TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው የቢል እና ሜሊንዳጌትስ ፋውንዴሽን የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ 150 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለዓለም የጤና ድርጅት ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አለታ ወንዶ!

በትላንትናው እለት በሲዳማ ዞን አለታ ወንዶ ከተማ አስተዳደር በአለታ ወንዶ ሆስፒታል የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከያ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መስራታቸውን ገልፀውልናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅቡቲ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,430
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 494
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 156
• አጠቃላይ ያገገሙ - 73
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 591

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TIGRAY

በትግራይ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል ወደክልሉ በመኪናም ይሁን በአየር የሚገባ መንገደኛ ለ14 ቀናት ለይቶ ማቆያ የመቆየት #ግዴታ አለበት። ይህን ልናሳታውሳችሁ እንወዳለን!

በሌላ በኩል የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሃጎስ ጎደፋይ ከደቂቃዎች በፊት በሰጡን መረጃ መሰረት ዛሬ የተደረገውን 6 የላብራቶሪ ምርመራ ጨምሮ በትግራይ 105 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጓል (ከዚህ ውስጥ ሀምሳ አምስቱ /55/ #EPHI ተልኮ የተመረመረ ነው) ሁሉም #ነፃ ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AMHARA

ከአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ በተገኘው መረጃ መሰረት ትላንት በጎንደር ከተማ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ሥራ ተጀምሯል።

ከዚህ ቀደም ምረመራ የጀመረውን የባህርዳሩ እና የጎንደር የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ መሣሪያዎች በ24 ሰዓታት 1 ሺህ 440 ናሙናዎችን መመርመር የሚችሉ መሆናቸው ተሰምቷል።

በቀጣይ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ላብራቶሪዎች ደሴ፣ ደብረ ብርሃን፣ እንጅባራ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ወልዲያ እና ደብረ ታቦር ከተሞች ለማስጀመር መሣሪያዎችን የመግጠምና ባለሙያዎችን የማሰልጠን ሥራ እየተሰራ ነው።

በአማራ ክልል የቤት ለቤት የቅኝት ተግባራት የማስተማርና አጠራጣሬ ምልክት ያላቸው ሰዎችን የመለየት ሥራ በተደራጀ ቡድን እያከናወነ ይገኛል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች ፦

- በዩናይትድ ኪንግደም የሟቾች ቁጥር 13,729 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ 861 ሰዎች ሞተዋል። በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎችም ቁጥር እየጨመረ ነው፤ ባለፉት 24 ሰዓት 4,618 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 103,093 ሆኖ ተመዝግቧል።

- በስውዲን ባለፉት 24 ሰዓት 613 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ 130 ተጨማሪ ሰዎች ሞተዋል።

- አሁንም በሩሲያ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው፤ ባለፉት 24 ሰዓት 3,448 ሰዎች በቫይረት ተይዘዋል። በሌላ በኩል 34 ሰዎች ሞተዋል።

- ባለፉት 24 ሰዓት በቻይና 46 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከእነዚህ ውስጥ 34 የሚሆኑት ከሌላ ሀገር ወደ ቻይና የገቡ ናቸው።

- በስፔን ባለፉት 24 ሰዓት 551 ሰዎች ሞተዋል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 19,130 ደርሷል።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የተያዙ ሰዎች 2,115,624 ደርሷል። ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከ527,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል። ከ141,000 በላይ ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

- ሰበታ ከተማ የሚገኘው የይሔይስ አበበ የገበያ ማዕከል ለተከራዮች የ3 ወር ኪራይ ነፃ አድርጓል። በገንዘብ 600,000 ብር ይደርሳል።

- አ/አ የሚገኘው የካሳ ግራንድ ሞል ባለቤቶች በህፃቸው ላይ ተከራይተው ለሚሰሩ ነጋዴዎች፣ የካፌ ባለቤቶችና ሌሎችም የ3 ወር 50% የቤት ኪራይ ቅናሽ ማድረጋቸውን አረጋግጠውልናል።

ሌሎች ቤቶቻቸውን ለመኖሪያ ቤት ያከራዩ በርካታ ኢትዮጵያውያን የቤት ኪራይ ክፍያን ነፃ እያደረጉ እንደሆነ እየገለፁልን ነው። በምንችለው አቅም የደረሱን እናቀርባለን። ሁሉንም በአንድ ጊዜ ማቅረብ ስለማንችል ይቅርታ እንጠይቃለን!

ሁላችሁንም ለበጎ ስራችሁ እናመሰግናለን!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ 'ለወገን ደራሽ ወገን ነዉ!' በሚል ፤ የኮሮና በሽታ (COVID-19) ከሚያስከትለዉ የጤና ችግር ባለፈ ፤ በሚያመጣዉ የኢኮኖሚ ችግር ፤ አቅመ ደካሞችና አረጋዊያን ይበልጥ እንዳይጎዱ በማሰብ በሀድያ ዞን አስተዳደር የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች መምሪያ በኩል ለተለዩ የእቅም ዉስንነት ላለባቸዉ ከ1,000 በላይ ወገኖች እገዛ አድርጓል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የተላከ!

የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ከአጋር አካላት በድጋፍ ያገኘውን 16 ሚሊየን ብር የሚሆን የምግብ፣ አልባሳት እና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ለተለያዩ ተቋማትና በችግር ውስጥ ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፍ የተደረገላቸው ተቋማት AWSAD ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ማገገሚያ ማእከል ፤ ሙዳይ የበጎ አድራጎት ማህበር፤ ወንጀል ነክ ነገር ውስጥ ገብተው የተገኙ ህጻናት ማቆያና ተሀድሶ ተቋም እንዲሁም ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከላየንስ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ እና በስሩ ከሚገኘው አዱሊጣ ኮንፈረንስና ስፓ ሪዞርት በተላከልን መልዕክት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት እየተደረገ ለሚገኘው ጥረት 3,000,000 ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀውልናል።

- ላንየስን ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለኮቪድ-19 ብሄራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ 2,000,000 ብር

- አዱሊጣ ኮንፈረንስና ስፓ ሪዞርት ለኦሮሚያ ክልል የኮቪድ-19 ድጋፍ አሰበባሳቢ 1,000,000 ብር

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ያለበቂ መከላከያ 300 ሺህ አፍሪካውያን በኮሮና ምክንያት ህይወታቸውን እንደሚያጡ ይገመታል ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ አስታወቀ።

የኮሮና ቫይረስ በአፍሪካውያን ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት በገመመገመበት በዚህ መግለጫ ከሰው ህይወት በተጨማሪ የአህጉሪቷን ምጣኔ ኃብት እያሽመደመደው እንደሆነም አስፍሯል።

በዚህ አመት የአህጉሪቱ ምጣኔ ሃብት በ3.2 በመቶ ያድጋል ተብሎ የተገመተ ቢሆንም ቫይረሱ ባደረሰው ጫና ምክንያት ምናልባት 1.8 በመቶ ሊያድግ ይችላል ብሏል። ይህም ሁኔታ 27 ሚሊዮን ህዝብን ለረሃብ እንደሚያጋልጥ የኮሚሽኑ መግለጫ ጠቁሟል።

ምንጭ ፦ BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTsionFirew

በአሜሪካ 'ኒውዮርክ ሆስፒታል' የድንገተኛ ክፍል ሃኪም፣ የሕብረተሰብ ጤና ባለሞያ ፣በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰርና ጤና ሚኒስተር አማካሪ የሆኑት ዶክተር ጽዮን ፍሬው ከሰሞኑን የኮሮና ቫይረስ ይዟቸው እንዳገገሙ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል።

ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት ከሰሞኑን ዶክተር ፅዮን ፍሬውን በተለያዩ ጉዳዮች አነጋግሮ ነበር። ዶክተር ፅዮን ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተከታዩን መልዕክት ለኢትዮጵያ ህዝብ አስተላልፈዋል ፦

በሽታው ስር ሳይሰድ በፊት መንግሥት እና የሚመለከታቸው ተቋሞች (ጤና ሚንስቴር እና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት) የሚያወጧቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች መከተል ይገባል።

ሰው አላግባብ መደንገጥ ሳይሆን የሚነገረውን ማድረግ አለበት፤ በማኅበራዊም ይሁን በማንኛውም ጉዳይ አትሰብሰቡ እየተባለ ሰው መሰብሰብ ካላቆመ በሽታው ይስፋፋል።

በተለይም በአሁን ወቅት “መዘናጋት ትክክል አይደለም። የምናውቀው ሰው እስኪሞት መጠበቅ የለብንም፤ ቁጥሩ 40 ሺህ ወይም 60 ሺህ እስኪደርስ መጠበቅ የለብንም። በጣም የምወደው ሰው ከዚህ በሽታ ሊሞት ይችላል ብለን እናስብ።

መዘናጋት በበሽታው የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር ከፍ ከማድረጉም ባሻገር፤ ቫይረሱ ስጋት የሚሆንበትን ጊዜም እንደሚያራዝመው ያስረዳሉ።

በተጨማሪም ቤት መቀመጥና እጅ መታጠብን የመሰሉ ተግባሮች ቀላል ቢመስሉም የበርካቶችን ሕይወት ይታደጋሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- ባለፉት 24 ሰዓት በፈረንሳይ 753 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 17,920 ደርሷል። በተጨማሪ 17,164 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት መደረጉን ተከትሎ አጠቅላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 165,027 ደርሷል።

- በኒውዮርክ የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ እስከ MAY 15 ተራዝሟል።

- ባለፉት 24 ሰዓት በቤልጂየም 1,236 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። 417 ሰዎች ሞተዋል።

- በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ34,000 በላይ ሆኗል። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ670,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል።

- ባለፉት 24 ሰዓት በሩዋንዳ 664 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 138 ደርሰዋል። በሌላ በኩል 6 ተጨማሪ ሰዎች አገግመዋል፤ አጠቅላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 60 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia