TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
27 ሚሊዮን ብር የሚገመት አደንዛዥ ዕፅ ወደ አገር ውስጥ ሊገባ ሲል ተያዘ!

የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን በቦሌ አለም አቀፍ አየርመንገድ በኩል ወደ አገር ሊገባ የነበረ 27 ሚሊዮን ብር የሚገመት 10.8 ኪ.ግ የሚመዝን አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።

የጉምሩክ ተቆጣጣሪዎች ባደረጉት ክትትል በቁጥጥር ስር ያዋሉት #ሄሮይን እና #ኮኬን የተባሉ አደንዛዥ እፆችን ነው፡፡ አደንዛዥ እፆቹን አንድ ናይጄሪያዊ ዜጋ በያዘው ቀላል ሻንጣ ውስጥ ደብቆ ለማለፍ ሲሞክር በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ የቦሌ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ተገኔ ደረሰ ለኢቢሲ ገልፀዋል፡፡

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia