TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ኦሮሚያ ክልል ሪፖርት ያደረገው 2 ኬዝ! በፌደራል እና በክልል ጤና ቢሮዎች የሚሰጡ መረጃዎች ሊናበቡና በግልፅ ማብራሪያ ሊሰጥባቸው ይገባል! (ቲክቫህ ኢትዮጵያ) ዛሬ ግንቦት 18/2012 ዓ/ም የጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ላይ በኦሮሚያ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የሚገልፅ መረጃ እንዳልነበር ይታወሳል። የክልሉ ጤና ቢሮ ባወጣው መግለጫ ደግሞ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 648 የላብራቶሪ…
የኮቪድ-19 ታማሚዎች መረጃ ሲሰጥ ግልፅነት የተሞላባቸውና #ብዥታን የማይፈጥሩ ሊሆኑ ይገባል!

(ቲክቫህ ኢትያጵያ)

ትላንት በፌደራል ደረጃ በጤና ሚኒስቴር ከተሰጠው መግለጫ በኃላ የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ይፋዊ በሆነው ማህበራዊ ሚዲያው ላይ ሁለት ሰዎች (1 ሰው ከጅማ እና 1 ከአዳማ) በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የሚገልፅ ሪፖርት ይፋ አድርጎ ነበር።

የክልሉ ጤና ቢሮም ሆነ የፌደራል ጤና ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ምን አይነት ዝርዝር ማብራሪያ እንዳልሰጡ ገልፀን ይህ አይነቱ አለመናበብ ብዥታን ስለሚፈጥን ቢስተካከል በሚል ሀሳብ ማንሳታችንን ታስታውሳላችሁ።

ዛሬ የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ሪፖርቱን ከማህበራዊ ሚዲያው ላይ አንስቶታል። በጉዳዩ ዙሪያ የትኛውም አካል ማብራሪያ አልሰጠም።

በቅድሚያ ለምን ሪፖርት ተደረገ ? ዛሬስ ለምን ተነሳ? መረጃው ትክክል ከሆነ ለምን በፌደራል ደረጃ ትላንት ወይም ዛሬ አልተገለፀም ? በስህተትም ከሆነ ለምን ስህተት ነው ተብሎ በዛው ገፅ ላይ ማብራሪያ አልተሰጠም ? ይህ ሁሉ ጥያቄ ምላሽ ይፈልጋል።

መሰል ሁኔታዎች ታማሚዎች በጨመሩ ቁጥር ከፍተኛ ብዥታን እና መደናገርን በህዝቡ ዘንድ ስለሚፈጥሩ በሚቻለው አቅም ሁሉ #ጥንቃቄ ቢደረግ መልካም ነው።

ከሁሉም ክልሎችና ከፌደራል የሚወጡት መረጃዎች ከምንም በላይ ግልፅነት የተሞላባቸው ፣ የተናበቡ ሊሆኑ ይገባል።

ምንም እንኳን ይህ ወረርሽኝ ለሁሉም አካላት አዲስ እና ፈታኝ ቢሆንም በሚቻለው አቅም ሁሉ ብዥታዎች እንዳይፈጠሩ መስራት ያስፈልጋል።

በሌላ በኩል ዛሬ በኦሮሚያ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዙ የተረጋገጠው የ40 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሰበታ ነዋሪ ነው። ግለሰቡ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌለው ሲሆን በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት በመጣራት ላይ ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia