TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጥንቃቄ ይደረግ🔝

ወደሀዋሳ ጉዞ ላይ የምትገኙ #አሽከርካሪዎች ከመቂ በኃላ መንገዱ በከፊል በአቧራ በመሸፈኑ #ለእይታ እጅግ አስቸጋሪ ነው፤ እባካችሁ በጥንቃቄ አሽከርክሩ...

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሽከርካሪዎች_ጥንቃቄ_እያደረጋችሁ

በዛሬዉ ዕለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰዎች ህይወት አለፈ።

አደጋዉ የደረሰዉ በምስራቅ ጎጃም ዞን እናርጅ እናዉጋ ወረዳ ደያጠባ ቀበሌ ነው።

ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ላይ ከሞጣ ወደ ብቸና ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ ኮድ (3) 78101አአ ሃይሉክስ እና ከደብረወርቅ ወደ ፈለገ ብርሃን ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ ኮድ (3) 16049 አማ የሆነ ዶልፊን የህዝብ ማመላለሻ መኪና እናርጅ እናዉጋ ወረዳ ደያጠባ ቀበሌ በመጋጨታቸው የሀይሉክሱን ሾፌር ጨምሮ የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ዋና ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ልጅአዱኛ ሙሉጌታ እንደገለጽት ሌሎች አደጋ የደረሰባቸዉ 3 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፤ ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎችም በደብረወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እየተረዱ መሆኑን ገልፀዋል።

የአደጋዉ መንስኤ እየተጣራ መሆኑ ተገልጿል።

በተለይ በዓላት በሚቃረቡበት ግዜ እና የበዓል ዕለት አሽከርካሪዎች ፍጥነታቸውን በመቀነስ እና አደጋን ተከላክሎ የማሽከርከር ብቃትን በማሳደግ በአጠቃላይ ለአደጋ በማይዳርግ ሁኔታ በማሽከርከር የራስ ህይወት እና የዜጎችን ህይወት ከሞት መታደግ ይገባል በማለት አሳስበዋል።

መረጃው የደረሰን ከምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ነው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሹፌሮች ጉዳይ . . . " በ2 ሳምንታት ብቻ ሰባት ሹፌሮች በታጣቂዎች ተገድለዋል። ከ2014 ዓ/ም ጀምሮ የተገደሉት ወደ 70 ይደርሳሉ " - ጣና የአሽከርካሪዎች ማኀበር በጅማና በአዲስ አበባ ከተማ መካከል ‘አስጎሪ’ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ሲያሽከረክሩ በነበሩ ሹፌሮችና ተሽከርካሪዎች ላይ ታጣቂዎች ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ/ም ጥቃት ማድረሳቸውን ስሜ ከመጠቀስ ይቆይ ያሉ የዓይን እማኝ ለቲክቫህ…
#አሽከርካሪዎች 

“ ታጣቂዎች ሌመን አካባቢ በከፈቱት ተኩስ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። መረጃው እውነት ነው ”- የዓይን እማኝና ባለስልጣን

“ በ3 ዓመታት ውስጥ 100 የሚደርሱ አሽከርካሪዎች በወንበዴ ጥይት ሕይወታቸው ሲቀጠፍ፣ ንብረት በየሜዳው ሲነድ፣ ገዳይን አሳደው ለሕግ ሲያቀርቡ አላየንም ” - የሹፌሮች አንደበት

በተለያዩ አካባቢዎች ላይ ሲከሰት ቢስተዋልም በተለይ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ታጣቂ ቡድኖች አማካኝነት “ የገበያ ዕቀባ ” የሚል የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ በመግታት፣ በሚንቀሳቀሱ ሹፌሮችና ተጓዦች ግድያ፣ የተሽከርካሪዎች ቃጠሎ በስፋት እየተፈጸመ መሆኑን ባለስልጣን፣ የዓይን እማኝና ሹፌሮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

“ ሰሞኑን ከአዲስ አዲስ አበባ ወደ ወላይታ ሶዶ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ የሸኔ ታጣቂዎች ሌመን አካባቢ በከፈቱት ተኩስ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። ሬሳቸውም ወደ ወላይታ ሶዶ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ተወስዷል ” ሲሉ አንድ የዓይን እማኝ ገልጸውልናል።

የተገደሉበት ምክንያት ምን እንደሆነ እንዲያስረዱ ሲጠየቁም፣ “ ታጣቂዎቹ ‘የገበያ ዕቀባ’ በሚል ሰሞኑን ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ አግደው ስለነበር ነው ” ብለዋል።

“ ሁለት ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ ” መባሉ እውነት ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው ሟቾቹ የሚኖሩበት ወረዳ አንድ ባለስልጣን “ ልክ ነው። መረጃው እውነት ነው ” ሲሉ አረጋግጠዋል።

“ ታጣቂዎች ናቸው የገደሏቸው ” የሚል መረጃ ደርሶናል ይህስ እውነት ነው ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄም፣ “ አዎ በታጣቂዎች ነው። እውነት ነው ” ብለዋል።

አንድ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ሹፌር በበኩላቸው፣ “ መንግሥት የትራንስፖርት አገልግሎት ስጡ ይላል። ታጣቂዎች በገሀድ መንገድ በመዝጋት ሹፌሮችን ይገድላሉ። እዚህ አገር አዛዡ ማነው ? ” ሲሉ ጠይቀዋል።

አክለውም፣ “ ሹፌሮች በሰላም ወጥቶ መግባት ብርቅ ሆኖባቸዋል። በርካቶች እንወጡ እየቀሩ ነው። መንግሥት ለዚህ ጉዳይ መፍትሄ የማይሰጠው ለምን ይሆን ? ምን ሰርተንስ ቤተሰብ እናስተዳድር ? ” የሚል ጥያቄም አንስተዋል።

የአሽከርካሪዎችን ሁኔታ በየወቅቱ በመከታተል የሚታወቀው የሹፌሮች አንደበት በበኩሉ፣ “ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በአገሪቱ በ3 አመታት ጊዜ ውስጥ 100 የሚደርሱ አሽከርካሪዎች በወንበዴ ጥይት ሕይወታቸው ሲቀጠፍ፣ ንብረት በየሜዳው ሲነድ፣ ገዳይን አሳደው ለሕግ ሲያቀርቡ አላየንም ” ሲል ወቅሷል።

አክሎም፣ “ ወንበዴን አሳዶ መያዝ፣ አድኖ መቅጣት ያልቻለ ኃይል እና አካል የእንቅስቃሴ እቀባን ተግብረው ከተማ የሚቆሙትን ‘ውጡ’ በማለት አስገድደው ልከው እንዲቃጠሉ አድርገዋል። ሶስት (3) የሚደርሱ ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸው መረጃ ደርሶናል ” ብሏል።

ለጉዳዩ ምን ምላሽ እንዳለቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ወደ ኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ያደረገው ሙከራ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ባይሳካም፣ ኃላፊው ጉዳዩን በተመለከተ ሰሞኑን ለኢፕድ በሰጡት ማብራሪያ፣ “ አሸባሪው ሸኔ የጠራው የገበያ አድማ በሕዝብና መንግሥት የተቀናጀ ሥራ ማክሸፍ ተችሏል ” ብለዋል።

መረጃው በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።

ፎቶ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሲጀመር ‘የኮቴ’ ክፍያ አገር ውስጥ መጠየቅ አግባብ አይደለም " - ጣና የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ማኀበር የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ፣ ሞጆ መግቢያ ‘ #የኮቴ ’ በሚል ታጣቂዎች አስቁመው 2,000 ብር እያስከፈሏቸው መሆኑን እየገለጹ ይገኛሉ። ካሁን ቀደም ገንዘቡን ሲጠየቋቸው የነበረው አንዳንድ ጊዜ በቀን እንደነበር ፣ ከሰሞኑን ግን ቀንም ሌሊትም እየጠየቋቸው ከመሆኑም ባሻገር ድብደባና…
#Ethiopia

“... የፌደራል ፓሊስ በፓትሮል መንገድ ላይ ወጥቶ እንዲሰራ ሁሉ ተደርጓል ” - ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር

የድንበር ተሻጋሪ የከባድ መኪና #አሽከርካሪዎች አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ በታጠቁ ኃይሎች እስከ ግድያ የሚድረስ ጥቃት እንደሚፈጸምባቸው መግለጻቸውን በተደጋጋሚ መረጃ ተለዋውጠን ነበር።

አሽከርካሪዎቹ፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ እየሰጠ እንዳልሆነ በመውቀስ የጥቃት መጠኑ ይለያይ እንጂ እስከ ቅርብ ጊዜ እንደቀጠለ ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈ ሀገር ውስጥ ገብተው የ " ኮቴ " እየተባለ የሚከፍሉት ክፍያ እጅግ ለስራቸው ፈተና እንደሆነ አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች እየደረሰብን ነው ያሉትን ችግር ለመቅረፍ በተጨባጭ ምን እየተሰራ ነው ? ሲል የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴርን ጠይቋል።

የተቋሙ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ ዶ/ር ቶለሳ በሰጡት ምላሽ ፣ “ ኢትዮጵያ ውስጥ ከገቡ በኋላ ሞጆ ወይንም ደግሞ ማራገፊያ ቦታ እስከሚደርሱ ነበር አሁን በጣም ቁጥጥር እየተደረገ ነው ” ብለዋል።

“ ከሚኒስቴር መ/ቤታችንም ሌላም አካል Direction ተሰጥቶ፣ እንዲያውም #የፌደራል_ፓሊስ በፓትሮል መንገድ ላይ ወጥቶ እንዲሰራ ሁሉ ተደርጓል ” ነው ያሉት።

“ ስለዚህ እኛ እንደዚህ አይነት #እሮሮ ይደርስባቸዋል የሚል መረጃ የለንም ” ያሉት ዶክተር ቶተሳ፣ “ አዲስ የመጣ ነገር የለም። #እየተሻሻለ_መጣ_እንጂ ” ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፣ አሽከርካሪዎቹ አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ “ በተለይ ኦሮሚያ ክልል” የ “ #ኮቴ ” እየተባሉ 2,000 እንደሚከፍሉና ከዚህም አለፍ ሲል ድብደባ ጭምር እየደረሰባቸው መሆኑን እየገለጹ ነው። እናንተ ደግሞ ‘ ችግሩ እየቀነሰ ነው ’ እያላችሁ ነው። ለዚህ ቅሬታ ምላሽዎ ምንድን ነው ? የሚል ጥያቄ አቅርቧል።

ዶ/ር ቶለሳ “ አዎ ይኼኛውን እኛም ከጭነት ተሽከርካሪ ተወካዮች ጋር ስብሰባ አካሂደን ነበር። በዚህም ወቅት ክፍያ እንደሚያስከፍሉ ሰምተናል ” ብለዋል።

ችግሩን ለመቅረፍ ከከተማው አስተዳደር ጋር ውይይት እንደሚደረግ ገልጸዋል። “ #ድብደባ ለሚባለውን ግን መረጃ የለንም። ካለ እንሄድበታለን ” ብለዋል።

“ ከኦሮሚያ ክልል መንግስትም ጋር አውርተን መፍትሄ የምንሰጥ ይሆናል ” ሲሉም አክለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#ቴፒ #አሽከርካሪዎች

° “ ከቴፒ ቡና ጭነን ለመውጣት ተከልክለን ከቆምን ወር ሊሞላን ነው ” - አሽከርካሪዎች

° “ ክልል ኮሚቴ አቋቁቁሞ ነገሩን እያጣራ ነው ”- ቡናና ሻይ ባለስልጣን

የጫኑትን ቡና ይዘው እንዳይንቀሳቀሱ በመከልላቸው ያለምንም መፍትሄ ከሦስት ሳምንታት በላይ ለመቆም እንደተገደዱ አሽከርካሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረዋል።

“ ለሥራ የምንወጣው ቤተሰቦቻችንንም ለማስተዳደር ነው ” ያሉት አሽከርካሪዎቹ፣ “ ሥራ ፈትተን የቆምንበት ጊዜ ቀላል አይደለም። እንኳን ቤተሰብ ልናስተዳድር ለእኛም ለእለት ለምግብ ገንዘብ ተቸግረናል ” ብለዋል።

“ የተከለከልንበትን ምክንያት እንኳን #አላወቅንም። መንግስት ግን አሽከርካሪዎች እያስተናገዱት ላለው ተደራራቢ ችግር መፈትሄ የማይሰጠው እስከመቼ ነው? ” ሲሉ ጠይቀዋል።

አንዳንዶቹ በወባ ተይዘው መተኛታቸውንም ለመስማት ችለናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ አሽከርካሪዎቹ ጉዳዩን በተመለከተ ይጠየቅልን ያሉት ቡናና ሻይ ባለስልጣንን ችግር ለምን ተፈጠረ? ችግሩን ለመቅረፍስ ምን እየተሰራ ነው? ሲል ተይቋል።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የግብይት ዘርፋ ኃላፊ አቶ ሻፊ ዑመር፣ “ ቡና በአገር ኢኮኖሚ፣ የአገር ሀብት ነው። ይቺ ቡና ከሌለች አገርም የለችም ማለት ይቻላል። 40 በመቶ ገደማ ቡና ነው ይዞ ያለው ” የሚል ቃል ሰጥተዋል።

“ ግን ቴፒ ላይ እያደረጉ ያሉት የExport ቡናን በአፈር እያሹ፣ በውሃ እያሹ ወደ Local መልሰው ቡናው ለExport እንዳይሆን እያደረጉ ነው፤ አቅራቢዎቹ ” ብለዋል።

“ ጅምላ ነጋዴዎቹ ይሄ ቡና በውሃና በአፈር ታሸ እንጂ ንጹህ ስለሆነ ጥሩ ያወጣላቸዋል። ለመሸጥ ነው የሚፈልጉት ” ያሉት አቶ ሻፊ፣ “ ለዚህ ደግሞ ብዙ ጊዜ መመሪያ አውጥተን ችግሩ እንዲቆም ብዙ ጊዜ ተናግረን ሳይፈታ ቀረ ” ሲሉ አስታውሰዋል።

አክለው፣ “ ይህ ብቻ ሳይሆን በአፈር የታሸ ቡናም መጋዚን ውስጥ አከማችተዋል። ይህ አገር ማጥፋት፤ አገርን ገቢ ማሻጣት ነው ” ብለዋል።

“ ላለፉት ስድስት (6) ወራት ቴፒ ብቻ ከሀምሌ እስከ ታህሳስ ድረስ 34 በመቶ ንጹህ ቡና Local ነው የወጣው። ስለዚህ ምንም Local የማውጣት መብት የላቸውም። የሚያወጣው ማዘጋጃና ማከማቻም በአካባቢው የለም ” ነው ያሉት።

መፍትሄውን በተመለከተ ፤ “ አሁን ላይ ጉዳዩን ለክልል ሰጥተናል። ክልል ኮሚቴ አቋቁሞ ነገሩን እያጣራ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

ስለዚህም አሽከርካሪዎቹ እንዳይንቀሳቀሱ የተደረጉት የExport ቡናን ወደ Local በሚለውጡ አቅራቢዎች መሆኑን ያስረዱት አቶ ሻፊ፣ “ እንደዚያ በሚያደርጉት ላይ ባለሙያዎች አጣርተው እርምጃ እንዲወሰድ ኮሚቴ ተቋቁሟል ” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia