TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrLoiceAchiengOmbajo

የኬንያ ተመራማሪዎች ለኮሮና ቫይረስ መድሃኒት ይሆናሉ ተብለው የሚገመቱ ሶስት መድሃኒቶች የክሊኒካል ሙከራ እስከሚደረግባቸው እየጠበቁ እንደሆነ ተገልጿል።

ተመራማሪዎቹ ሙከራ እስከሚደረግባቸው የሚጠብቋቸው መድሃኒቶች ኢቦላን ለማከም የሚውለው ሬምደስቪር፣ የወባ መድሃኒት እና ከኤች አይ ቪ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ኢንፌክሽኖችን ለማከም የሚውለው ሊፖናቪር ናቸው።

ዋና ተመራማሪዋ ዶ/ር ሎይስ አቺንግ ኦምባጆ እንደገለጹት ሙከራዎቹ የሚደረጉት ዓለማ አቀፍ ስርዓቶችን ተከትሎ ነው። የምርምር ስራውን ማን በገንዘብ እየደገፈው እንደሆን ግን የተባለ ነገር የለም።

በተመራማሪዋ መረጃ መሰረት የአገሪቱን የመድሃኒቶች ቦርድ እንዲሁም የብሄራዊ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ካውንስል ይሁንታ እስከሚያገኙ እየጠበቁ ነው - #BBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia