TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ፦ • በሩዋንዳ 923 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁለት (2) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። • በኬንያ 800 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ዘጠኝ (9) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። • በጅቡቲ 580 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሰባ ሁለት (72) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። • በኢትዮጵያ 431 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሶስት (3) ሰዎች በቫይረሱ…
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ፦

• በኬንያ 704 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ዘጠኝ (9) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

• በሩዋንዳ 664 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁለት (2) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

• በጅቡቲ 494 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አንድ መቶ ሀምሳ ስድስት (156) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

• በኢትዮጵያ 401 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሰባት (7) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTsionFirew

ይሄም ያልፋል!

'በኒውዮርክ ሆስፒታል' የድንገተኛ ክፍል ሃኪም፣ የሕብረተሰብ ጤና ባለሞያ ፣በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር ጽዮን ፍሬው ያስተላለፉት መልዕክት ፦

ኢትዮጵያ-ፋሲካን ዳግማዊ ትንሳኤን እና መጪ ሰርጎችን እንደ በፊት ተሰባስቦ በአንድነት መታደም ባለመቻላችን አንዳንዶቻችን በጣም እንዳዘንን እረዳለሁ።

ዛሬም ሆነ ነገ የመጣብን ክፉ ጠንቅ እስኪያልፍ ራሳችሁን ከአካላዊ መቀራረብ ስላራቃችሁም እናመሰግናለን።

አንዳንድ ወገኖች 'እረ ለፋሲካማ ተራርቀን አይሆንም!' ብላችሁ ለጠየቃችሁኝ መልሴ ቅልጥ ባለ ጦርነት ውስጥ ጥይት አየር ላይ ከወዲህ ወዲያ እየበረረ ቦምብ እዚህም እዚያ እየፈነዳ እንሰባሰብ አትሉም አይደል?

የጦርነት አውድማው ሆስፒታል ሆነ እንጂ ይሄንንም እንደዛ አስቡት ጦርነት ላይ ነን። እኛ የጤና ባለሙያዎቹ እየተፋለምን ነው። ስለዚህ በቤቶቻችሁ ሆናችሁ በዓሉን በሐሴት አክብሩ። ገበያውም ላይ እንጠንቀቅ አይዞን ይሄም ያልፋል!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአሜሪካ እስካሁን 100 ትውልደ- ኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ ሕይወታቸው ማለፉን አምባሳደር ፍፁም አረጋ ተናግረዋል።

በአሜሪካ የሚገኙ ብዙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ- ኢትዮጵያ በሆስፒታል፣ በአረጋዊያን መንከባከቢያና በማይዘጉ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች ስለሚሠሩ በቀጥታ ተጎጂ መሆናቸውን ገልፀዋል።

እስካሁን በጣም በተቀናጀ ሁኔታ ይፋዊ ቁጥር ባይገኝም ከእድር፣ ከኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አገልግሎትና ከመሳሰሉት ቦታዎች በተሰባሰበ መረጃ መሰረት 100 ትውልደ- ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ሕይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"የባለቤቴን አስክሬን ሳልቀብር እኔም በኮሮናቫይረስ መያዜ ተነገረኝ " - የሦስት (3) ልጆች እናት ወ/ሮ አበራሽ ኦሮሞ

Fundraiser by Yared Estifanos : ለዮሴፍ ሲቡ ቀብር ማስፈፀሚያና ለቤተሰብ ድጋፍ Memorial Fundraiser
https://www.gofundme.com/f/bkfab?utm_source=customer&utm_medium=copy_link-tip&utm_campaign=p_cp+share-sheet

15 MB (WiFi ተጠቀሙ)

#VOA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለሚመለከተው አካል!!

ይህ ሁኔታችን ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍለናል!!

- በየመነኸሪያው ያለው የሰው መጨናነቅ እና ብዛት እጅግ በጣም የሚያስፈራ ነው። ከስፍራው ካሉ የቤተሰባችን አባላት እንደተነገረን አስተባባሪዎች ወይም ሰዎች ርቀታቸውን እንዲጠብቁ የሚየርጉ ሰዎች የሉም። በተለይ ከአዲስ አበባ ወደ ክልል የሚደረግ ጉዞ በእንዲህ ያለ መልኩ መሆኑ እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው። ሳይረፍድ መፍትሄ ይፈለግለት!

- በጅቡቲ መስመር ያለው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ጥንቃቄን የሚፈልግ ነው። በጅቡቲ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከግምት ውስጥ ያስገባ ጥንቃቄ ካልተደረገ ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍለናል።

አንዳንድ አካባቢዎች ጭራሽ የቫይረሱ ስርጭት እየተረሳ ነው። በእርግጥ ለበዓል ዝግጅት ያስፈልግ ይሆናል ወደፊት ለሚመጣው ጊዜ አብረን በደስታ እንድናሳልፍ ዛሬ የምንባለውን እናድምጥ!

PHOTO : ADDIS ABABA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዋጋ እንዳያስከፍለን!

ይህ ቪድዮ አዲስ አበባ አውቶብስ ተራ ያለው እንቅስቃሴ የሚያሳይ ነው። ከፍተኛ ጥንቄ ማድረጋችን ለእኛ እና ለቤተሰቦቻችን ጤና ወሳኝ ነው። በተለይ ከአዲስ አበባ ወደ ክልል ከተሞች የምንሄድ መንገደኞች ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

እንግሊዝ በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እንዲያስችሉ የላከቻቸው የተለያዩ የሕክምና ቁሳቁስ ዛሬ አዲስ አበባ ደርሰዋል፡፡

የሕክምና ቁሳቁሱ በእንግሊዝ የዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ዲፓርትመንት የገንዘብ ድጋፍ በዩኒሴፍ ኢትዮጵያ የተገዙ ናቸው፡፡

ድጋፉ የሕክምና ማስኮች፣ የቀዶ ጥገና ጋውኖች፣ የፊት መሸፈኛዎች፣ ሙሉ አካልን የሚሸፍኑ የሕክምና አልባሳት እና ሌሎች ቁሳቁስ ተካተውበታል፡፡

ድጋፉ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ለኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡- ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር 96 ደረሰ!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 842 የላቦራቶሪ ምርመራ አራት (4) ተጨማሪ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በአጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ዘጠና ስድስት (96) ደርሷል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 96 ደርሰዋል!

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ነዋሪ ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ። በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው።

ታማሚ 2 - የ52 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላትና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላት።

ታማሚ 3 - የ52 ዓመት ኢትዮጵያዊ የባህር ዳር ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌለው። በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው።

ታማሚ 4 - የ23 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ ቅዳም ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌላት፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላት ግንኙነት እየተጣራ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈፀም የወጣ የትራንስፖርት ዘርፍ አፈፃጸም መመሪያ ይፋ የተደረገ ሲሆን፤ በትራንስፖርት አጠቃቀምና በመንግስት ሰራተኞች የስራ ሰአት ላይ ማሻሻያዎች ተደርገዋል። 

የፌዴራል የትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርአቶ አብዲሳ ያደታ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፤ በመመሪያዉ መሰረት የግል ወይም የቤት ተሸከርካሪዎችን መጠቀም የሚቻለዉ የሠሌዳቸዉ የመጨረሻ ቁጥር ሙሉ ወይም ዜሮ የሆኑት ዛሬ ሚያዚያ 9 ቀን 2012 ዓ ም ሲሆን፤ የሠሌዳቸዉ የመጨረሻ ቁጥር ጎዶሎ የሆኑት ደግሞ ነገ ቅዳሜ የሚንቀሳቀሱ ይሆናል፡፡ 

በተጨማሪም የፌዴራል ሠራተኞች ሥራ መግቢያ ሰዓት ከጠዋቱ 1፡30 ሲሆን ከስራ መውጫ ሰዓት ደግሞ ከቀኑ 9፡30 ይሆናል፤ ይህ የሥራ ሰዓት ሽግሽግ ሠራተኞቹ በስራ ሰዓት መካከል የሚያገኙትን የእረፍት ጊዜ አያሳጣቸውም ተብሏል። 

አዉቶቢሶች፣ ታክሲዎች፣ የግል ተሸከርካሪዎች፣ የመንግስት ተሸከርካሪዎች እንዲሁም የአዲስ አበባም ሆነ የኢትዮ-ጅቡቲ የመንገደኞች የባቡር ትራንስፖርት በህግ ከተፈቀደላቸዉ የሠው ብዛት 50% ብቻ እንደሚጭኑ ያስገድዳል።

More https://telegra.ph/EPA-04-17

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BREAKING

ባለፉት 24 ሰዓት በጅቡቲ 1,056 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 141 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጣል። አጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 732 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኬንያ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓት 450 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 12 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 246 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከቡዙአየሁ ታደለ ፋውንዴሽን የተላከ!

ብዙአየሁ ታደለ ፋውንዴሽን በባህር ዳር ከተማ ለሚገኙ 8,000 (ስምንት ሺ) ወገኖች የምግብ ድጋፍ አድርጓል።

የኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ አ.ማ. ግብረ-ሰናይ ድርጅት የሆነው ብዙአየሁ ታደለ ፋውንዴሽን የአክስዮን ማህበሩ አንድ ኩባንያ ከሆነው ኢስት አፍሪካን ትሬዲንግ ሃውስ (በሽ ገበያ) በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ለ8,000 (ስምንት ሺ) የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ለአንድ ወር የሚቆይ የምግብ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ወጪው በገንዘብ ብር 2 ሚሊዮን ይተመናል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በከተማው በበጎ-ፈቃደኝነት እያገለገሉ ለሚገኙ 100 ወጣቶች የእጅ ጓንትና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉ ፋውንዴሽኑ በአገሪቱ በሚገኙ ስምንት ከተሞች ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የዕለት ጉርሳቸውን ማሟላት የተቸገሩ ወገኖችን ለመርዳት እየሰራ ያለበት የፍቅር ማዕድ የተሰኘ ፕሮጀክት አንድ አካል መሆኑን የፋውንዴሽኑ የአማራ ክልል ስራ-አስኪያጅ ወ/ሮ ሔለን አዲስ ገልፀዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WHO

የዓለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ባለፈው ሳምንት በፍጥነት ከፍ እያለ መምጣቱን ተከትሎ፣ አህጉሪቱ ቀጣይዋ የቫይረሱ ማዕከል(Epicenter) ልትሆን ትችላለች አለ።

እስካሁን ድረስ በአፍሪካ በቫይረሱ ሳቢያ ወደ 1,000 የሚጠጉ ሰዎች መሞታቸውን እና ከ18,000 በላይ ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ የጠቀሰው ድርጅቱ፣ ቁጥሩ በአውሮፓ አንዳንድ ሀገራትና በአሜሪካ ከታየው እጅግ ያነሰ መሆኑን ጠቅሷል።

ቫይረሱ በደቡብ አፍሪካ፣ በናይጄሪያ፣ በኮትዲቯር በካሜሩን እና በጋና ከዋና ከተሞች ወደ መሃል አገር እየተሰራጨ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት መታዘቡን፣ የድርጅቱ የአፍሪካ ዳይሬክተር ማትሺዲሶ ሞኤቲ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ዳይሬክተሯ የአፍሪካ ሀገራት ብዙ የኮሮናቫይረስ ህሙማንን የማከም አቅም ስለሌላቸው፣ ከሕክምናው ይልቅ በመከላከል ላይ ትኩረት እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።

የድርጅቱ የአፍሪካ ዳይሬክተር አክለውም "በአብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገራት በቂ የጽኑ ህሙማን ሕክምና መስጫ መሣሪያዎች እንደሌሉ ስለምናውቅ፣ የጽኑ ህሙማን ክብካቤ ወደ መሻት ደረጃ የሚደርሱ ሰዎችን መጠን አነስተኛ ለማድረግ እንፈልጋለን" ሲሉ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፋርማ ኮሌጅ የኮሮና ቫይረስ ስርጭቱን ለመከላከል የሚረዱ ግብዓቶችን ገዝቶ ለሀዋሳ፣ ለሻሸመኔ እና ለወላይታ ሶዶ ከተማ መስተዳድሮች ገቢ በማድረግ ሀገራዊ ድርሻውን እየተወጣ መሆኑን አሳውቋል፡፡ በዚህም መሰረት እስካሁን ኮሌጁ ያበረከታቸው ድጋፎች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-

- 30 ሺህ ጊዜያዊ የእጅ ጓንቶች፤
- 200 ጥንድ አንሶላዎች ከትራስ ጨርቅ ጋር፤
- 300 መከላከያ ጋዎኖች እና
- 600 የራስ ሽፋኖች ገዝቶ በማቅረብ ገቢ አድርጓል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia