TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በማዳጋስካር በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 169 ደረሱ!

በማዳጋስካር ባለፉት 3 ቀናት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 11 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 169 ደርሷል። ቫይረሱ (ኮቪድ-19) ከተያዙት ውስጥ 101 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን የማዳጋስካር ጤና ሚኒስቴር በዕለታዊ መግለጫው አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በቻይና በኮቪድ-19 ሞት ሳይመዘገብ 12ኛ ቀን ተቆጥሯል ፤ ባለፉት 24 ሰዓት በሀገሪቱ አንድ (1) ሰው ብቻ በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል።

- በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ውስጥ ሰዓት 346 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 31,587 ደርሷል።

- ደቡብ ኮሪያ ከ20 ቀን በኃላ ከ15 በላይ ኬዞችን ሪፖርት አድርጋለች ፤ ባለፉት 24 ሰዓት 18 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

- በስፔን ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 179 ሰዎች በኮቪድ-19 ምክንያት ሲሞቱ 2,666 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በሩሲያ ቫይረሱ የሚሰራጭበት ፍጥነት አስደንጋጭ ሆኗል፤ ትላንት ብቻ 10,817 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 104 ሰዎች ሞተዋል።

- በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 194 ሰዎች መሞታቸው ሲረጋገጥ 1,083 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

- ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በአንድ ቀን 1,024 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ በሽታው ያገገሙ ሰዎች 12,144 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ደቡብ ኮሪያ በምሽት መዝናኛ ውስጥ የተቀሰቀሰውን የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ስርጭት ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገች ነው!

(በቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት)

የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት በሴዑል በአንድ የምሽት መዝናኛ ውስጥ የተቀሰቀሰውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ ነው።

የደቡብ ኮሪያ የበሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል ቅዳሜ ዕለት በቫይረሱ የተያዙ አዲስ 18 ሰዎች ተገኝተዋል ብሏል።

ከእነዚሀም መካከል 17 ወደዚህ የምሽት ክበብ ያቀኑ ናቸው። ለሰዎቹ በበሽታው ለመያዝ ምክንያት ነው የተባለ አንድ የ29 ዓመት ወንድ ተለይቷል።

የሀገሪቱ ጤና ባለስልጣናት ወደ ምሽት ክበቡ የሄዱ ሰዎች እራሳቸውን እንዲያገሉ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ወደ ምሽት ክበቡ ካቀኑ ሰዎች ጋር ግንኙነት ሊኖራቸው የሚችሉ ሰዎችን በመለይት ላይም ናቸው።

የሴዑል ከንቲባ በከተማዋ የሚገኙ መጠጥ ቤቶችና የምሽት መዝናኛ ክበቦች ላልተወሰነ ጊዜ #ዝግ እንዲሆኑ አዘዋል። "የሰዎች ቸልተኝነት ቫይረሱ እንዲቀሰቀስ ያደርጋል" ብለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የማንቂያ ደውል ይሁነን!

ከዚህ ቀደም ከሞያሌ መምጣቱ የተገለፀው ግለሰብ የሀላባ ዞን ባዘጋጀዉ ለይቶ ማከሚያ ማዕከል ዉስጥ ሀኪም ተመድቦለት ተገቢዉን ክትትል እየተደረገለት እንደሚገኝ የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጌታቸው ገልፀዋል።

ግለሰቡ #ፖዘቲቭ ሆኖም እስከአሁን መደበኛ 'ምልክቶችን አለማሳየቱ' ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል 'ማንቂያ ደወል' ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል።

ከዚሁ ግለሰቡ ጋር የቅርብ ንክኪ እንዳላቸዉ የተጠረጠሩ 37 ሰዎች በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸዉ ሲሆን የመጀመሪያ ዙር የምርመራ ዉጤታቸዉ የበፊቱን ሁኔታ ብቻ የሚገልፅ በመሆኑ 15 ቀን ሲሞላቸዉ ሁለተኛ ዙር ምርመራ ተደርጎላቸዉ ዉጤታቸዉ በክልሉ ጤና ቢሮ በኩል የሚገለፅ ይሆናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ የዞኑ ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#KimJongUn #XiJinping

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ቻይና የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝን በመቆጣጠር ረገድ ባስመዘገበችው ስኬት 'የእንኳን ደስ አላችሁ!' መልዕክት ለቻይናው ፕሬዘዳንት ዢ ጅንፒንግ መላካቸውን #KCNA ዘግባል።

ፕሬዘዳንት ዢ ጅንፒንግ ዛሬ ቅድሜ ለኪም ጆንግ ኡን ምላሽ የሰጡ ሲሆን ለላኩላቸው መልዕክት አመስግነዋቸዋል ፤ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታ በሚደረገው ጥረት ከሰሜን ኮሪያ ጎን እንደሚቆሙ ፤ እገዛ ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።

ምንም እንኳን ሰሜን ኮሪያ የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ታማሚዎችን እየደበቀች ነው እየተባለች በተለያዩ አካላት ብትታማም እስካሁን ድረስ በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የተያዘ ሰው ስለመኖሩ ሪፖርት #አላደረገችም

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"እርግዝና እና ኮሮና ቫይረስ"

(በዶ/ር ያቤፅ ከበደ - የጤና ባለሙያ)

እርጉዝ ሴቶች ስለ ኮሮና ቫይረስ(COVID-19) ማወቅ የሚገባቸው ነገሮች፥

ኮሮና ቫይረስ ነፍሰጡር ሴቶች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት በእርግጠኝነት የታወቀ ነገር የለም፤ ነገር ግን እርጉዝ እናቶች፦

- በአንዳንድ ኢንፌክሽኖች የመያዝ እድላቸውን ከፍ የሚያደርጉ በሰውነታቸው ላይ የሚመጡ ለውጦች አሉ

- በኮሮና ቫይረስ እና መሰል ቫይረሶች የተጋለጡ ለከፋ ህመም እንደሚዳርጋቸው አንዳንድ ጥናቶች ያሳያሉ

በወሊድ እና በድህረ ወሊድ ቀጠሮዎቼ ላይ መገኘት እችላለሁን? የሚለው ጥያቄ የብዙ እናቶች አእምሮ ውስጥ የሚመላለስ ነው። ሆኖም ግን በእርግዝና በወሊድ እና በድህረ-ወሊድ ጊዜ ህክምና አለመከታተል የሚያስከትሉት አደጋዎች ለእርስዎ ፣ ለልጅዎ ወይም ለሁለቱም ሊተርፍ ይችላል።

በእርግዝና ወቀት ከእናት ወደ ልጅ በደም የመተላለፍ እድል እስከአሁን ባሉ ጥናቶች በጣም ዝቅተኛ ነው፣ ከወለዱ በኋላ ግን በንክኪ ሊተላለፍ ይችላል፤ በአንፃሩ ደግሞ የእናትጡት ወተት ከብዙ በሽታዎች ይከላከል።

ስለዚህ ነፍሰጡሮች እና ወላዶች በተቻላቸው መጠን ከማነኛውም ሰው ጋር ያላቸውን ንክኪ ማቆም አለባቸው።

በሚያጠቡበት ሰዓት ደግሞ የራሳቸውን ፣ የእጃቸውን ንፅሕና በጣም መጠበቅ እና የፊት ጭምብል ማድረግ ይኖርባቸዋል። እነዚህ እና ሌሎች የጤና ባለሙያዎቻቸው የሚመክሯቸውን ምክሮች በአግባቡ መፈጸም አለባቸው።

በጤና ተቋማት ሲወልዱ እናት ደህና ልጅም ጤና!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የኢትዮጵያና የጎረቤት ሀገራት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ መረጃ ፦

- ጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ 1,189 ፣ ሞት 3 ፣ ያገገሙ 834

- ኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 649 ፣ ሞት 30 ፣ ያገገሙ 207

- ሶማሊያ በቫይረሱ የተያዙ 997፣ ሞት 48 ፣ ያገገሙ 110

- ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 1,111፣ ሞት 59 ፣ ያገገሙ 102

- ኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ 210 ፣ ሞት 5 ፣ ያገገሙ 97

- ደቡብ ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 120 ፣ ሞት 0፣ ያገገሙ 2

- ኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ 39 ፣ ሞት 0 ፣ ያገገሙ 37

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የማንቂያ ደውል ይሁነን! ከዚህ ቀደም ከሞያሌ መምጣቱ የተገለፀው ግለሰብ የሀላባ ዞን ባዘጋጀዉ ለይቶ ማከሚያ ማዕከል ዉስጥ ሀኪም ተመድቦለት ተገቢዉን ክትትል እየተደረገለት እንደሚገኝ የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጌታቸው ገልፀዋል። ግለሰቡ #ፖዘቲቭ ሆኖም እስከአሁን መደበኛ 'ምልክቶችን አለማሳየቱ' ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል 'ማንቂያ ደወል' ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል። ከዚሁ ግለሰቡ ጋር…
የማንቂያ ደውል ይሁነን!

"ሳል፣ ትኩሳት፣ ለመተንፈስ መቸገርና የራስ ህመም የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምልክቶች ቢሆኑም አንዳንድ ሰዎች ምንም አይነት ምልክት ሳያሳዩ #ፖዘቲቭ ሊሆኑና ወደ ሌሎች ሰዎች የማስተላለፍ ዕድል ሊኖራቸዉ ስለሚችል ምልክቶች ታዩም አልታዩ የሚደረጉ መሰረታዊ የጥንቃቄ መመሪያዎችን መተግበር አማራጭ የሌለዉ ተግባር ነው" - አቶ አለማየሁ ጌታቸው (የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrAnthonyFauci

የአሜሪካው ከፍተኛ የሕክምና አማካሪ እንዲሁም የአሜሪካ የኮሮና ቫይረስ ግብረ ኃይል ከፍተኛ ኃላፊ የሆኑት ዶክተር አንቶኒ ፋውቺ በኮሮናቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ መፍጠራቸውን ተከትሎ ራሳቸውን አግልለው ተቀምጠዋል መባሉን BBC አስነብቧል።

የ79 አመቱ ዶክተር አንቶኒዮ ፋውቺ የኮቪድ-19 ምርመራ አድርገው ነፃ መሆናቸው ቢረጋገጥም ተከታታይ ምርመራ እንደሚደረግላቸው የሚመሩት ድርጅት የዩናይትድ ስቴትሱ ብሔራዊ ጤና ኢንስቲትዩት ቃለ አቀባይ ገልፀዋል - #BBC

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ80,000 በላይ ሆኗል ፤ 1.3 ሚሊዮን ሰው በቫይረሱ ሲያዝ 238,000 በላይ የሚሆኑት ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#China #SouthKorea #Russia

- ባለፉት 24 ሰዓት በቻይና አስራ አራት (14) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ ፤ ሁለቱ ከውጭ የገቡ እንደሆኑ ተገልጿል። በቻይና በአንድ ቀን ከ10 በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከ9 ቀናት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

- በደቡብ ኮሪያ በ24 ሰዓት 34 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በደቡብ ኮሪያ ከአንድ ወር በኃላ በአንድ ቀን ከ30 በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

- ሩሲያ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው ፤ ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ 11,012 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። በተጨማሪ 88 ሰዎች ሞተዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 29 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 2,171 ላቦራቶሪ ምርመራ 29 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 239 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ወንድ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ እድሜያቸው ከ15-45 ዓመት የሆኑ ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 21 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ ፣ 7 ሰዎች ከሶማሌ ክልል (ሶማሌ ለይቶ ማቆያ) እና 1 ሰው ከኦሮሚያ ክልል (አዳማ ከተማ በቤት ለቤት አሰሳ እና ቅኝት የተለየ) ይገኛሉ።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 8

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው - 21

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው - 0

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት ሁለት ሰዎች ከአዲስ አበባ ከተማ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ዘጠና ዘጠኝ (99) ደርሷል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#DrLiaTadesse

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 34,860
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 2,171
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 29
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ - 133
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• አዲስ ያገገሙ - 2
• አጠቃላይ ያገገሙ - 99
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 5
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 239

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱዳን ተጨማሪ 53 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸዉ ተረጋገጠ!

(በኢትዮጵያ የሱዳን ኤምባሲ)

የሱዳን ጤና ሚንስቴር ባወጣዉ መግለጫ በትላንትናው ዕለት ተጨማሪ ሃምሳ ሶስት (53) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ 7 (2 ከካርቱም) ሰዎች ህይወታቸዉ ማለፉን እንዲሁም አስራ ሰባት (17) ሰዎች ማገገማቸውን ገልጿል።

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መኖሪያ አድራሻ፦

1. ካርቱም ግዛት 42
2. ሰሜናዊ ኮርዶፋን 4
3. ጋዳሪፍ 5
4. ሰሜን ዳርፉርና ደቡብ ኮርዶፋን አንደ አንድ ሰዉ

በአጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1,164 (ካርቱም ግዛት 976) መድረሱንና ከዚህ ዉስጥ 64 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ 119 ሰዎች በተደረገላቸዉ ህክምና አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በ4 ቀናት ብቻ በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ብዛት ፦

• ሚያዚያ 29/2012 ዓ/ም - 21 ሰዎች

• ሚያዚያ 30/2012 ዓ/ም - 3 ሰዎች

• ግንቦት 1/2012 ዓ/ም - 13 ሰዎች

• ግንቦት 2/2012 ዓ/ም - 21 ሰዎች

በድምሩ በ4 ቀናት 58 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል!

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ በድጋሚ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን ፤ መዘናጋት እና መሰላቸት የሚያስከፍለው ዋጋ ከፍተኛ ነው!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrRashidAman

በኬንያ በትላንትናው ዕለት 32 ሰዎች ማገገማቸውን የኬንያ ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል (እስካሁን በአንድ ቀን ካገገሙ ሰዎች ሁሉ ከፍተኛው ነው) ፤ አጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች 239 ደርሰዋል።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓት 1,056 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 23 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 672 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በ4 ቀናት ብቻ በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ብዛት ፦ • ሚያዚያ 29/2012 ዓ/ም - 21 ሰዎች • ሚያዚያ 30/2012 ዓ/ም - 3 ሰዎች • ግንቦት 1/2012 ዓ/ም - 13 ሰዎች • ግንቦት 2/2012 ዓ/ም - 21 ሰዎች በድምሩ በ4 ቀናት 58 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል! የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ…
ትኩረት በጋራ መኖሪያ ቤቶች አከባቢ!

በአዲስ አበባ በሚገኙ የተለያዩ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አከባቢ ያሉ የመዝናኛ ቤቶች ፣ መጠጥ ቤቶችና ግሮሰሪዎች ከወትሮው ባልተለየ መልኩ ሰዎች ተሰብስበው ይገለገላሉ፡፡

ምንም እንኳን አንዳንድ ቦታዎች ርቀትን ለመጠበቅ የሚመስል ሙከራ ቢኖርም ከቦታቸው ጥበትና ከተገልጋዮች ብዛት የተነሳ ለቁጥጥር አስቸጋሪ መሆኑን ታዝበናል፡፡

ይህንን አተኩረን የምንጠይቀው የጋራ መኖሪያ ቤቶች አከባቢ የሚታየው የጥግግት መጠን ከሌሎች አከባቢዎች እጅጉን ስለሚልቅና ስለሚያሳስበን ነው፡፡ በርካቶች በአንድ የአገልግሎት መስጫ ቦታዎች ስለሚጠቀሙ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrFawziyaAbikar

በሱማሊያ ተጨማሪ 57 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ ተጨማሪ 57 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 1,054 ደርሷል።

በሌላ በኩል ትላንትናው ዕለት ስምንት (8) ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 118 ደርሷል።

በተጨማሪ በሀገሪቱ የሟቾች ቁጥር ወደ ሀምሳ አንድ (51) ከፍ ብሏል ባለፉት 24 ሰዓት የሶስት (3) ሰዎች ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል፤

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትግራይ ክልል ተጨማሪ 2 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ!

የትግራይ ጤና ምርምር ኢኒስቲትዩት ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ መሰረት 86 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን አሳውቋል።

በትግራይ ክልል ደረጃ እስካሁን 694 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ስድስት (6) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ዛሬ በቫይረሱ መያዛቸው በተረጋገጠው ታማሚዎች ዙሪያ የክልሉን የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሓጎስ ጎዶፋይን አነጋግረን ተጨማሪ መረጃዎችን እንሰጣችኃለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrHagosGodefay

ዶክተር ሓጎስ ጎዶፋይ በዛሬው ሪፖርት ላይ የሰጡን አጭር መረጃ ፦

- ሁለቱም (2) #ከጅቡቲ ተመላሽ ሹፌሮች ናቸው።

- እድሜያቸው 30 እና 38 ዓመት ነው።

- በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ናቸው።

- ምንም ምልክት አይታይባቸውም።

- ከጅቡቲ ወደ ትግራይ ክልል የገቡት ሚያዚያ 29 ነው።

ዛሬ አመሻሹን በትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ሪፖርት የተደረገው ኬዝ 10:00 ነው ውጤቱ #የደረሰው ፤ በ24 ሰዓቱ የፌደራል ጤና ሚስቴር መግለጫ ያልቀረበው በዚህ ምክንያት ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia