TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አክሱም #Axum

በጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር የተመራ ልዑካን ቡድን #የአክሱም_ሀውልትን ጎበኘ። ለስራ ጉብኝት ኢትዮጵያ የሚገኘው በጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒትሯ አማንኤላ የተመራው ቡድን የአክሱም ሀውልት ጎብኝቷል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት በቅርሱ ላይ እየታየ ያለውን ችግር በባለሞያዎቹም ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

የልዑካን ቡድን አባላቱ ቅርሱ የተደቀነበትን ችግር በአስቸኳይ ለመንግስታቸው በማሳወቅ ቅርሱ ጥገና የሚደረግበትን መንገድ እናመቻቻለን ብለዋል፡፡ በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ዉስጥም ባለሞያዎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚላኩም ተናግረዋል።

ልዑካን ቡድኑ በቅርሱ በአካል የተመለከቱትን ችግር ለመንግስታቸው አቅርበው ምላሽ እንደሚያገኙ እምነት እንዳለቸው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስተር የባህል ዘርፍ ሚኒትር ዴኤታ ክብርት ቡዝነሽ መሰረት ተናግረዋል።

ቅርሱ በዋናነት የከርስ ምድርና የገፀ ምድር ውሃ መጠን መጨመር ምክንያት በሀውልቱ ስር ያለውን አፈር የመሸርሸር አደጋ በማጋጠሙ ሀውልቱ ላይ የመዝመም አደጋ እንዲከሰት አድርጓል ተብሏል፡፡

ምንጭ፡- የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አክሱም

በአክሱም ከተማ ከነሀሴ 24 ቀን ጀምሮ የሚከበረውን የዓይኒዋሪ/አሸንዳ በዓል ምክንያት በማድረግ ባዛርና ዓውደርእይ ዛሬ ተከፈተ። በትግራይ ክልል የአሸንዳ በዓል በየዓመቱ ከነሀሴ 16 ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት እንደሚከበረው ሁሉ የዓይኒዋሪ በዓል ደግሞ ከነሀሴ 24 ቀን ጀምሮ በአክሱምና አካባቢው በተመሳሳይ መልኩ ይከበራል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አክሱም

በአክሱም ከተማ በአንድ ነጋዴ ቤት በሕገ ወጥ መንገድ የተደበቀ 250 ጄሪካን የምግብ ዘይት በቁጥጥር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ። በአክሱም ከተማ በአንድ ነጋዴ ቤት በሕገ ወጥ መንገድ የተደበቀ 250 ጀሪካን  የምግብ ዘይት በቁጥጥር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ። የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ኪሮስ አየለ እንዳሉት ግለሰቡና ዘይቱ የተያዘው ጄሪካኖች በቁጥጥር ሥር የዋሉት በኅብረተሰብ ጥቆማ ነው።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አክሱም

የትግራይ ክልል የንግድ፣ ኢንዱስቱሪና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አብርሃም ተከስተ በዛሬው የሆቴል በምረቃ ወቅት የተናገሩት፦

"እያደገ የመጣውን ኢንቨስትመንት ፍሰት ለማስተናገድ የሚያስችል የአሰራርና አደረጃጀት ሪፎርም እየተከሄደ ነው። አለም አቀፍ ደረጃቸውን  የጠበቁ ሆቴሎች መከፈት ለቱሪዝም ፍሰትና እድገት የላቀ አስተዋጽኦ አላቸው። በአክሱም ከተማ ዛሬ የተመረቀው ሆቴል ለክልሉ ብሎም ለሀገሪቱ ቱሪዝም ፍሰት መጨመርና እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ ይኖረዋል።"

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#መቐለ #ራያ #አክሱም #ዓዲግራት

ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ስድስት አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ በማቅናት ምልከታ ሊያደርግ ነው፡፡

በግጭቱ ምክንያት ሥራ ያቋረጡትን አክሱም፣ ራያ፣ አዲግራት እና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ አገልግሎት ለመመለስ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።

እስካሁን ባለው ሁኔታ አክሱም እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ዳግም ወደ አገልግሎት በሚመለሱበት ሁኔታ ላይ ንግግር መጀመሩን በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደር እና መሰረተ ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለፋና ተናግረዋል።

በቀጣይም ከመቐለ እና አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ግንኙነት እንደሚጀመር ኃላፊው አመላክተዋል፡፡

በአክሱም ከተማ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ተከትሎ፤ ስድስት አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ከሰኞ ጀምሮ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ዋናውን ግቢ ጨምሮ አድዋ እና ሽረ ግቢዎችን በስፍራው በመገኘት ምልከታ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ቡድኑ ተቋማቱ በሰው ኃይል፣ በመሰረተ ልማት፣ በቤተ ሙከራ፣ በኔትወርክ፣ በመኝታና መማሪያ ክፍሎች፣ በማስተማሪያ ሆስፒታል፣ በቤተ መጻሕፍት እና ሌሎች አገልግሎቶች ዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሥራውን ለማስጀመር የሚያስችለውን ሁኔታ ይመለከታል፡፡ #FBC

@tikvahuniversity
#አክሱም

የአክሱም ህዳር ፅዮን በዓልና የቱሪስት እንቅስቃሴ ምን ይመስላል ? 

አክሱም ከተማ ህዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም አመታዊ የህዳር ፅዮን በዓለ ንግስ ታከብራለች።

አክሱምና ዙሪያዋ ለአገር ውስጥና ውጭ  ጎብኚዎች የሚማርኩ በርካታ ቅርሶች የሚገኙባት በኢትዮጵያ ካሉ ታላላቅ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች አንዷ ነች።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ከአውዳሚው ጦርነት በኃላ የአክሱምና ዙሪያዋ የቱሪስት እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስል ለመታዘብ ቦታው ድረስ ተጉዞ ነበር።

ከቱሪስት እንቅስቃሴ አኳያ የሚመለከታቸው አካላት አነጋግሮ እንዲሁም የህዳር ፅዮን በዓለ ንግስ ቀድመ ዝግጅት ምን እንደሚመስል ተከታትሏል።
 
አቶ ኪዲ ተጠምቀ በአክሱም ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት የቱሪስት ማእከል አስተባባሪ ናቸው።

በትግራይ ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 24/2015 ዓ.ም ለሶስት አመታት የተካሄደው ደም አፋሳሽ ጦርነት በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መቆሙ ተከትሎ ወደ አክሱም የሚደረገው የአገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች ፍሰት መጀመሩ መልካም ቢሆንም ከጦርነቱ በፊት ከነበረው የጎብኚዎች ቁጥር  ጋር ሲነፀፀር እጅግ አነስተኛ ነው ብለዋል።

ከሰላም ስምምነቱ በኃላ በአንድ አመት ውስጥ ፦ የፊሊፕንስ  ፣ የቻይና ፣ የኬንያ፣ የጣልያን ፣ የአሜሪካ ፣ የካናዳ ፣ የፈረንሳይ ፣ የዩጋንዳ፣ የደቡብ አሜሪካ፣ የናምቢያ ፣ የአውስትራሊያ ፣የቤሌጅም፣ የሰፔን ፣ የጀርመን ፣ የፓኪስታን ፣ የኮሪያ ፣ የቼክ ሪፐብሊክ ፣ የሃንጋሪ ፣ የደቡብ አፍሪካ ፣ የህንድ ፣ የፓላንድ ፣ የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው 200 የውጭ ዜጎች አክሱም ጎብኝተዋል።

ከጦርነቱ በፊት አክሱም የተጠቀሰው ያህል ቁጥር ያለው ቱሪስት በአንድ ቀን ውስጥ ታስተናግድ ነበር ይላሉ አቶ ኪዱ ተጠምቀ።  

በተጨማሪ፦

- በጦርነቱ ምክንያት ውድመትና ዝርፍያ ደርሶባቸው የነበረው ደረጃቸው የጠበቁ ሆቴሎች እድሳት ተደርጎላቸው አገለግሎት እየሰጡ ነው።

- ከአክሱም በ20 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው ታሪካዊቷ የዓድዋ ከተማ የሚገኙ ሆቴሎችም አገልግሎት እየሰጡ ነው።

- ለጉብኝት የሚመጡት ቱሪስቶች የማረፍያ እጥረት አይገጥማቸውም።

አቶ ኪዱ ፥ የፕሪቶሪያው ስምምነት ተከትሎ አንድ አመት የሞላው ተነፃፃሪ ሰላም በክልሉ እንዳለ ፣ የአክሱም አውሮፕላን ማረፍያ አገልግሎት ባይጀምርም የሽረ አውሮፕላን ማረፍያ ከአክሱም በ60 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚገኝ መሆኑ ከሽረ ወደ አክሱም በመኪና የሚያጓጓዝ ደረጃው የጠበቀ የአስፋልት መንገድ መኖሩ ፣ በአክሱም ከተማ ለጎብኚዎች የሚያሰጋ የፀጥታ ስጋት እንደሌለ ሚድያዎች እንዲሁም የፌደራል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መ/ቤት በተለያዩ የውጭ ቋንቋዎች መረጃ በተከታታይ ያለማሰራጨታቸው ለቱሪስቶች ቁጥር ማነስ አስተዋፅኦ አለው ያሉ ሲሆን ይህ እጥረት እንዲታረም አሳስበዋል።

አክሱም የፀጥታ ስጋት የሌለባት ደህንነቷ የተጠበቀና በበቂ ሁኔታ እንግዶችን እያስተናገደችን መሆኗን በማወቅ ቱሪስቶች / ምእመናን ወደ አክሱ። በልበ ሙሉነት እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል።

አንድም በመኪና ካልሆነም ከአዲስ አበባ በአውሮፕላን ወደ ሽረ በመምጣት ከሽረ አውሮፕላን ማረፍያ እስከ አክሱም 60 ኪሎ ሜትር ርቀት በመሆኑ ደረጃውን በጠበቀው የአስፋልት መንገድ በመኪና ተጉዞ አክሱም መግባት ይቻላል።

መረጀው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ ታጋቹ ከ3 ወር መሰወር በኃላ የማስለቀቂያ ክፍያ ተጠየቀባቸው።  "አጋቾች ነን" ባዮች የጠየቁት ገንዘብ በ1 ሳምንት ጊዜ ካልተከፈላቸው ታጋቹን እንደሚገድሉት እንደዛቱ የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። እገታው እንዴት እና መቼ ተፈፀመ ?  የሰዎች እገታ ከህፃናት አልፎ እድሜያቸው በገፉት ላይም በመቀጠል በህብረተሰቡ ውስጥ ቀውስን ማቀጣጠል መቀጠሉ እየተገለፀ ይገኛል። ታጋቹ…
#Update

ታግታ ከተወሰደች በኃላ ለማስለቀቂያ 3 ሚሊዮን ብር የተጠየቀባት ታጋዲዋ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ታግታ ከተወሰደች 20 ቀናት ሆኗታል።

ቤተሰቦቿ " ልጃችንን አፋልጉን " ሲሉ በፈጣሪ ስም ተማጽነዋል። መላው ኢትዮጵያ ህዝብ እና የፀጥታ ኃይል ልጃቸውን እንዲፈልግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የታዳጊ ተማሪ ማህሌት ቤተሰቦች ከትግራይ ዓድዋ ከተማ ያስተላለፉት የአፋልጉን የተማፅኖ ጥሪ ምን ይላል ?

የማህሌት ተኽላይ ቤተሰቦች ፦

" ታዳጊ ልጃችን ተማሪ ማህሌት ተኽላይ መጋቢት 10/2016 ዓ.ም ከ 11:00 ሰዓት በኃላ ወደ ቋንቋ ትምህርት ቤት በመሄድ ሳለች በትግራይ ዓድዋ ከተማ ዓዲ ማሕለኻ ተብሎ ከሚጠራ ልዩ ቦታ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታፍና ተወስዳለች።

አጋቾቹ በወሰዱዋት ቀን በራስዋ ሞባይል ስልክ ወደኛ በመወደወል ለማስለቀቅያ 3 ሚሊዮን ብር እንድንከፍላቸው ጠይቀውናል።  ከዛ በኃላ ግን በደውሉበት የልጃችን የሞባይል ቁጥር ብንደውልም አናገኛቸውም፤ በሌላ የሞባይል ቁጥር ደውለውም ያሉን ነገር የለም።

ስለሆነም እኛ የታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ወላጆች በከፍተኛ ጭንቅና ሃዘን ውስጥ እንገኛለን። ስለዚህ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብና የፀጥታ አካላት የአፋልጉን የተማፅኖ ጥሪ እናቀርባለን። "

ማህሌት ተኽላይ የሚመለከት ማንኛውም አይነት መረጃ ለመስጠት ፦
+251938819844 ሙሴ ተኽላይ
+251992733943 ደጀን ተኽላይ 
+251935036100/
+251962529287 ሚልዮን ተኽላይ
በሚሉ የሞባይል ቁጥሮች እንድትጠቀሙ በትህትና እንጠይቃለን። "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሁኔታውን እንዲያብራሩ የታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ቤተሰቦችን ጠይቆ ፥ " የዓድዋ ፓሊስ እኛን መልሶ ምን አዲስ ነገር አለ ብሎ ይጠይቀናል ? " ሲሉ መልሰዋል።

የመቐለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ #ዓድዋ እና #አክሱም ያደረገው ጉዞ በፓሊስ አመራሮች ስብሰባ ምክንያት አልተሳካም።

#TikvahFamilyMekelle
                                            
@tikvahethiopia