TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የእንግሊዝ የልማት ተራድኦ ድርጅት (DFID) የኢትዮጵያ ተወካይ ክርስቲያን ሮግ የሶማሌ ክልልን ጎብኝተዋል። መንግስትቸው ለክልሉ ልዩ ፖሊስ #ድጋፍ አድርጓል መባሉንም #አስተባብለዋል። ከክልሉ ፕሬዝዳንት #ሙስጠፋ_ዑመር ጋርም መልካም ውይይት ማድረጋቸውን ሀላፊው ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጨማሪ ባንኮች ተዘረፉ‼️

በኦሮሚያ ክልል ወለጋ አካባቢ ተጨማሪ ስድስት ባንኮች በታጣቂዎች በትላንትናው ዕለት መዘረፋቸውን አንድ የአካባቢው ባለስልጣን ለDW ገለጹ። ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ በሁለት የወለጋ ዞኖች የተዘረፉት ባንኮች 17 መድረሱን የየአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል።

የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታመነ ኃይሉ ዛሬ ለDW እንደተናገሩት በአካባቢያቸው ባሉ ስድስት የመንግስት እና የግል ባንኮች ዝርፊያው የተፈጸመው ትላንት እሁድ ከቀኑ አምስት ሰዓት ጀምሮ ነው። “በትላንትናው ዕለት የባንክ ዘረፋ የተካሄደው በሃዋ ገላን ወረዳ፣ እሮብ ገበያ ላይ፣ በአንድ የንግድ ባንክ እና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ [ላይ] ነው። እዚያው ወረዳ ላይ መቻራ የምትባል ከተማ ላይ አንድ የንግድ ባንክ እና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ተዘርፈዋል። ከዚያ ደግሞ ሰዲ ጨንቃ ወረዳ ላይ በጨንቃ ከተማ አንድ የንግድ ባንክ፣ አንድ የኦሮሚያ የህብረት ስራ ባንክ ዝርፊያ ተካሂዶበታል” ብለዋል።

ተዘረፉ በተባሉት ባንኮች እስካሁን መጠኑ ያልታወቀ ገንዘብ በታጣቂዎች መወሰዱን የገለጹት የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ የየባንኮቹ ሰራተኞች በታጣቂዎች ታግተው ተወስደዋል የሚል ስጋት እንዳለም አስረድተዋል። “ ካሸሪዎች [ገንዘብ ያዥዎች] እና ስራ አስኪያጆችን ይዘው ሄደዋል ነው የሚባለው። እንግዲህ ሰዎቹን ስላላገኘን እስካሁን ምን ያህል ገንዘብ ተወሰደ የሚለውን ማወቅ አልቻልንም። ግን ደግሞ ሰዎቹን ይዘው ሄደዋል የሚል መረጃ ነው ያለን” ሲሉ አብራርተዋል።

ታጣቂዎቹ ከባንክ ዘረፋ በተጨማሪ በሁለት ወረዳዎች ያሉ የመንግስት መስሪያ ቤት ማውደማቸውን አቶ ታመነ ይናገራሉ። “በላሎ ክሌ የመንግስት መስሪያ ቤት አቃጥለዋል። በዋሃ ገላን፣ በየ ማለጊ ወረዳ ላይም የመንግስት መስሪያ ቤት የተቃጠለበት ሁኔታ ነው ያለው። እንግዲህ እነኚህ ወረዳዎች ሰራዊት የሌለበት ወረዳ ነው። ሰራዊት ከሌላ አጎራባች ቦታ እስኪደርስ ይሄን ጉዳት አድርሰው የታጠቁት ኃይሎች ከአካባቢው ተንቀሳቅሰዋል” ብለዋል።

ዘረፋ እና የንብረት ቃጠሎ በደረሳባቸው ቦታው ግጭት እንደሌለ የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ ተናግረዋል። አሁን በቦታዎቹ ላይ የጸጥታ ኃይሎች ገብተው ህዝቡን እየያረጋጉ እንደሚገኙም ገልጸዋል። በአካባቢው የመከላከያ ሰራዊት በሄሊኮፕተር ታግዞ ጥቃት ፈጽሟል የሚባለውንም #አስተባብለዋል

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሺርካ

✦ " 11 የአንድ ቤተሰብ አባላት (አያት ፣ ልጅ፣ የልጅ ልጅ ፣ የ39 ቀን ጨቅላ) ጨምሮ 17 ስዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል " - የቲክቫህ ቤተሰብ አባል

✦ " ከሟቾቹ ውስጥ ከ70 ዓመት አዛውንት እስከ 26 ቀን ህጻን ነፍሰጡር እናቶች ይገኙበታል " - ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪ (ለቪኦኤ)

✦ " ጥቃቱን ያደረሰው አሸባሪው ሸኔ ነው " - የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን (ለቪኦኤ)

✦ " እኛ ንፁሃን ላይ ጥቃት አላደረስንም " - የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ለቪኦኤ)

✦ " ባለሞያ መድበን ምርመራ ጀምረናል " - ኢሰመኮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ


በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ፤ ሺርካ ወረዳ ፤ በተፈጸመ ጥቃት ንጹሐን ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መሞታቸውን እና የዐይን እማኞችና መልክታቸውን ያደረሱ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።

አንድ #የአካባቢው ነዋሪ የቤተሰባችን አባል በላኩልን መልዕክት ፤ " ህዳር 13 /2016 በግምት ከምሽቱ 2:30 አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ እና በታጠቁ ኢ - መደበኛ ሀይሎች በሽርካ ወረዳ ሶሌ ዲገሉ ጉና እና ጢጆ ለቡ በተባሉ የገጠር ቀበሌዎች በተፈፀመ ጥቃት 11 የአንድ ቤተሰብ አባላት (አያት ፣ ልጅ፣ የልጅ ልጅ ፣ የ 39 ቀን ጨቅላ) ጨምሮ 17 ስዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ በተመሳሳይ ሰዓት በተፈፀመ በሌላኛው ጥቃት ደግሞ 11 በድምሩ 28 ሰው ሲልፍ ሁለት ህፃናት ደግሞ ቆስለው ህክምና ላይ ይገኛሉ " ሲሉ ገልጸዋል።

ቪኦኤ አማርኛ አገልግሎት ክፍል በጉዳዩ ላይ በሰራው ዘገባ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ሦስት ቀበሌዎች ሐሙስ ህዳር 13 እና ሰኞ ህዳር 17 ቀን በተፈጸመ ጥቃት #36_ሰዎች መሞታቸውን ገልጿል።

ከሟቾቹ ገሚሶቹ የሁለት ቤተሰብ አባላት መሆናቸውን በዘገባው ጠቅሷል።

ቃላቸውን የሰጡ አንድ ስሜ አይጠቀስ ያሉ ነዋሪ ፤ " ህዳር 13 ለ 14 አጥቢያ ለቡ በተባለው ቀበሌ ላይ 11 ሰው አንድ ላይ ሰብስበው እነዚህ ታጣቂዎች አንድ ላይ ረሽነዋል። ሶሌ ዲገሉ በተባለው ቀበሌ ደሞ 17 ሰው አስሩ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው ሰብስበው ረሽነዋል። እነዚህ 17ዱ በአንድ ጉድጓድ 11ቱ በአንድ ጉድጓድ ተቀብረዋል። የዚህን ሀዘን ሳንጨርስ እንደገና በሦስተኛው ቀን ለቡ በተባለው ቀበሌ የአንድ ቤተሰብ አባላት 8 ሰዎች ረሽነዋል። እነዚህም በአንድ ጉድጓድ ተቀብረዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ነዋሪው አክለው፤ " ከእነዚህ ከሟቾቹ ውስጥ ከ70 ዓመት አዛውንት እስከ 26 ቀን ህጻን ነፍሰጡር  እናቶች ይገኙበታል" ያሉ ሲሆን " የሦስቱ ቦታ ጥቃቶች በተመሳይ መልኩ ቤት እየገቡ አንድ ቦታ ያሉ ሰዎችን መረሸን ነው። ህጻን የለም አዋቂ የለም ገብተው መረሸን ነው። የአማርኛ ስም ያላቸው፣ የአማራ ስም ያላቸውና የኦርቶዶክስ እምነት አማኝ ላይ ያተኮረ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ጥቃቱን ማን እንደፈጸመ የተጠየቁት ነዋሪው " ምንም የሚታወቅ ነገር የለም የታጠቁ ኃይሎች ናቸው እከሌ ልንላቸው አንችልም። " ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል።

የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ሓላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ፣ ለጥቃቱ መንግሥት ' ሸኔ ' እያለ ከሚጠራው (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚለው ታጣቂ ቡድን) ተጠያቂ አድርገዋል።

ኃላፊው ለቪኦኤ በሰጡት ምላሽ " በሽርካ ወረዳ ሶሌ ዲገሉ፤ ጢጆ ለቡ፤ ሲላ ዋጂ አሸባሪው ሸኔ ንጹሐን ላይ ጥቃት ፈጽሟል። ከ2 ዓመት ህጻንን እስከ አቅመ ደካማ ሴቶችን ላይ አነጣጥሮ እኔ ባለኝ መረጃ የ27 ሰዎች ህይወት አልፏል " ብለዋል።

አክለውም " ይኼ አሸባሪ ቡድን ባሳለፍነው ሳምንት ቡኖ በደሌ ጨዋቃ ወረዳ ላይ በኢትዮጵያ የጸጥታ አካል በተወሰደበት እርምጃ ብዙ ኃይሉ ሙትና ቁስለጫ በመሆኑ ይሄንን ለመበቀል ብሎ በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ይሄንን ጥቃት ፈጽሟል።" ሲሉ ከሰዋል።

በመንግሥት " ኦነግ ሸኔ " የተባለውና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው የታጠቀ ኃይል ቃል አቀባይ የሆኑት ኦዳ ታርቢ ለቪኦኤ ኦሮምኛ ክፍል በሰጡት ምላሽ ውንጀላውን #አስተባብለዋል፡፡

" እኛ ኃይላችን በተባለው አከባቢ #በሰላማዊ ሰዎች ላይ የወሰደው እርምጃ፤ ያጠፋው የሰላማዊ ሰዎች ህይወትም የለም። ከህዳር 14 - 17 ድረስ በሥርዓቱ ኃይል ብዙ ሰው ተገሏል፤ ብዙ ቤትም ተቃጥሏል። ይህም በምስራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ ነው የተፈጸመው አዛውንቶችም ተገለዋል። ይህንን ለማድበስበስ ነው ጣታቸውን በእኛ ላይ የሚጠቁሙት " ሲሉ ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ሓላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ግን ይህ ኃይል የሚፈጸጸምማቸውን ጥቃት መካድ ባህሪው ነው ሲሉ ገልጸውታል።

አስተያየታቸውን የሰጡን የቲክቫህ ቤተሰቦች ፤ " እዚሁ ወረዳ ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ግድያ እንደነበረ ቢታወቅም በአካባቢው ያሉ የመንግስት ታጣቂዎች ለጉዳዩ የሰጡት ትኩረት አነስተኛ ስለነበር ይህ ሁሉ ሰው ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ተጨፍጭፈዋል። የአካባቢው ህዝብም በአካባቢው ለመኖር ዋስትና ስለሌለው አካባቢውን ለቆ ለስደት እየተዳረገ ነው፡፡" ሲሉ ተናግረዋል።

በኦሮሚያ ክልል ፤ ምሥራቅ አርሲ ዞን ፤ ሽርካ ደረሰ ስለተባለው ጥቃት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ( #ኢሰመኮ ) ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን የኮሚሽኑ የክትትልና ምርመራ ስራ ክፍል ሲኒየር ዳይሬክተር ሚዛኔ አባተ (ዶ/ር)፣ " መረጃ ደርሶናል እያየነው ነው " የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

" አሁን ላይ በዝርዝር የምናገረው ነገር የለም። ነገር ግን እኛ ጉዳዮች እንደዚህ በሚደርሱን ሰዓት ጉዳዩን የሚከታተል ባለሙያ እንመድባለን፣ በዚህም ምርመራ እናደርጋለን። ያ ነገር የተጀመረ መሆኑን ነው መናገር የምችለው " ሲሉ ገልጸውልናል።

@tikvahethiopia