TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአማራ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ለመጪዉ ዓመት ለክልሉ የ47.4 ቢሊዮን ብር በጀት አፀደቀ። አራተኛ ቀኑን የያዘዉ የምክር ቤቱ 13ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ጠዋት ያፀደቀዉ በጀት ከቀዳሚዉ በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ3.8 ቢሊዮን ብር ጭማሪ አለዉ።

በሌላ በኩል...

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጀት #እንዲጸድቅ ያቀረበውን 971 ሚሊዮይ 632 ሺህ 330 ብር ምክር ቤቱ አጽድቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኮንስትራክሽን

አስገዳጁ ረቂቅ አዋጅ . . .

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ፤ ትላልቅ #ተቋራጮች ከአነስተኛ የግንባታ ተቋራጮች ጋር በጥምረት እንዲሠሩ #የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን አስታውቋል።

ረቂቁ በከተማና መሰረተ-ልማት ሚኒስቴር ቀርቦ እንደሚገመገም ተገልጿል።

ረቂቁ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት #እንዲጸድቅ ሲደረግ በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማረም በአገሪቱ የሚገኙ ትላልቅና ዋና ዋና ተቋራጮች ከአነስተኛ ትናንሽ ተቋራጮች በጥምረት እንዲሠሩ ዕድሉን የሚፈጥር ነው ተብሏል።

ረቂቅ ህጉን #በአስገዳጅነት እንዲዘጋጅ የተደረገው አነስተኛ አቅም ያላቸው ተቋራጮች ሰፊ ልምድና አቅም ካላቸው ተቋራጮች ጋር በመሥራት ልምድ እንዲያገኙና ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ በማሰብ ነው ተብሏል።

አነስተኛ ደረጃ ያላቸው ተቋራጮች ያልተገባ ተግባር ሲፈጽሙ ተጠያቂ እንዲሆኑ እና #ክፍያ ላይም ምንም ዓይነት ችግር እንዳይገጥማቸው የሚያስችል ሕግ መሆኑ ተገልጿል።

አዋጁን በማርቀቅ ሂደት ፦
- የሕንፃ አማካሪ ድርጅቶች፤
- የሕንፃ ተቋራጭ ማህበራት፤
- በአገሪቱ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች፤
- ፕሮጀክት ያላቸው አካላት፤
- የገንዘብ ሚኒስቴር፤
- የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
- በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚሠሩ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እንደተሳተፉበት ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ፤ አነስተኛ ደረጃ ያላቸው የግንባታ ተቋራጮች እራሳቸውን ብቁ አድርገው መንግሥት በሚያሰማራቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ ድርሻ ይዘው ለመሥራት ከወዲሁ ዝግጅት ያድርጉ ብሏል።

Credit : EPA

@tikvahethiopia