TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እስቴ ወረዳ‼️

በቤተ እምነቶቹ ላይ የደረሰው #ቃጠሎ አማኞችን እንደማይወክል የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አስታወቀ፡፡ ድርጊቱ ሀይማኖትን በመጠቀም ኢትዮጵያ ሰላም እንዳትሆን የሚፈልጉ አካላት እንደሆነም ነው ምክር ቤቱ ያስታወቀው፡፡

በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን እሰቴ ከተማ ቀበሌ 03 ላይ ሁለት #መስጊዶች #ተቃጥለዋል፡፡ ጉዳቱ የደረሰው ጥር 26/ 2011ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 አካባቢ ነው፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ አብመድ ያነጋገራቸው የአማራ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ጸሃፊ #ሼህ_ሙሀመድ_ሀሰን ድርጊቱ ለበርካታ ዘመናት በፍቅር የኖሩትን ህዝቦች #ለማለያየት ያለመና ሁለቱንም ወገኖች የማይወክል መሆኑን አሥረድተዋል፡፡

ትናንት ማለዳ አካባቢ የእስልምና ኃይማኖት ተከታይ በሚያዘጋጀው የሰርግ ሥነ ሥርዓት ላይ ከማተሚያ ቤቶች በመጣ ወረቀት እና ማስጌጫ ዳሱን የማስዋብ ሥራ እየተከናወነ እያለ ነው የድርጊቱ መነሻ የተከሰተው ብለዋል ሼህ ሙሃመድ፡፡

ከማስዋቢያው ጋር አብሮ የመጣ #የማርያም ስዕል ከሌሎች ማስዋቢያ ቁርጥራጮች ጋር ወድቆ መገኘቱን ነው የጸቡ መነሻ መሆኑን ያስረዱት፡፡ ጉዳዩ እንደተፈጸመ ስዕሉን ማን እንዳመጣው ስላልታወቀ የሁለቱም ኃይማኖቶች አማኞች በተገኙ ስዕሉ ተነስቶ ጉዳዩም አሳፋሪ እንደሆነ ተነግሮ ሁኔታው ተረጋግቶ ነበር፡፡

‹‹ከቀኑ 10፡00 አካባቢ ግን ይህን ምክንያት በማድረግ ሁለት መስጊዶች #ተቃጥለዋል፤ ሌላ ሶስተኛ መስጊድ ላይም #ድብደባ ተፈጽሟል፤ ሱቆችም ዘርፈዋል›› ነው ያሉት ሼህ ሙሃመድ፡፡

ድርጊቱ #የክርስትናም ሆኑ #የእስልምና አማኞችን የማይወክል ነው ሲሉም አውግዘውታል፡፡ ኢትዮጵያ #ሰላም እንዳትሆን የሚፈልጉ የፖለቲካ አራማጆች የዘሩት ጥል አልሆን ሲላቸው ወደ ሀይማኖት እየተዘዋወሩ መሆናቸውን የተናገሩት የአማራ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ጸሃፊው ‹‹ኢትዮጵውያን የሀይማኖት ልዩነት ሳይለያየን ለብዙ ዓመታት በሰላም እና በፍቅር ኖረናል፤አሁንም እንኖራለን፤የሴረኞችን ድርጊት አውግዘን በፍቅራችን እቀጥላለን ነው ያሉት፡፡››

‹‹ሀይማኖት ሀገር መገንቢያ እንጂ ሀገር ማፍረሻ አይደለም›› ያሉት ዋና ጸኃፊው በሀይማኖቶች ገብተው ኢትዮጵያን ለመበታታን የሚጣጣሩ የፖለቲካ ቅጥረኞችን ሁሉም ዜጋ ሊያወግዛቸው እንደሚገባ ነው የጠየቁት፡፡ ድርጊቱ የክርስትና ሀይማኖት ተከታዮችን እንደማይወክልም አረጋግጠዋል፡፡

ህዝቡን የሚያረጋጋ እና ድርጊቱን እነማን እንደፈጸሙት የሚለይ ቡድንም ወደ ስፍራው መሄዱን ነግረውናል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ ድርጊቱ የፖለቲከኞች እንጂ የአማኞች አለመሆኑን ተረድቶ በተለመደው ፍቅሩ እንዲቀጥልም ሼህ ሙሀመድ ሀሰን አስገንዝበዋል፡፡

via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን እሰቴ ከተማ ቀበሌ 03 ላይ ሁለት #መስጊዶች #ተቃጥለዋል፡፡ ጉዳቱ የደረሰው ጥር 26/ 2011ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 አካባቢ ነው፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ የአማራ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ጸሃፊ #ሼህ_ሙሀመድ_ሀሰን ለአብመድ እንደተናገሩት ድርጊቱ ለበርካታ ዘመናት በፍቅር የኖሩትን ህዝቦች #ለማለያየት ያለመና ሁለቱንም ወገኖች #የማይወክል መሆኑን አሥረድተዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በእስቴ ወረዳ የተቃጠሉትን #መስጊዶች
አንድ ላይ ተባብረን በጋራ #እናሰራ!

1000273509497 የሂሳብ ቁጥር [Este M/E/Yetekatelu Mesgede Yerdata][የእስቴ መ/እ/የተቃጠለው መስጊድ የእርዳታ]

#TIKVAHETHIOPIA #ቲክቫህኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia