TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" Galatoomaa Tour "

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ እና የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ ወደ በሰኔ እና ሃምሌ ወር 2022 ወደ #ሰሜን_አሜሪካ እና #አውሮፓ እንደሚጓዙ ታውቋል።

አመራሮቹ ጉዟቸውን " Galatoomaa Tour " በሚል የሚያደርጉ ሲሆን በተለያዩ ከተሞች ከደጋፊዎቻቸው ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ጉዞውን በተመለከተ እስካሁን በሁለቱ ወራት የሚያዳርሷቸውን ከተሞች እና ቀናት ይፋ ከመሆን በዘለለ ለጊዜው በዝርዝር ይፋ የተደረገ መረጃ የለም።

@tikvahethiopia
#ዓለምአቀፍ

የጣሊያኗ " ላምፔዱሳ " ደሴት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች።

አዋጁን ያወጀችው ባለፉት ሁለት ቀናት ከአፍሪካ የተነሱ ወደ 8,000 የሚጠጉ ስደተኞች ወደ ደሴቷ መድረሳቸውን ተከትሎ ነው።

ስድተኞች ከተለያዩ አፍሪካ ሀገራት ወደ ጣልያን እየገቡ የሚገኙት በጀልባ ለህይወታቸው እጅግ አስጊ በሆነ መንገድ ተጉዘው ነው ተብሏል።

አንድ ከጊኒ ተነስቶ ጣልያን የገባ ስደተኛ ፤ በሕይወት ተርፎ ጣልያን በመግባቱ ዕድለኛ እንደሆነ ተናግሯል።

ሀገሪቱ አሁን እየገቡ ያሉትን ስደተኞች ወደ ሌሎች የመቀበያ ቦታዎች ለማዘዋወር እየሰራች ነው ተብሏል።

የጣልያን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የትራንስፖርት ሚኒስትር ማትዮ ሳልቪኒ ፤  በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ስደተኞች ጣልያን መድረሳቸውን " የጦርነት አነይት ድርጊትን " ይወክላል ብለዋል።

ሚኒስትሩ " ጣሊያንን ለማተራመስ ሆን ተብሎ የተነደፈ ስልት መሆኑን እርግጠኛ ነኝ " ያሉ ሲሆን ከዚህ ሴራ ጀርባ ማን እንዳለ ለመግለፅ አልወደዱም።

" ከዚህ በስተጀርባ አንድ እቅድ እንዳለ እርግጠኛ ነኝ " ያሉት ሚኒስትሩ " ከ100 በላይ ጀልባዎች በጥቂት ሰአታት ውስጥ መድረሳቸው ድንገተኛ ሳይሆን የተደራጀ የጦርነት አይነት ድርጊት ነው። " ብለዋል።

" ይህ የሚያመጣው ተፅእኖ በላምፔዱሳ ላይ  ብቻ የሚያበቃ አይደለም ፤ ወደ ሮም፣ ሚላን፣ ቱሪን፣ ኔፕልስ፣ ፓሌርሞ ስለሚሄዱ አሳዛኝ መዘዞችን ያስከትላል። " ሲሉ ተናግረዋል።

ጣልያን ከፍተኛ የስደተኞችን ቁጥር የምታስተናግድ አውሮፓዊት ሀገር ስትሆን በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየው ያለው ነገር ውጥረት መፍጠሩ ተገልጿል።

በላምፔዱሳ ያለው ከመደበኛ በላይ ሁኔታ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ አስገድዷል።

ባለፉት 2 ቀናት ብቻ 8,000 ከአፍሪካ የተነሱ ስደተኞችን የቀበለችው የጣልያኗ ደሴት ላምፔዱሳ አጠቃላይ የነዋሪዎቿ ብዛት 6000 ብቻ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ።

በሌላ በኩል ፤ የጀርመን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በጣሊያን በኩል ወደ #አውሮፓ የገቡ አዲስ ስደተኞችን ለጊዜው መቀበል እንዳቆመ አስታውቋል።

ጀርመን እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው ጣልያን ባአውሮፓ ህብረት በኩል በስደተኞች ላይ የተደረሰውን ስምምነት ለማክበር ፈቃደኛ ባለመሆኗ ነው ተብሏል።

የጀርመን መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት " ከፍተኛ የስደተኞች ጫና አለ " በሚል ምክንያት ጀርመን ከጣሊያን የሚገቡ አዲስ ስደተኞችን ላልተወሰነ ጊዜ መቀበል አቋርጣለች።

ፈረንሳይ በበኩሏ ወደ ግዛቷ ለመሻገር የሚሞክሩ ስደተኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ ከጣሊያን ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ የሚገኙ የፖሊስ እና የጦር ሃይሎች ጥበቃን በከፍተኛ ሁኔታ እንደምታጠናክር ይፋ አድርጋለች።

ቪድዮ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያዎች የተገኘ

@tikvahethiopia
#IOM

" በቅርብ ከደርሱት #አስከፊ አደጋዎች አንዱ ነው " - የተመድ የስደተኞች ድርጅት

ስደተኞችን ይዞ ሲጓዝ የነበረ ጀልባ በሊቢያ ባሕር ዳርቻ ተገልብጦ፣ ሕፃናትና ሴቶችን ጨምሮ ከ60 ሰዎች በላይ መሞታቸውን የተመድ የስደተኞች ድርጅት አስታውቋል።

ቅዳሜ የደረሰው አደጋ፣ ወደ #አውሮፓ ለመሻገር በሚሹ ስደተኞች ላይ በሜዲትሬንያን ባሕር ላይ በቅርቡ ከደርሱት አስከፊ አደጋዎች አንዱ ነው ተብሏል።

የተመድ ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) እንዳለው፣ 86 ሰዎችን ይዛ ስትጓዝ የነበረው ጀልባ፣ ከፍተኛ ማዕበል ገጥሟት በሊቢያ ምዕራባዊ ባሕር ዳርቻ በምትገኘው " ዙዋካ " ከተሰኘች ከተማ አቅራቢያ ስትገለበጥ 61 ሰዎች #ሰምጠዋል

ድርርቱ ማዕከላዊው የሜዲትሬንያን ባሕር፣ ለፍልሰተኞች አደገኛ የጉዞ መሥመር መሆኑ ቀጥሏል ብሏል።

#ሊቢያ በጦርነት በመታመስ ላይ ያለች አገር ብትሆንም፣ ከአፍሪካ እና ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ #ሁከትን እና #ድህነት በመሸሽ ወደ አውሮፓ መሻገር ለሚፈልጉ ስደተኞች ተመራጭ መተላለፊያ ሆናለች፡፡

የስደተኞች ድርጅቱ እንደሚለው፣ በመጠናቀቅ ላይ ባለው የፈርንጆች 2023 ብቻ ከ2 ሺሕ 500 በላይ ፍልሰተኞች ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሲሞክሩ በባሕር ላይ #ሕይወታቸውን_አጥተዋል

መረጃው የቪኦኤ ነው።

@tikvahethiopia
#አውሮፓ

የአውሮፓ ፓርላማ የህብረቱን #የስደተኞች እና #የጥገኝነት ደንቦችን የሚያጠናክር ትልቅ ማሻሻያ አጽድቋል።

የአውሮፓ ህብረት የጥገኝነትና ፍልሰት ስምምነት ከ2015 ጀምሮ ሲመከርበት የቆየ ሲሆን በ2 ዓመት ውስጥ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።

አዲሱ ሕግ ምን ይዟል ?

➡️ የጥገኝነት ሂደት ጥያቄ #ያፋጥናል ፤ መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ #ያስገድዳል

➡️ የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት የጥገኝነት ጠያቂዎችን ኃላፊነት እንዲጋሩ ያደርጋል።

➡️ የአውሮፓ ህብረት 27 አባል አገራት በሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ከጣሊያን፣ ግሪክ እና ስፔን ካሉ " #የድንበር " አገራት እንዲወስዱ ወይም በምትኩ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያቀርቡ ያደርጋል።

➡️ ዝቅተኛ ተቀባይነት የማግኘት እድል ያላቸው የጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ አውሮፓ ህብረት ግዛት ሳያስገቡ ጉዳያቸው በፍጥነት መታየት አለበት ይላል።

➡️ የጥገኝነት ጥያቄዎች ቢበዛ በ12 ሳምንታት ውስጥ እንዲያልቁ ይላል።

➡️ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገባቸው በ12 ሳምንታት ጊዜ ውስጥ #በግዳጅ ወደ አገራቸው መመለስ አለባቸው  ይላል።

➡️ ስደተኞች ከመግባታቸው በፊት ባሉ በ7 ቀናት ውስጥ ጠንከር ያለ የማጣራት ሂደት ይደረግላቸዋል። የጤና እና የደህንነት ፍተሻዎችን ይጨምራል።

➡️ ከ6 ዓመት እና ከዛ በላይ ለሆኑ ማናቸውም ስደተኞች የባዮሜትሪክ መረጃ ይሰበሰባል። ስደተኞች ቁጥር በአጋጣሚ ካሻቀበም ምላሽ የሚሰጥበት አሠራር ተዘርግቷል።

ምንም እንኳን አንዳንድ የአውሮፓ ህብረት አገራት የተወሰኑ የስምምነቱን ክፍሎችን ቢቃወሙም በሚያዝያ ወር መጨረሻ በሚደረግ ድምጽ አሰጣጥ የአብዛኛውን ይሁኝታ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

ባለፈው አመት 380 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች የአውሮፓ ህብረትን ድንበር በህገ ወጥ መንገድ አቋርጠዋል። ይህም እ.አ.አ ከ 2016 ወዲህ ከፍተኛው ቁጥር ነው።

ስለ ሕጉ ምን ተባለ ?

#ጀርመን፦ የጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስ “ ታሪካዊና አስፈላጊ እርምጃ ” ብለውታል።

#የአውሮፓ_ፓርላማ፦ የፓርላማው ፕሬዝዳንት ሮቤታ ሜሶላ “ በአብሮነት እና በኃላፊነት መካከል ያለውን ሚዛን ጠብቋል ሁሉንም ነገር በአንድ ጀምበር ባይፈታም ግን 10 ግዙፍ እርምጃ የተጓዘ ነው " ብለዋል።

#ሀንጋሪ ፦ ምንም አይነት የስደት ስምምነት ቢደረስ መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞችን አልወስድም ብላለች።

#ፖላንድ ፦ የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶናልድ ቱስክ የተወሰኑ ጥገኝነት ጠያቂዎችን መውሰድ አልያም ለድንበር አገራት ገንዘብ መክፈል የሚለውን ሃሳብ " ተቀባይነት የሌለው " ሲሉ ውድቅ አድርገዋል።

#ስሎቫንያ፦ “ ልንሰራበት የምንችለው ስምምነት ነው ” ስትል ደግፋለች።

#ቤልጂየም፦ “ ፍፁም አይደለም (ሕጉን) ግን እንደግፈዋልን ” ስትል አሳውቃለች።

#ፈረንሳይ ፦ ፕ/ት ኢማኑኤል ማክሮን ድጋፍ ሰጥተዋል። የፈረንሣዩ ቀኝ አክራሪ ናሽናል ራሊ አባል ጆርዳን ባርዴላ ስምምነቱ “ #አስፈሪ ” ነው ሲሉ ተቃውመዋል።

#አምነስቲ_ኢንተርናሽናል ፦ ስምምነቱ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ “ከፍተኛ ስቃይ” የሚመራ ነው ሲል አስጠንቅቋል።

ከመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚነሳው አንዱ ተቃውሞ ዝቅተኛ ተቀባይነት የሚኖራቸው #ጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳያቸው በድንበር #መግቢያዎች ላይ ወይም #በማቆያ_ስፍራዎች እንዲስተናገዱ በማድረግ ፍትሃዊ ዕድል የማግኘት ተስፋቸውን ያመነምነዋል የሚል ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመረጃው ምንጭ ቢቢሲ መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" 480 ስደተኞች #በሊቢያ የባህር ጠረፍ ላይ ተይዘዋል " - IOM ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 480 ስደተኞች በሊቢያ የባህር ጠረፍ ላይ መያዛቸው ተነግሯል። የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት/IOM ሰኞ'ለት ባወጣው መግለጫ 480 ስደተኞች በባህር ላይ ጠባቂዎች መያዛቸውን አስታውቋል። ድርጅቱ "ከመጋቢት 24 እስከ 30,2024 ውስጥ 480 ስደተኞች ተይዘው ወደ ሊቢያ ተመልሰዋል " ነው ያለው። ከተያዙት…
#ሊቢያ #ግሪክ

እንደ ጣሊያን የባሕር ጠረፍ ጥበቃ መረጃ ፥ ባለፈው ሳምንት የሜዲትሬንያን ባሕርን አቋርጠው ወደ #አውሮፓ ለመሻገር በመሞከር ላይ የነበሩ ፍልስተኞች ጀልባቸው ተገልብጦ 1 ህጻንን ጨምሮ 9 ሰዎች ሞተው አስክሬናቸው ተገኝቷል።

15 የሚሆኑ ፍልሰተኞች የደረሱበት አይታወቅም። 22 ሰዎችን ደግሞ መታደግ ተችሏል።

ከላምፔዱሳ ደሴት 50 ኪ.ሜ. ላይ ማዕበል በማየሉ ነው አደጋው የደረሰው። ላምፔዱሳ ወደ አውሮፓ ለመሻገር ለሚሞክሩ ፍልሰተኞች የመጀመሪያ ማረፊያ ነች፡፡

በሌላ በኩል ፤ ባለፈው ሳምንት ግሪክ የ3 ታዳጊዎችን አስከሬን ስታገኝ ፤ 19 ፍልሰተኞችን ደግሞ ታድጋለች።

ፍልሰተኞቹ ይጓዙበት የነበረው ጀልባ ከቋጥኝ ጋራ በመጋጨቱ አደጋው ሊደርስ የቻለው።

ግሪክ ከአፍሪካ፣ እስያ እና መካከለኛው ምሥራቅ ወደ አውሮፓ ለመሻገር ለሚሹ ፍልሰተኞች አማራጭ ናት።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia