TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አርባ ምንጭ⬆️

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #አብይ_አህመድ ለጋሞ ሽማግሌዎች #የሰላም ተምሳሌትነት ምስጋ ለማቅረብ ከክቡር ፕሬዚዳንት አቶ #ኢሳያስ_አፈወርቂ ጋር በውቧና ለምለሚቷ የ40 ምንጮች ባለቤት በሆነችው በአርባምንጭ ከተማ በምስጋና ፕሮግራም ላይ በጋሞ ሽማግሌዎች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች እና በአካባቢው ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።

ምንጭ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahehiopia
ተጨማሪ ፎቶዎች⬆️ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድና የኤርትራ ፕሬዝዳንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ በጅማ ዞን ሰቃ ጮቆርሳ ወረዳ የሚገኘውን የሰቃ ፏፏቴን ዛሬ ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ላይ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ኃይለማሪያም_ደሳለኝና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ:- የጅማ ዞን ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኤርትራው ፕሬዚዳንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ በኢትዮጵያ ያደረጉት የሁለት ቀን የስራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ዛሬ አስመራ ገብተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኤርትራው ፕሬዝዳንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የደረሱበትን የሰላም #ስምምነት አስመልክተው ነገ ከድምጺ ሃፋሽ ኤርትራ ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ እንደሚያደርጉ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረ መስቀል ዛሬ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ሰላም ስምምነቱን ከፈረሙ ወዲህ ስለ ዝርዝር ይዘቱ ይፋዊ መግለጫ ሲሰጡ የነገው የመጀመሪያቸው ይሆናል፡፡

ምንጭ፦ WazemaRadio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ‼️

የኤርትራ ህዝብና መንግስት በአፍሪካ ቀንድ ለተፈጠረው ሰላምና ወዳጅነት መጠናከር ከምንም በላይ ቅድሚያ እንደሚሰጡት ፕሬዝዳንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ ተናገሩ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት ከሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው፡፡ ፕሬዝዳንቱ እንዳሉት የሰላም ሂደቱ ኢትዮጵያ የኢትዮ- ኤርትራን የድንበር ኮሚሽን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ በመቀበሏ ዙሪያ የተገደበ አይደለም።

ሂደቱ በኤርትራውያን ፅናትና በኢትዮጵያ በተፈጠረው ለውጥ በመታገዝ አዲስ የወዳጅነት ምዕራፍ የተገለጠበት ነው፡፡

ይህ እርምጃ የውጭ ኃይሎች ቀጣናውን ለመቆጣጠር የነበራቸውን ምኞት ያመከነ ጭምር ነው፡፡

አዲሱ የሰላም ንቅናቄ በመላው የአፍሪካ ቀንድ የጋራ ራዕይ በመሰነቅ ትርጉም ያለው መስተጋብርና ትብብር ለመፍጠር ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል ፕሬዝዳንት ኢሳያስ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ለዓመታት ችግርን በፅናት ተጋፍጦ በመጨረሻ ለድል በቅቷል ያሉትን ህዝባቸውን ስለቁርጠኝነቱ በእጅጉ አመስግነውታል፡፡

ምንጭ፡- የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፕሬዘዳንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ በቅርቡ #ጅቡቲን ሊጎበኙ ነው🛫
#update ፕሬዝዳንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ በቅርቡ ጅቡቲን እንደሚጎበኙ የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መሐሙድ ዐሊ የሱፍ ትናንት ላንድ ዜና አውታር ተናግረዋል፡፡ የጉብኝቱ ቀን ገና ያልተቆረጠ ሲሆን ፕሬዝዳንት ኡመር ጌሌም ወደፊት ኤርትራን ይጎበኛሉ፡፡ ላለፉት ጥቂት ወራት የሁለቱ ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች በቅርብ እየተገናኙ ሲነጋገሩ ቆይተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕምድ ለዕርቁ ምቹ ሁኔታ ፈጥረዋል፤ ጥረታቸውንም ወደ ቀጠናው መረጋጋትና ሰላም አስፍተውታል፤ ለዚህ ደሞ ዕውቅና መስጠት ያስፈልጋል- ብለዋል ውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ፡፡

©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሞቃዲሾ‼️

የኤርትራው ፕሬዝዳንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ ሞቃዲሾ ሶማሊያ ናቸው። የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት አላማ የሁለቱን ሀገሮች ግንኙነት ለማሳደግ ያለመ ነው ተብሏል። ኢትዮጵያ ሶማሊያና ኤርትራ የሶስትዮሽ የጋራ ጉባዔ በባህርዳር አድርገው በደረሱት ስምምነት አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባትና በተላያዩ ዘርፎች ለመተባበር መስማማታቸው ይታወሳል። ሶስቱ መሪዎች በሞቃዲሾ ዳግም እንደሚገናኙም ይጠበቃል። ጅቡቲን የትብብሩ አካል ለማድረግም እቅድ አለ። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በዚሁ ወደ ናይሮቢ አቅንተው ኬንያን እንደሚጎበኙም ተነግሯል።

©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፕሬዘዳንት ኢሳያስ ከAU ስብሰባ ለምን ቀሩ

(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)

የኤርትራው ፕሬዝደንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ ለምን ከአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ቀሩ? ይህን ጥያቄ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ለኤርትራው የተመድ እና አፍሪካ ህብረት ልኡክ ዋና ሀላፊ አምባሳደር አርአያ ደስታ አቅርቦላቸው ነበር። መልሳቸው፦
"የምፅዋ #የነፃነት_ቀን አሁን በኤርትራ እየተከበረ ነው። በአጋጣሚ የዚህ አመት የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ገፋ በመደረጉ ከቀኑ ጋር ተገጣጠመ። ያው ስንት ሰማእት ያለቀበት ማስታወሻ ፕሮግራም ሀገር ቤት ስላለ እዚህ አልተገኙም።"

ፎቶ፦ EP
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፕሬዝዳንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ መንግሥት ከተወሰኑ የኤርትራ ተቃዋሚ ኃይሎች አመራሮች ጋር ድርድር ጀምሯል። ግንኙነቱ የተጀመረው በኢትዮጵያ መንግሥት አደራዳሪነት ነው።

Via #Eshet_Bekele
🗞ቀን 13/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia