TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ🔝

ከወርሃ ጥር ጀምሮ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአመራርና አስተዳደደር ሃላፊዎች #ሹመትን አስመልክቶ የወጣውን መመሪያ ተከትሎ የፕሬዝዳንት አፈላላጊ ኮሚቴ በመሰየም ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የፕሬዝዳንት አፈላላጊ ኮሚቴም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአመራርና አስተዳደደር ሃላፊዎችን ምርጫና ሹመት/ምደባ አስመልክቶ የወጣውን መመሪያ ቁጥር 002/2011 ተግባራዊ በማደረግ ሃላፊነቱን በብቃት ሲወጣ ቆይቷል፡፡

በምልመላ እና መረጣ ሂደት ውስጥ በመስፈርትነት የተቀመጡ የትምህርት ዝግጅት፣ የአመራር ልምድ፣ በማስተማር እና በምርምር የተገኘ ልምድን መሰረት በማድረግ ከቀረቡ አሰር ዕጩዎች ተገቢውን መስፈርት የሚያሟሉ ስምንት ተወዳዳሪዎችን ለስትራቴጂክ ዕቅድ ገለጻ ኮሚቴው በመምረጥ ለውድድር አቅርቧል፡፡

ዕጩ ተወዳዳሪዎቹም የቦርድ አመራሮች፣ የሴኔት መማክርት አባላት፣የማኔጅመንት ሃላፊዎች፣በተቋሙ ከሚገኙ ከሁሉም የአካዳሚክ ዘርፎች እና የአስተዳዳር ክፍሎች የተወጣጡ የስራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ስትራቴጂክ እቅዳቸውን ማቅረብ ችለዋል፡፡

በተሰጣቸው አስራ አምስት ደቂቃ ስትራቴጅክ ዕቅዳቸውን በማቅረብ፣ ከተሳታፊ ለሚነሳላቸው ጥያቄ ለአስራ አመስት ተጨማሪ ደቂቃ ማብራሪያ እንዲሰጡ ተደርጎ በሚስጥራዊ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ዕጩ #ተወዳዳሪዎች ድምጽ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

በምርጫው ሂደት ከተሳተፉ ስምንት ዕጩዎች አምስቱ ተለይተው ለቀጣዩ ሂደት ለዩኒቨርሲቲው ቦርድ የቀረቡ ሲሆን፤መስፈርቱን በማሟላት ከአንድ እስከ አምስት የወጡ ጩዎች ይፋ ተደርገዋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

1. ዶ/ር ታከለ ታደሰ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) 88.33 በማምጣት 1ኛ
2. ዶ/ር አብርሃም አላኖ(ተባባሪ ፕሮፌሰር) 77.7 በማምጣት 2ኛ
3. ዶ/ር ሰለሞን ለማ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) 72.94 በማምጣት 3ኛ
4. ዶ/ር ወንድሙ ወልዴ( ረዳት ፕሮፌሰር) 70.37 በማምጣት 4ኛ
5. ዶ/ር መስፍን ቢቢሶ(ተባባሪ ፕሮፌሰር) 66.78 በማምጣት 5ኛ ደረጃን የያዙ ሲሆን በአሰራሩ መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአመራርና አስተዳደደር #ሃላፊዎች ሹመትን አስመልክቶ የወጣውን መመሪያ በሚደነግገው መሰረት #የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ከሚቀርቡለት አምስት ዕጩዎች ሶስቱን ለይቶ ለትምህርት ሚኒስቴር እንሚልክ ተጠቁሟል፡፡

የውድድር ሂደቱ ፍጹም #ሠላማዊ እንደነበር እና መመሪያና ደንቡ በሚፈቅደው ልክ ግልጽ አሰራርን ተከትሎ ተግባራዊ መደረጉን የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር #ቶላ_በሪሶ ገልጸዋል ሲል የዘገበው የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚኒዩኬሽንና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia