TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Oromia

" የልዩ ኃይል ስምሪት አቁመናል ፤ ... በክልሉ ያለውን የፀጥታ ማስከበር ሥራ የአገር መከላከያ ሠራዊት ተረክቧል " - የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የልዩ ኃይል አደረጃጀት ስምሪት ማቆሙን አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ነው ይህንን ያሳውቁት።

ዋና ኮሚሽነሩ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፤  የፌዴራሉ መንግሥት ባስተላለፈው መሠረት የልዩ ኃይል አደረጃጀት መዋቅርን በተለያዩ የፀጥታ መዋቅሮች መልሶ የማደራጀቱ ተግባር እየተከናወነ ነው ብለዋል።

በክልሉ ያለውን የፀጥታ ማስከበር ሥራንም #የአገር_መከላከያ_ሠራዊት መረከቡን ገልጸዋል።

" የልዩ ኃይል አደረጃጀት ቀድሞውኑም ለጊዜያዊ የፀጥታ ችግር ያለ ሕገ መንግስታዊ መርህ ነው " የተመሰረተው የሚሉት ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ ለሁሉም ክልሎች በወጥነት ተላልፏል ያሉትን መዋቅሩን በሌላ ፀጥታ ተቋማት የማደራጀቱ ሥራ እየተተገበረ ነው ብለዋል።

" ግንዛቤ ውስጥ መግባት ያለበት የሚፈርስ የሚለው መልሶ ለመገንባት በሚል መወሰድ አለበት። እንደ ወንጀለኛ ፈርሶ የሚሳደድ አካል የለም። አደረጃጀቱ ስህተት ስለነበረበት በዚህ መደራጀት አለበት የሚል ነው መወሰድ ያለበት። አንድ ሕጋዊ ክፍተት መኖሩ ሲሆን ሌላው የሚገዳደር የተለያዩ የፀጥታ መዋቅሮች በአንድ አገር ውስጥ አያስፈልግም በሚል የፀጥታ ችግሮች በመከላከያ፣ በፌዴራል ፖሊስ እና በክልሎች መደበኛ ፖሊስ በየደረጃው እንዲሠራ በሁሉም ውይይት ተደርጎበት የተወሰነው። " ሲሉ ተናግረዋል።

ውሳኔው ሁሉንም ክልሎች የሚመለከት እንደሆነ የገለፁት ኮሚሽነር አራርሳ በተደረገው ውይይትና በተደረሰበት ስምምነትም አተገባበሩም በአንድ ላይ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

ሂደቱን የአገር መከላከያ እንደሚያስፈጽም መወሰኑንም አመልክተዋል።

" የፌዴራል መንግሥት ውሳኔውን ያስተላለፈው ሁሉም ክልሎች ተግባራዊ እንዲያደርጉ ነው። ከዚያ ውስጥ ኦሮሚያ አንዱ እንደመሆኑ መመሪያውን ተቀብለን በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት እያደራጀን ነው። ኦሮሚያ አላፈረሰም ለአንዳንድ ክልል ብቻ የተላለፈ ነው ሚለው እውነት አይደለም ብቻ ሳይሆን በሬ ወለደ እንደ ማለት ነው። ይሄ የሚደበቅም ስላልሆነ ምንም የተለየ ማብራሪያ አያሻውም። ንጹሑ ህዝብ ግን እንዳይደናገር ውሳኔው ማንንም የሚመለከት መሆኑን ቢገነዘሙ መልካም ነው። " ብለዋል።

አሁን በክልሉ የሚሰማራ የልዩ ኃይል አደረጃጀት የለም ያሉት ኮሚሽነር አራርሳ በመከላከያ፣ በፌዴራል ፖሊስ እና በክልል መደበኛ ፖሊስ እንደየሚያስፈልገው መስፈርት እየተደራጁ ለስልጠና እየተሰማሩመሆኑንም ተናግረዋል።

" በሁሉም የፀጥታ መዋቅሮች አልደራጅም ያለ አሊያም በጡረታ መገለልም ያለበት በደንቡ መሰረት የመሸኘቱ ሥራ እየተተገበረ " ነው ብለዋል።

#ዶቼቨለ_ሬድዮ

@tikvahethiopia