TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የሬሜዲያል ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች ፈተናቸውን ከነሐሴ 23 – 26 ቀን 2015 ዓ.ም በኦንላይን እንደሚወስዱ አሳውቋል።

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈትነው ማለፊያ ነጥብ (50%) ሳያመጡ የቀሩ ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማካካሻ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው የማካካሻ ትምህርት ፈተናን ከሰኔ 26-30 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲወስዱ መደረጉ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ከተፈታኝ ተማሪዎች እና የማካካሽ ትምህርቱን ከሚሰጡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቁጥር አንፃር እንዲሁም በወቅቱ በተከሰተው ችግር ምክንያት በሁለት የመንግስት እና በ143 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማካካሻ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለነበሩ ተማሪዎች የሪሜዲያል ፈተናውን ለመስጠት ባለመቻሉ በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም ፈተናውን እንዲወስዱ ተወስኖ ነበር፡፡

ሚኒስቴሩ በቅርቡ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቦርድ አባላት ጋር ጉዳዩን አስመልክቶ ባደረገው ውይይት እና በተደረሰው ስምምነት መሰረት ፈተናው ከነሐሴ 23 – 26 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲሰጥ ተወስኗል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፦

- ፈተናው #በበይነ_መረብ እንዲሰጥ ከስምምነት ላይ የተደረሰ በመሆኑ አብዛኞቹ ተማሪዎች ግን የኮምፒዩተር ክህሎት ስለሚያንሳቸው እያንዳንዱ ተቋም ከወዲሁ ተማሪዎቹን በማሰልጠን የማብቃት ስራ እንዲሰራ፣

- ተፈታኞች የ #ፊዚክስ እና የ #ታሪክ ኮርሶች በሪሜዲያል ፈተና ውስጥ እንደማይካተቱ አውቀው በሌሎች ትምህርት ዓይነቶች ላይ አተኩረው ዝግጅት እንዲያደርጉ እንዲደረግ፤

- ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ፈተናውን የሚወስዱበት ተቋም ወይም ቦታ በመለየት ከተፈታኝ ተማሪ ቁጥር ጋር በቶሎ እንዲያሳውቁና ተማሪዎቹ ከዋናው ፈተና በፊት ልምምድና ከፈተና ሶፍትዌር ጋር ትውውቅ እንዲያደርጉ ሞዴል ፈተናዎችን እንዲፈትኑ ፤ ፈተናው የሚሰጥባቸው ከየመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችም ከኢንተርኔት ጋር የተገናኙ ኮምፒዩተሮችን ለዚህ ስራ ዝግጁ በማድረግ ጠንካራ ክትትል እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

(በዶ/ር ኤባ ሚጄና - የአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ ተፈርሞ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፣ ለሐረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፣ ለሐረር መምህራን ኮሌጅ የተላከው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)

More : @tikvahuniversity

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia