዎቹን ጫና እንዲቀንስም ጠይቀዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

TIKVAH-ETHIOPIA
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 142 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል! ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 4,120 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ አርባ ሁለት (142) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,486 ደርሷል፡፡ ቫይረሱ የተገኘባቸው 84 ወንድ እና 57 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ7 እስከ 78 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት…
ኦሮሚያ ክልል!
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተከናወነው የላብራቶሪ ምርመራ 314 ሲሆን ከእነዚህ መካከል ነው ሰባት (7) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው። አጠቃላይ በክልሉ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 90 ደርሰዋል።
የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦
ታማሚ 1 - የ31 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዳማ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።
ታማሚ 2 - የ48 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዳማ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።
ታማሚ 3 - የ34 ዓመት ኢትዮጵያዊት የጅማ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የላትም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘች።
ታማሚ 4 - የ61 ዓመት ኢትዮጵያዊ የምዕራብ ሸዋ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የላቸውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኙ።
ታማሚ 5 - የ13 ዓመት ኢትዮጵያዊት የቡራዩ ነዋሪ ፤የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የላትም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘች።
ታማሚ 6 - የ45 ዓመት ኢትዮጵያዊ የቡራዩ ነዋሪ ፤የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።
ታማሚ 7 - የ3 ወር ህፃን የቡራዩ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።
Via @tikvahethAFAANOROMOO (Biiroo Fayyaa Oromiyaa)
@tikvhhethiopiaBot @tikvahethiopia

በአዲስ አበባ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 1,082 ደርሰዋል!
በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ግንቦት 26/2012 ዓ/ም ድረስ በተደረጉ የላብራቶሪ ምርመራዎች 1,082 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
ባለፉት 24 ሰዓት ቫይረሱ የተገኘባቸው 126 ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 4 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 14 ሰዎች በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው የተቀሩት 108 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው ናቸው።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በአዲስ አበባ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው አንድ መቶ ሃያ ስድስት (126) ሰዎች ክፍለ ከተማ ፦
• አዲስ ከተማ - 47 ሰዎች
• ልደታ - 8 ሰዎች
• ጉለሌ - 10 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 14 ሰዎች
• ቦሌ - 11 ሰዎች
• አራዳ - 6 ሰዎች
• የካ - 6 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 4 ሰዎች
• ቂርቆስ - 10 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 7 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 3 ሰዎች
አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ 1,082 ሰዎች ክፍለ ከተማ እንደሚከተለው ቀርቧል ፦
• አዲስ ከተማ - 305 ሰዎች
• ልደታ - 176 ሰዎች
• ጉለሌ - 141 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 110 ሰዎች
• ቦሌ - 99 ሰዎች
• አራዳ - 48 ሰዎች
• የካ - 46 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 41 ሰዎች
• ቂርቆስ - 41 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 29 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 46 ሰዎች

አማራ ክልል!
ዛሬ በ26/9/2012 ዓ/ም በአማራ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ስድስት (6) ሰዎች ሁሉም ወንድ ሲሆኑ ከምዕራብ ጎንደር ዞን ናቸው፤ የእድሜ ክልላቸው ከ23 እስከ 62 ዓመት ውስጥ ይገኛል። ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውና በለይቶ ማቆያ ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ ናቸው።
አጠቃላይ በአማራ ክልል ያለው የቫይረሱ ስርጭት ፦
• ምዕ/ጎንደር - 68 ሰዎች
• ማ/ጎንደር - 1 ሰው
• ጎንደር ከተማ - 3 ሰዎች
• ደሴ ከተማ - 2 ሰዎች
• ባህር ዳር ከተማ - 4 ሰዎች
• አዊ ብሄረሰብ- 3 ሰዎች
• ሰ/ሸዋ - 2 ሰዎች
• ሰ/ወሎ - 3 ሰዎች
• ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን - 1 ሰው
• ደ/ጎንደር - 1 ሰው
• ምስ/ጎጃም (ድንበር ተሻጋሪ) - 1 ሰው
እስካሁን ድረስ በአማራ ክልል 2,230 የላንራቶሪ ምርመራ ተደርጓል ፤ ሰማንያ ዘጠኝ (89) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ ሰባት (7) ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና አገግመዋል።

በ2 ወር ውስጥ 101 ሕጻናት ተደፍረዋል!
ኮሮና ወደ ሀገራችን ከገባ በኅላ ሌላ ገጽታ እያሳየን ይገኛል። ብዙዎች በቤታቸው እንዲቀመጡ በሚመከርበት ወቅት በቤት ውስጥ በሕጻናትና ሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ልብ ሊባል እንደሚገባ ከምንሰማቸው አንዳንድ መረጃዎች መገንዘብ ይቻላል።
በትላንትናው ዕለት በዋልታ ቴሌቪዥን '51 በመቶ' በሚል በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ የአዲስ አበባ ሴቶችና ሕጻናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አልማዝ አብርሃ እንደገለጹት ከ3 ሆስፒታሎች በተገኘ ሪፓርት ብቻ በሁለት ወር 101 ሕጻናት መደፈራቸውን ገልጸዋል።
ይህ ቁጥር ትምህርት ቤቶች በተዘጉበት ፣ ሕጻናት ከቤት በማይወጡበትና ጥቆማዎች ሊደርሱ በማይችሉበት ሁኔታ ይሄን ያህል መጠን መጠቀሱ በራሱ አስደንጋጭ ነው ብለዋል። ከሕጻናት በተጨማሪም በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች እየተበራከቱ መምጣታቸውን ገልጸዋል።
ወይዘሮ አልማዝ ጨምረው እንደገለጹት ከተደፈሩት ሴት ህፃናት በተጨማሪ 57 የሚደርሱ አብዛኞቹ እድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ 'ወንድ ልጆች' እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል።
@tikvahethmagazine @tikvahethiopia

"የ14 እና የ17 ዓመት ልጆች በአባቶቻቸው ተደፍረዋል" - ወይዘሮ ማኅሌት ኃይለማርያም
የኢትዮጵያ ሴቶች መጠለያ ጥምረት ም/ሰብሳቢ ወይዘሮ ማኅሌት ኃይለማርያም 'ከዋልታ ቴሌቪዥን' ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት ጥቃት የተፈጸመባቸው ሴቶችና ሕጻናትን የሚቀበሉ መደበኛ መጠለያዎች በኮሮና ምክንያት አዳዲስ ኬዞችን መቀበል በማቆማቸው በርካታ ዜጎች ተቸግረው እንደነበር ገልጸዋል።
አሁን ላይ አዲስ ኬዞችን የሚቀበል ለስድስት ወር የሚቆይ መጠለያ በቅርቡ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። በመጠለያውም እስከ አሁን 27 የሚደርሱ በጾታዊ ጥቃት ፣ በአስገድዶ መድፈር፣ ልጅ በመካድና በባላቸው ጥቃት የተፈጸመባቸውን ሚስቶች ተቀብሎ እያስተናገደ ነው ብለዋል።
በማዕከሉ ከገቡ ሕጻናት ውስጥ በአባቶቻቸው የተደፈሩ የ14 እና የ17 ዓመት ልጆችን እንደምሳሌነት የጠቀሱት ሰብሳቢዋ ላላስፈላጊ ውርጃ ተጋልጠው ሽንታቸውን መቆጣጠር የማይችሉበት ደረጃ ደርሰው ነበር ብለዋል።
በተለይ የ17 ዓመቷ ልጅ አባትየው የአደንዛዥ እፅ ጭምር እንድትጠቀም ማድረጉን ገልጸዋል። ጥቃቶች አይነትና መልካቸውን እየቀየሩ መምጣታቸውንም ነው የተናገሩት።

#AddisAbaba
በአዲስ አበባ የመቄዶንያ አረጋውያንና አእምሮ ሕሙማንና የጌርጌሶኖን የአእምሮ ሕሙማን ማዕከላት የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የኬሚካል ርጭት ዛሬ ተካሂዷል - #ENA

Debo (3).apk
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
'ደቦ' የንክኪ መለያ መተግበሪያ!
ደቦ ንክኪን መለያ የሞባይል መተግበርያ (አፕሊኬሽን) ከላይ በ 'Reply' ያስቀመጥነውን በመከተል በስልኮ ላይ ይጫኑ። አጠቃቀሙን በቪዲዮው ላይ ይመልከቱ።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ደቦ ንክኪን መለያ የሞባይል መተግበርያ (አፕሊኬሽን) ከላይ በ 'Reply' ያስቀመጥነውን በመከተል በስልኮ ላይ ይጫኑ። አጠቃቀሙን በቪዲዮው ላይ ይመልከቱ።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrTedrosAdhanom የዓለም ጤና ድርጅት /WHO/ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መድሃኒት ለማግኘት ሲጠቀምበት የነበረውን የፀረ ወባ መድሃኒት ፣ ሃይድሮክሲክሎሮክዊን ለጊዜው #አቋረጠ። የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ቦርድ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከአምስት ቀን በፊት በታተመው ላንሰት የሕክምና መጽሔት ላይ የወጣውን የጥናት ሪፖርት መሰረት አድርጎ ነው። በዚህ ጥናት መሰረት መድሃኒቱ…
#DrTedrosAdhanom
የዓለም ጤና ድርጅት [WHO] ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ተቋርጦ የነበረው #የሃይድሮክሲክሎሮክዊን (የፀረ ወባ መድሃኒት) የክሊኒካል ሙከራ ሊቀጥል እንደሆነ በዛሬው ዕለት ተናግረዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዓለም ጤና ድርጅት [WHO] ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ተቋርጦ የነበረው #የሃይድሮክሲክሎሮክዊን (የፀረ ወባ መድሃኒት) የክሊኒካል ሙከራ ሊቀጥል እንደሆነ በዛሬው ዕለት ተናግረዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያና ጎረቤት ሀገራት 16,451 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል!
በኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ ብቻ በአጠቃላይ 16,451 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በተጨማሪ ከላይ በጠቀስናቸው 7 ሀገራት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የ517 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 4,511 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።
በኢትዮጵያ እና በጎረቤት ሀገራት ይለውን የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ መረጃ ከ CARD ጋር ባዘጋጀነው ምስል ከላይ መመልከት ትችላላችሁ።
እናመሰግናለን!

በደቡብ ክልል በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 13 ደርሰዋል!
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ መንግስት ጤና ቢሮ ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ በክልሉ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች አስራ ሶስት (13) መድረሳቸውን አስታውቋል።
ጤና ሚንስቴር በግንቦት 20/2012 ዓ/ም በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ሪፖርት ካደረጋቸው ሰዎች ውስጥ አንዱ የሆነው የክልሉ ነዋሪ ግንቦት 24 ከአዲስ አበባ ወደ ሐዋሳ በመምጣት ላይ እያለ በጥርጣሬ በለይቶ ማቆያ (ሀዋሳ ማቆያ) እንዲቆይ ተደርጓል።
ግለሰቡ በዛው ዕለት በክልሉ በድጋሚ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። በአጠቃላይ እስካሁን በክልሉ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 13 መድረሱ ተረጋግጧል፡፡

በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 17 ደረሰ! ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የሶስት ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል። የመጀመሪያዋ የ71 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፣ ሁለተኛ የ46 ዓመት ወንድ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪ እና ሶስተኛ የ40 ዓመት ወንድ የደቡብ ክልል ነዋሪ ናቸው። የመጀመሪያዋ ግለሰብ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆኑ ሁለቱ (2) ህይወታቸው አልፎ ለአስክሬን ምርመራ በሆስፒታል በተደረገ…
በካፋ ዞን የተመዘገበው ሁለተኛው ሞት!
በትላናንትናው ዕለት በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ካለፈ ሶስት (3) ሰዎች መካከል ከደቡብ ክልል ተብሎ የተገለፀው በካፋ ዞን መሆኑን የዞኑ ጤና መምሪያ አስታውቋል።
ሟቹ በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ አላራገጣ ቀበሌ ሞቶ የተገኘ ሲሆን 'ለአስክሬን ምርመራ' ከተላከ በኃላ በተደረገው ምርመራ ነው በኮሮና ቫይረስ መጠቃቱ የተረጋገጠው።
ከሟቹ ጋር ግኑኝነት ያላቸውን ሰዎች የመለየቱ ስራ የተጀመረ ሲሆን በቦቃ ከተማ ለይቶ ማቆያና በካካ ከተማ በተዘጋጀው ቦታ እየገቡ ይገኛሉ፡፡