TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Alert🚨

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከዕለት ወደ ዕለት #እየጨመረ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳውቋል።

ትላንት ለ5,916 ግለሰቦች የኮቪድ-19 ምርመራ ተደርጎ 511 ግለሰቦች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ይህ ማለት ናሙና ከሰጡ 100 ግለሰቦች 9ቱ (9%) የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ትላንት በኮቪድ-19 የመያዝ ምጣኔ ከ68 ቀናት በኋላ የመጀመሪያው ከፍተኛ ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል።

በኮቪድ-19 ቫይረስ ተይዘው ህይወታቸውን የሚያጡ ግለሰቦች ቁጥርም እየጨመረ ይገኛል። በትላንትናው ዕለት ብቻ 8 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ቫይረስ ህይወታቸውን አጥተዋል። ይህ ቁጥር ከ47 ቀናት በኋላ ከፍተኛው የሞት ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል።

ወደ #ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ግለሰቦች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እያሻቀበ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ 25 ግለሰቦች ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የገቡ ሲሆን በአጠቃላይ 308 ግለሰቦች አሁን ላይ በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፤ ይህም ከ53 ቀናት በኋላ ከፍተኛው ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል።

አሁንም ይህ ወረርሽኝ ችላ ሊባል የሚገባው ጉዳይ አንዳልሆነ ያስገነዘበው የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወረርሽኙ የብዙዎችን ህይወት እየነጠቀ ብዙዎችን ደግሞ አካላዊ እና ማህበረሰባዊ ቀውስ ውስጥ እየከተተ ይገኛል ብሏል።

@tikvahethiopia