TIKVAH-ETHIOPIA
ሰለሞን ቱፋ ለ ነሀስ 🥉 ሜዳሊያ ይወዳደራል ! የጃፓኑን ተጋጣሚው ሰርጅዮ ሱዙኪ በመርታት ወደ ሩብ ፍፃሜው ያለፈው ሰለሞን ቱፋ ደምሴ በቱኒዚያው ተፎካካሪው በነጥብ ልዩነት ቢሸነፍም በተሻለ ነጥብ ወደ ቀጣዩ ዙር በማለፍ ተጫማሪ ውድደሩን ያደርጋል። ሰለሞን ቱፋ ዛሬ ከ ቀኑ 7:15 ላይ ከ ሩሲያዊው አርታሞኖቭ ሚኪሀሊ ጋር የሚፋለም ይሆናል። ሰለሞን ቱፋ የነሀስ ሜዳልያ ለማግኘት በሚደረገው ፉክክር ከሩሲያ…
#Tokyo2020 #Ethiopia🇪🇹
ሰለሞን ቱፋ በመጨረሻም የሶስተኛ ዙር ጨዋታውን ተሸንፎ ለ ነሀስ ሜዳልያ ከሚደረገው ውድድር ውጪ ሆኗል።
በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያን በመወከል በ58 ኪሎ ግራም በ ወርልድ ቴኳንዶ የተሳተፈው ሰለሞን ቱፋ በመጀመሪያ ጨዋታው የጃፓኑን ተጋጣሚው ሱዙኪ ሰርጂዮን በመርታት ወደ ሩብ ፍፃሜ ያለፈ ሲሆን በሩብ ፍፃሜው በቱኒዚያው ተፎካካሪው ተሸንፏል።
ቱኒዚያዊው ሞሀመድ ካሊል 32 ለ 9 በሆነ የ ነጥብ ልዩነት ሰለሞን ቱፋን በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜው አልፏል ።
ሰለሞን ቱፋ በ2ቱ ጨዋታዎች በሰበሰበው ነጥብ የ ነሀስ ሜዳለያ ለማግኘት በሚደረገው ፉክክር ከ ሩሲያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ተወዳዳሪ አርታሞኖቭ ሚካዬል ጋር ጨዋታ አድርጎ በድምር ነጥብ 27 ለ 5 ተሸንፎ የቶክዮ ኦሊምፒክ ውድድር ጨዋታዎቹን አጠናቋል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሎምፒክ ታሪካችን በወርልድ ቴክዋንዶ እንድንወከል ላደረገን እና በውድድሩም ጥሩ ተጋድሎ በማድረግ መፎካከር በቻለው ሰለሞን ቱፋ 🇪🇹 ኮርተናል።
[#HawaryawPetros]
ስፖርታዊ ጉዳዮች @tikvahethsport

#Tokyo2020
የ12 ዓመቷ ሶሪያዊ ታዳጊ በቶኪዮ ኦሎምፒክ !
በዘንድሮው የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ከሚሳተፉ ሀገራት መካከል ሶርያ ትገኝበታለች።
በውድድሩ ላይ በእድሜ ትንሿን ተወዳዳሪ የምታሳትፈው ሶርያ ስትሆን ተወዳዳሪዋ የ12 ዓመቷ ሄንድ ዛዛ ናት ፤ ዛዛ በጠረጴዛ ቴኒስ ነው ሀገሯን ሶሪያ ወክላ በዓለም አቀፉ ውድድር የሚትፋለመው።
የቶኪዮ በእድሜ ትንሿ ተወዳዳሪ ሄንድ ዛዛ በ ኦሎምፒክ የ መጀመሪያ ጨዋታዋ ብትሸነፍም ሌሎች ሕፃናት “ ሕልማቸውን እንዲከተሉ ” ታበረታታለች።
በልጅነቷ በሀገሯ በጦርነት የተጎዳችው ዛዛ ወደ ውድድሩ ለመድረስ “ብዙ የተለያዩ ችግሮችን” ማለፍ እንደነበረባት ተናግራለች።
የቶኪዮ መረጃዎችን ይከታተሉ : @tikvahethsport

ታዳጊዋ ለሀገሯ ወርቅ አስገኘች !
የ13 ዓመቷ ጃፓናዊት የ #SkateBoard ተወዳዳሪ ሞሚጂ ኒሺያ ለሀገሯ ጃፓን በውድድር ዘርፉ የመጀመሪያውን ወርቅ አስገኝታለች።
ሞሚጂ ኒሺያ በ ታሪክ ለ ሀገሯ ወርቅ ያስገኘች በ እድሜ ትንሿ ተወዳዳሪም ለመሆን በቅታለች ።
@tikvahethsport

#Ethiopia 🇪🇹 #Tokyo2020
ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የመጀመሪያውን ዲፕሎማ አግኝታለች።
በወርልድ ቴኳንዶ የመጀመሪያ ተሳትፎን በኦሎምፒክ ያደረገው ሰለሞን ቱፋ 7ኛ ደረጃን በ መያዝ ዲፕሎማውን መረከቡን #EOC አሳውቋል።
Via @tikvahethsport

#ETHIOPIA 🇪🇹 #Tokyo2020
ዛሬ ሌሊት ከ9፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚደረጉ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ የአለም አትሌቲክስ ባወጣው የተወዳዳሪዎች ዝርዝር መሰረት ከዚህ በታች የተገለፁ የሀገራችን አትሌቶች ውድድሮቻቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል።
በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ፦
- ሀብታም አለሙ
- ነፃነት ደስታ
- ወርቅውሃ ጌታቸው
በ3000 ሜትር መሰናክል ወንዶች ማጣሪያ ፦
- ጌትነት ዋለ
- ለሜቻ ግርማ
- ታደሰ ታከለ
ድል ለሀገራችን🇪🇹ኢትዮጵያ !

#Tokyo2020 🇪🇹 #ETHIOPIA
ሰለሞን ባረጋ ወርቁን አጥልቋል !
በትላንትናው ዕለት ለኢትዮጵያ የመጀመሪያው ወርቅ ያስገኘው ሰለሞን ባረጋ ከደቂቃዎች በፊት ከቀድሞው የኬንያ አትሌት እና ከአሁኑ የ ኬንያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ፖል ቴርጋት ወርቁን ተረክቦ አጥልቋል።
ኢትዮጵያ በሜዳሊያ ሰንጠረዡ ከዓለም ሰላሳ ሰባተኛ ላይ ስትቀመጥ ከአፍሪካ በሜዳሊያ ዝርዝር ውስጥ ከደቡብ አፍሪካ እና ቱኒዚያ በመቀጠል ሶስተኛ ላይ ተቀምጣለች።

ሀብታም አለሙ በ800 ሜትር ውድድር ሁለተኛ በመውጣት ለፍፃሜ ማለፏን አረጋግጣለች።
ሀብታም አለሙ የ ፍፃሜ ውድድሯን በመጪው ማክሰኞ ቀን 9:25 የምታደርግ ይሆናል።

በ3 ሺ ሜትር መሰናክል ማጣሪያ በተደረገ ውድድር ኢትዮጵያዊያኖቹ መቅደስ አበበ ሶስተኛ ደረጃ እንዲሁም ዘርፌ ወንድማገኝ በምርጥ ሰዓት 4ኛ ደረጃን በመያዝ ለፍፃሜው ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።
በመጀመሪያው ምድብ ተወዳድራ የነበረው አትሌት ሎሚ ሙለታ 10ኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ሳትችል ቀርታለች።
የ3 ሺ ሜትር መሰናክል የፍፃሜ ውድድር በመጪው ዕሮብ ከ ቀኑ 8:00 ጀምሮ የሚካሄድ ይሆናል።

በ1,500 ሜትር ማጣሪያ በተደረገ ውድድር ኢትዮጵያዊያኖቹ ፍሬወይኒ ሀይሉ እና ለምለም ሀይሉ ከ ምድባቸው አምስተኛ ደረጃን በመያዝ ለግማሽ ፍፃሜው ማለፋቸውን አረጋግጠዋል ።
በሶስተኛው ምድብ ተወዳድራ የነበረው አትሌት ድርቤ ወልተጂ 12ኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ሳትችል ቀርታለች።
የ1,5000 ሜትር የግማሽ ፍፃሜ ውድድር በመጪው ረቡዕ ከቀኑ 7:00 ጀምሮ የሚካሄድ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ጀግና ልጆች ለሜቻ ግርማ እና ጌትነት ዋለ በተሳተፉበት የ3000 ሜትር መሰናክል ወንዶች ፍፃሜ ውድድር ለሀገራቸው መልካም ውጤት አስመዝግበዋል።
ለሜቻ ግርማ በ8:10.38 2ኛ ሆኖ በመግባት ለኢትዮጵያ የብር ሜዳልያ ሲያስገኝ ጌትነት ዋለ በ8:14.97 4ኛ ደረጃም ይዞ በማጠናቀቅ ዲፕሎማ አስገኝቷል።
በዚህ ርቀት የውድድር ዘርፍ የኬንያውያን የበላይነት የተገታ ሲሆን የዛሬውን ውድድር የሞሮኮ አትሌት ሱፊአኔ ባካሊ በበላይነት አጠናቋል።
@tikvahethiopia