TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከኮቪድ-19 ታማሚዎች ነፃ የሆነው ክልል...

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮቪድ-19 ተገኝቶባቸው በአሶሳ ከተማ ሰልጋአሉ የጤና አጠባበቅ ጣቢያ ላይቶ ማከሚያ ገብተው የህክምና ክትትልና ድጋፍ ሲደረግላቸው የነበሩ 2 ግለሰቦች ከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸው ተገልጿል።

ይህ ሪፖርት እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገኙ #በሁሉም የለይቶ ማከሚያ ቦታዎች ምንም አይነት የኮቪድ-19 ታካሚ ግለሰቦች አለመኖራቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አሳውቋል።

በክልሉ ባሉ ሁሉም የማከሚያ ቦታዎች የኮቪድ-19 ታማሚ የለም (ሁሉም ታማሚ አገግሟል) ማለት ቫይረሱ በክልሉ ውስጥ አይኖርም ማለት እንዳልሆነ በመገንዘብ የተለመደው #ጥንቃቄ እንዲደረግ ቢሮው አሳስቧል።

ባለፉት 14 ቀናት ትኩሳት ወይም ጉንፋን መሰል ምልክቶች (እንደ ሳል የጉሮሮ ህመም የመተንፈሻ አከል ችግር ወ.ዘ.ተ) የታየበት ማንኛዉም ሰዉ ያገጠመው ሰው በ6016 ነፃ ስልክ መስመር በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠይቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ዝርዝር ፦

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከዛራ የካቲት 27 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ/ም የሚቆይ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ መዘጋጀቱን አስታውቋል።

በዚሁ መሰረት የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ይፋ አድርጓል።

- ቤንዚን በሊትር 25 ብር ከ 86 ሳንቲም፥

- ኤታኖል ድብልቅ ቤንዚን በሊትር 25 ብር ከ 36 ሳንቲም፥

- ነጭ ናፍጣ በሊትር 23 ብር ከ18 ሳንቲም፥

- ኬሮሲን በሊትር 23 ብር ከ18 ሳንቲም፥

- ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 20 ብር ከ27 ሳንቲም፥

- ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 19 ብር ከ78 ሳንቲም፥

- የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 38 ብር ከ65 ሳንቲም ይሆናል ብሏል ሚኒስቴሩ።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተደረገውን የዋጋ ማስተካከያ በተመለከተ በዝርዝሩ የተካተቱ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫን ለማሳወቅ የህዝብ ማስታወቂያ ዛሬ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል።

በዚሁ መሰረት #በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች በሚገኙ ማደያዎች ተግባራዊ ይደረጋል ብሏል። #FBC

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ተመረቀ።

ማዕከሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ነው የተመረቀው።

ለኩላሊት ህመምተኞች እፎይታን ይሰጣል ተብሎ የሚጠበቀው ዛራ ለምርቃት የበቃው በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ የተሰራው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ቀድሞ #በሁሉም የመንግስት ሆስፒታሎች ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት #በአምስት_እጥፍ ያሳድገዋል ተብሏል።

የኩላሊት እጥበት ማዝእከሉ የከተማ አስተዳደሩና የአብ ሜዲካል ሴንተር በትብብር የተሰራው መሆኑ ተገልጿል።

Via AA Mayor Office

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ፦ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በላከልን መልዕክት በዛሬው ዕለት የመሰረተ ልማት መጋራት እና #በደንበኞች_መካከል_የግንኙነት_ልውውጥ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙርያ ከበርካታ ዙር ውይይቶች በኋላ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን ገልጾልናል። ውይይቶቹ በኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለሥልጣን የተመሩ መሆኑን የገለፀው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ባለሥልጣኑ ላሳየው ብቁ የአመራር ጥበብ ምስጋና…
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከምን ደረሰ ?

ሳፋሪኮ ኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ለመጀመር እያደረገ ስላለው እንቅስቃሴ እንዲሁም አሁናዊ የተቋሙን እንቅስቃሴ በተመለከተ በቀጣይ ሳምንት ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ተቋሙ ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት ፤ " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎት ሊጀምር ነው " የሚሉ፣ ቀኖች እና ሌሎች ተቋማዊ መረጃዎችን ያካተቱ ዜናዎችና መረጃዎች በማሕበራዊ ድረገጾች መውጣታቸውን እንዳስተዋለ ገልጿል።

#በያዝነው_የፈረንጆች_ዓመት ውስጥ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና #በሁሉም_የኢትዮጵያ_ክፍሎች ምርጥ የደንበኞች አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችሉትን ዝግጅቶች እያደረግ መሆኑን የገለፀው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለዚህም፦

- የኔትወርክ ግንባታ፣

- የሰው ኃብትን #በኢትዮጵያዊያን_ሠራተኞች ማደራጀት

- የጥራት ፍተሻዎችን እያደረገ እንደሚገኝ አሳውቋል።

በቀጣይ ሳምንት ስለተቋሙ እንቅስቃሴ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ እንደሚሰጥ የገለፀ ሲሆን የአገልግሎቱን መጀመረ የሚጠባበቁ ሁሉ ትክክለኛ መረጃዎችን ከተቋሙ ትክክለኛ አድራሻ ብቻ እንዲካታተሉ መልዕክቱን አስተላልፏል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
አዲስ አበባ 🛫 መቐለ !

#ከአዲስ_አበባ ወደ #መቐለ ከነገ ጀምሮ ዳግም በረራ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፥ " ተቋርጦ የነበረው ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ የአየር ትራንስፖርት በነገው ዕለት ይጀምራል " ብለዋል።

" በፌዴራል መንግስቱ እና በህወሓት መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የአቬየሽን ሰራተኞች ወደ መቐለ አቅንተው የመቐለ አየር መንገድ ለበረራ ምቹ ሁኔታ ላይ መሆኑን አረጋግጠዋል " ሲሉ አቶ መስፍን ገልፀዋል።

ነገ በሚጀምረው በረራ በቀን አንድ ጊዜ የሚካሄድ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን የደንበኞችን ፍላጎትን መሰረት በማድረግ የበረራው ቁጥሩ ከፍ ሊል የሚችልበትን ሁኔታ እንደሚፈጠርም አሳውቀዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ፤ ተቋርጦ የነበረውን የበረራ እንቅስቃሴ #በሁሉም የትግራይ ክልል የበረራ መዳረሻዎች ለማስጀመር ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም ዛሬ በሰጡት መግለጫ አንስተዋል፡፡

" ነገ የሚጀምረው በረራ (ወደ መቐለ) ከሌላው ወገኑ ጋር ግንኙነቱ ተቋርጦ የነበረውን የትግራይ ህዝብ ዳግም እንዲገናኝ ለማድረግ ትልቅ እድል የሚፈጥር " ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈ የሸቀጦችና ሌሎች ተደራሽ የመሆን እጥረት የነበረባቸውን የሰብዓዊ ድጋፎችን በበቂ ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ይህም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን ከፍ ማድረግ የሚያስችል እንቅስቃሴ መሆኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል፡፡

#የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

አዲስ አበባ ከተማ በምታስተናግደው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ምክንያት ከዛሬ ጀምሮ የሞተር ብስክሌት እና የባጃጅ እንቅስቃሴ መከልከሉ ታውቋል።

የከተማው የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ፤ " 36ኛው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባን ምክንያት በማድረግ ከዛሬ የካቲት 1/2015 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ በከተማችን ሞተር ብስክሌት እና የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) ማሽከርከር የተከለከለ መሆኑን እናሳውቃለን " ብሏል።

የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ ባጃጅ ክልከላው ከዛሬ የካቲት 1/2015 ዓ.ም ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 5/2015 ዓ.ም አመሻሽ 12:00 ሰዓት ድረስ ፀንቶ ይቆያል ተብሏል።

ሞተር ብስክሌቶች ከዛሬ የካቲት 1/2015 ዓ.ም  ጀምሮ ስበስባድ እስኪጠናቅ የካቲት 13/2015 ዓ.ም አመሻሽ 12:00 ሰዓት ድረስ ሞተር ብስክሌትን ማሽከርከር ፍጹም የተከለከሉ መሆኑ ተገልጿል።

ክልከላ የሚመለከተው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር ስራ አካላት ከሚጠቀሙባቸው ውጪ ነው ተብሏል።

ክልከላድ በአዲስ አበባ ከተማ #በሁሉም አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ባጃጆችን፣ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌቶችን በኤሌክትሪክ የሚሰሩትን ጭምር በሙሉ የሚያካትት መሆኑ ተመላክቷል።

የባጃጅ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች፣ የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች ይሄንኑ ክልከላ መሰረት በማድረግ እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ኤጀንሲው አሳስቧል።

ክልከላድን በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ ይወሰዳል ሲል ኤጀንሲው አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" የቦርዱ ውሳኔ የሰላም ሂደቱ አደጋ ውስጥ የሚከት ነው " - ህወሓት

ህወሓት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ አልቀበልም አለ።

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከቀናት በፊት ምርጫ ቦርድ ያሳለፈውን ውሳኔ እንደማይቀበለው ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

የምርጫ ቦርድን ውሳኔ " አልቀበለውም " ያለው ህወሓት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እወያይበታለሁ ብሏል።

የምርጫ ቦርድም ውሳኔውን እንደገና በማጤን የፕሪቶርያ ስምምነትና ሌሎች የፌደራል ተቋማት ያስተላለፉትን ውሳኔዎች መነሻ በማድረግ እንዲያስተካክል ጠይቋል።

ህወሓት የሰላም ስምምነቱ ባለቤት ናቸው ያላቸው የድርጅቱ አባላት፣ የትግራይ ህዝብና የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የቦርዱ ውሳኔ የሰላም ሂደቱ ኣደጋ ውስጥ የሚከት መሆኑ በመገንዘብ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

የፌደራል መንግስትም " ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የሰጠውን ውሳኔ በተጀመሩት አወንታዊ የሰላም እና የመደጋገፍ ጥረቶች ላይ ሊያሳድረው የሚችል አላስፈላጊ ጫና እንዲሁም የፌደራል መንግስቱ ህጋዊ ውሳኔዎችን እና ስምምነቶችን #በሁሉም የመንግስት ተቋማት እና አካላት እንዲከበሩ የማድረግ ኃላፊቱን ግምት ውስጥ በማስገባት የቦርዱን ውሳኔ እንደገና ታይቶ ከህወሓት ህጋዊ ሰውነት ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጥያቄዎች ያሉትን ህጋዊና ፖለቲካዊ አማራጮች ተጠቅሞ ነገሮች ቅድመ-ጦርነት ወደ ነበሩበት ሁኔታ እንዲመለሱ በሚያደርግ ቀና አካሄድ እንዲፈቱ እንዲያድረግና የፕሪቶርያ ስምምነት በተሟላ መንገድ ተግባራዊ እንዲደረግ እና የተጀመረውን የሰላም ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንዲያደርግ " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

(የህወሓት ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ትምህርት የሚጀምረው መስከረም 7 ነው " - የአ/አ ትምህርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2016 የትምህርት ዘመን ትምህርት የፊታችን ሰኞ መስከረም 7 /01/2016 ዓ.ም በሁሉም ትምህርት ተቋማት እንደሚጀምር አስታወቀ። ቢሮው ይህን ያሳወቀው የትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ/ም የትምህርት ካላንደርን ለህዝብ ካሰራጨ በኃላ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው አጭር መልዕክት ነው።…
#AddisAbaba

ነገ ሰኞ መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት ዘመኑ የመማር ማስተማር ስራ በይፋ ይጀምራል።

ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ባገኘነው መረጃ ከነገ ጀምሮ በከተማው ውስጥ በሚገኙት ሁሉም የትምህርት ተቋማት የ2016 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ስራ የሚጀምር ይሆናል።

ነገ ለሚጀምረው ትምህርት በየክፍለ ከተሞቹ የሚገኙት የትምህርት ፅህፈት ቤቶች እንዲሁም የትምህርት ተቋማት በቂ የሆነ ዝግጅት አድርገው የተማሪዎችን ለዓመቱ ትምህርት መገኘት ብቻ እየጠበቁ ይገኛሉ ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ፤ ለ2016 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ዝግጅት በከተማው ያሉ ትምህርት ቤቶችን የማደስ፣ ግብዓቶችን የማሟላት ፣ ከአጠቃላይ የትምህርት ማህበረሰቡ ጋር የመምከር ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል።

በነገው ዕለት በከተማዋ ትምህርት የሚጀምረው #በሁሉም የትምህርት ተቋማት ውስጥ ነው።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐ ግብር ሊጀምር ነው።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጪው #መስከረም_ወር ጀምሮ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐግብር እንደሚጀምር አስታውቋል።

ዩኒቨርሲቲው በቅደመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች ተመርቀው የስራ ዓለም ውስጥ ለሚገቡ ተመራቂዎች ራሱን የቻለ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ እንደሚሰጥ ገልጿል።

ፕሮግራሙ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና የገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ነው ያለው ዩኒቨርሲቲው " ይህ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጥ ነው " ብሏል።

" የፕሮግራሙ መጀመር በሥራ ገበያው ውስጥ ብቁ ሙያተኞችን ለማግኘትና የዩኒቨርሲቲውን አቅምና ብቃት ያለው ባለሙያ የማፍራት ተልዕኮ የሚያሳካ ነው " ሲል ገልጿል።

የሙያ ብቃት ማረጋገጫው #በሁሉም_ዘርፎች ላይ የሚሰጥ ሲሆን ይህ የሚመራበት አሰራር ይዘረጋል ተብሏል።

በትምህርት ስርዓት ውስጥ ያሉ #ተማሪዎችም ሆኑ በስራ ገበያ ያሉ ሰራተኞችና ምሁራን ለተማሩበት ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ወይም #ፕሮፌሽናል_ሰርትፊኬት መውሰድ እንደሚችሉ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል። #ኢዜአ

@tikvahethiopia