የቤት ኪራይ ነፃ የማድረጉ በጎ ተግባር ቀጥሏል!
ከጎተራ ወደ ወሎ ሰፈር የሚወስደዉ መንገድ ላይ የሚገኘዉ ባለ 9 ፎቅ ህንጻ ወንጌላዊት ታደሰ ህንጻ ባለቤት ወ/ሮ ገነት ታደሰ ለህንፃዉ ተከራዮች በሙሉ የአንድ ወር የቢሮ ክራይ ነፃ ማድረጋቸዉን ወንድማቸዉ ሽመልስ ታደሰ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል። አጠቃላይ የህንፃው ወርሃዊ የኪራይ ገቢ 700,000 ብር ይደርሳል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ማፊ ሞል የ2 ወር ኪራይ ነፃ አድርጓል!
ከኢንጂነር ታከለ ኡማ በተገኘው መረጃ መሰረት ማፊ ሞል ለ112 ሱቆች የሁለት ወር የሱቆች ኪራይ ነፃ ያደረገ ሲሆን 300,000 ብር ደግሞ ለከተማ አስተዳደሩ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት ለሚደረገው ጥረት ድጋፍ አድርጓል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከኢንጂነር ታከለ ኡማ በተገኘው መረጃ መሰረት ማፊ ሞል ለ112 ሱቆች የሁለት ወር የሱቆች ኪራይ ነፃ ያደረገ ሲሆን 300,000 ብር ደግሞ ለከተማ አስተዳደሩ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት ለሚደረገው ጥረት ድጋፍ አድርጓል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች ፦
- ለ65 ዓመታት ያህል በትዳር የቆዩት የ88 ዓመት የእድሜ ባለፀጋዎቹ ባለትዳሮች ሁለቱም ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸው ከወደ ስፔን ተሰምቷል።
- በዩናይት ኪንግደም የሟቾች ቁጥር ወደ 10,000 እየተጠጋ ነው። ባለፉት 24 ሰዓት 917 ሰዎች የሞቱ ሲሆን አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 9,875 ደርሷል።
- በስውዲን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 10,000 መድረሱን ለማወቅ ተችሏል።
- በቻይና ሁቤይ ግዛት ውሃና ከተማ በነበረው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለበርካታ ሳምታት ተዘግቶ የቆየው HONDA ዳግም ተከፍቶ ወደስራ ገብቷል።
- የጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የጤና ሁኔታ በእጅጉ እየተሻሻለ መምጣቱን ቃልአቀባያቸው ተናግረዋል።
- በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት 619 ሰዎች የሞቱ ሲሆን 4,694 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
- በስፔን የኮሮና ቫይረስ ሟቾች ቁጥር እየቀነሰ መጥቷል። ባለፉት 24 ሰዓት 510 ሰዎች በቫይረሱ ሲሞቱ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 16,353 ሆኖ ተመዝግባል።
- በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ1.7 ሚሊዮን በልጧል። ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከ390,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል። ከ105,000 በላይ ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።

የረር ህንፃና ሙልጌታ ዘለቀ ህንፃ ቅናሽ አድርገዋል!
የአቶ ሙሉጌታ ዘለቀ ቤተሰቦች በመገናኛ እና ኮተቤ አካባቢ በሚገኙ ህንፃዎቻቸው (የረር ህንፃና ሙልጌታ ዘለቀ ህንፃ) ውስጥ ተከራይተው ለሚገኙ ተከራዮቻቸው በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት በተፈጠረው የገበያ መቀዝቀዝ ምክንያት ሊያጡት የሚችሉትን ገቢ መነሻ በማድረግ (ለ3 ወር) እስከ ሰኔ 30 ድረስ የሚቆይ የ50% የኪራይ ቅናሽ ማድረጋቸውን ገልፀውልናል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአቶ ሙሉጌታ ዘለቀ ቤተሰቦች በመገናኛ እና ኮተቤ አካባቢ በሚገኙ ህንፃዎቻቸው (የረር ህንፃና ሙልጌታ ዘለቀ ህንፃ) ውስጥ ተከራይተው ለሚገኙ ተከራዮቻቸው በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት በተፈጠረው የገበያ መቀዝቀዝ ምክንያት ሊያጡት የሚችሉትን ገቢ መነሻ በማድረግ (ለ3 ወር) እስከ ሰኔ 30 ድረስ የሚቆይ የ50% የኪራይ ቅናሽ ማድረጋቸውን ገልፀውልናል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በተመሳሳይ ...
በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 02 አከባቢ የሚገኙት ንጉስ ህንፃ እና ጆሲ ሞል ልክ እንደ የረር ህንፃ ሁሉ ለተከራዮቻቸው የ50 % ቅናሽ አድርገዋል። መልዕክቱን ያደረሱን የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ እንግዳወርቅ ኃይሉ ናቸው።

#COVID19
የፌደራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እንቅስቃሴዎች የሚገቱ ከሆነ የቤት ለቤት አቅርቦት መስጠት እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡
ወረርሽኙ በኢትዮጵያ ከተከሰተ ጀምሮ ሕብረተሰቡ ላልተፈለገ የዋጋ ንረት መጋለጡን የሚያነሳው ኤጀንሲው፤ የአቅርቦት ችግሩን ለመፍታት ብሎም እንቅስቃሴ የሚገታ ከሆነ የቤት ለቤት አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል፡፡
የምግብ ፍጆታዎችን በተለይም አትክልቶችን እና ሰብሎችን ለማቅረብ የተዘጋጀው ኤጀንሲው፤ ለመጪው የትንሳኤ በዓል የሚያስፈልጉ የእንስሳት ተዋጽኦ ውጤቶች፣ ሰብሎች እና የሌሎች ሸቀጦች እጥረት የለብኝም ብሏል፡፡
ኤጀንሲው ያሉበትን የገንዘብ እጥረት፣ የማከማቻ መጋዘን ውስንነት እንዲሁም ወረርሽኙ የሚያመጣውን የምጣኔ ሃብት ቀውስ ለመቅረፍ 600 ሚሊዮን ብር ከመንግስት እንደተመደበለት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ኡስማን ሱሩር ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፦ አሐዱ ቴሌቪዥን

የሀዋሳ ኦሲስ ኢንተርናሽናል ሆቴል ባለቤትና የሉሲ ኮፊ ኤክስፖርተር በአሁን ሰዓት ደግሞ 'ቀነኒሳ ሆቴል' ተከራይተው በአዲስ መልክ እየሰሩ የሚገኙት የአትሮኖስ ትሬዲንግ ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ አቶ ብርሃን ተድላና አቶ ተስፋዬ አየለ ሀገሪዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ እንደሆነ አሳውቀውናል።
- ይህ የችግር ወቅት እስኪያልፍ ድረስ በየሳምንቱ እሁድ ዕለት 250 የምግብ እጥረት ሊገጥማቸው ለሚችሉ ዜጎች፣ ጎዳና ላይ ላሉ ወገኖችና ለአእምሮ ህሙማን በያሉበት የምግብ አቅርቦት ለማድረስ ዝግጅት አድርገዋል። ከምግብ በተጨማሪ የንፅህና መጠበቂያ ሳሙናም ለማድረስ ይሰራል።
- የምገባው ተግባር ከነገ ይጀምራል። አቶ ብርሃን ተድላ ከማኔጅመት አባላት ጋር በመሆን ይህን ስራ የሚከውኑ ይሆናል።
- ምንም እንኳን የቤት ኪራይ ወጪ ቢኖርባቸውም ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እስከመጨረሻው ለመወጣት ቃል ገብተዋል።
- አቶ ብርሃን ተድላ ሁሉም አካል ጊዜውን በበጎ ነገር ላይ በማሳለፍ ከፈጣሪው ጋር ሊታርቅ ይገባል፤ እኛ የምንበላውን ለጎረቤቶቻችን በማካፈልም ይህን ፈታኝ ወቅት እንለፈው ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

በተጨማሪ ባለሀብቱ አቶ ብርሃን ተድላ በድርጅቶቻቸው ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞቻቸውን እንዳላሰናበቱ ገልፀውልናል።
ግምሽ ሰራተኞች ለቫይረሱ ተጋላጭ እንዳይሆኑ የዓመት ፍቃድ እንዲያገኙ በማድረግ እረፍት እንዲወጡ ተደርጓል።
በአዲስ አበባ በተከራዩት 'ቀነኒሳ ሆቴል' ውስጥ የሚሰሩ ግማሽ ሰራተኞች ደግሞ ለቫይረሱ እንዳይጋለጡ ለመከላከልና ጥንቃቄ ለማድረግ ሲባል በዛው ሆቴል ውስጥ ደህንነታቸው ተጠብቆ፣ ማደሪያም ተዘጋጅቶላቸው እየሰሩ ይገኛሉ።
በሀዋሳው ኦሲስ ሆቴል ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ደግሞ ከቤታቸው እየተመላለሱ እየሰሩ ቢገኙም ለቫይረሱ እንዳይጋለጡ በቂ ጥንቃቄ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ነግረውናል።

#StateofEmergency
የተጣሉ ግዴታዎች!
- ማንኛውም በስራ ላይ ያለ ፣ ጡረታ የወጣ ወይም በትምህርት ላይ ያለ የጤና ወይም የሌላ ሙያ ባለቤት ወይም ማንኛውም ዜጋ የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት አስተዋፅዖ እንዲያደርግ በመንግስት ጥሪ ሲደረግለት የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡
- ማንኛውም የቤት፣ የሆቴል፣ የአፓርታማ፣ የተሽከርካሪ፣ የአዳራሽ ወይም የማንኛውም ንብረት ባለቤት መንግስት የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል ፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ለሚያደርገው ጥረት አስፈላጊ የሆነ ንብረቱን ለዚህ አላማ አገልግሎት ላይ እንዲውል በሚኒስትሮች ኮሚቴ ወይም ኮሚቴው ውክልና በሰጠው የመንግስት አካል ሲወሰንና ሲጠየቅ ንብረቱን ለእለት ከእለት ፍጆታው የሚጠቀምበት ካልሆነ በሰተቀር ውሳኔውን ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ አለበት።
ተጨማሪ የተጣሉ ግዴታዎችን ይህን ተጭነው ያንብቡ : https://telegra.ph/DrAbiyAhemed-04-11

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተከለከሉ ተግባራት!
- ለሀይማኖታዊ ወይም ማህበራዊ አላማ፣ ለመንግስታዊ ወይም ፖለቲካዊ ስራ ወይም ሌላ መሰል አላማ አምልኮ በሚደረግባቸው ቦታዎች፣ በመንግስት ተቋማት፣ በሆቴሎች፣ በማናቸውም የመሰብሰቢያ አዳራሾችና በማናቸውም ቦታ አራትና ከዚያ በላይ ሆኖ በአንድ ቦታ ላይ መገኘት የተከለከለ ነው፤
- ማንኛውም ሰው ለሰላምታና ሌላ ማንኛውም አላማ በእጅ መጨባበጥ ክልክል ነው፣
- ማንኛውም ሀገር-አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ሰው በማንኛውም ጊዜ ከተሸከርካሪው ወንበር ብዛት 50% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤
- ማናቸውም የከተማ ውስጥ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ታክሲ፣ አውቶቡስ፣ የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አውቶቡስ ከተሸከርካሪው የወንበር ቁጥር 50% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤
- ማንኛውም የግል ተሸከርካሪ ሾፌሩን ሳይጨምር ከተሸከርካሪው የወንበር ቁጥር 50% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤
- የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ከዚህ በፊት ሲጭን ከነበረው አቅሙ 25% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤ 8. የኢትዮ-ጂቡቲ የምድር ባቡር ከወንበር ቁጥሩ 50% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ ተከለከለ ነው፤
ተጨማሪ የተከለከሉ ተግባራትን ይህን ተጭነው ያንብቡ
https://telegra.ph/DrAbiyAhemed2-04-11

በአሜሪካ 'ኒውዮርክ ሆስፒታል' የድንገተኛ ክፍል ሃኪም ፣ የሕብረተሰብ ጤና ባለሞያ ፣ በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር እና የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስተር አማካሪ የሆኑት ዶክተር ጽዮን ፍሬው በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ይህን ብለዋል፦
"ኢትዮጵያ እዚ በቺካጎ ከተፈጠረው እንማር። አንድ በሽታው እንዳላበት ያለወቀ ሰው ለቅሶ እና ከዛም ልደት ግብዣ በመሄዱ 16 ሰው ታሞ 3 ሰው ሞቷል። እባካችሁ ግብዣው እና ድግሱን ለሌላ ቀን እናርገው። አለበዚያ ለቅሶው ይበዛል።"
https://www.washingtonpost.com/health/2020/04/08/funeral-birthday-party-hugs-covid-19/
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ኢትዮጵያ እዚ በቺካጎ ከተፈጠረው እንማር። አንድ በሽታው እንዳላበት ያለወቀ ሰው ለቅሶ እና ከዛም ልደት ግብዣ በመሄዱ 16 ሰው ታሞ 3 ሰው ሞቷል። እባካችሁ ግብዣው እና ድግሱን ለሌላ ቀን እናርገው። አለበዚያ ለቅሶው ይበዛል።"
https://www.washingtonpost.com/health/2020/04/08/funeral-birthday-party-hugs-covid-19/
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች፦
- ህንድ ውስጥ በእድሜ ትንሹ የቫይረሱ ተጠቂ ሆኖ ተመዝግቦ የነበረው የ10 ወር ህፃን ከበሽታው አገግሞ ከሆስፒታል መውጣቱ ተሰምቷል።
- በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ20,000 በልጧል። ባለፉት 24 ሰዓት ከ1,300 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል። አሜሪካ በሟቾች ቁጥር ከዓለም ሀገራት ቀዳሚ ሆና ተመዝግባለች።
- በፈረንሳይ ባለፉት 24 ሰዓት 635 ሰዎች የሞቱ ሲሆን አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ከ13,800 በልጧል።
- በሩሲያ ባለፉት 24 ሰዓት 1,667 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ 12 ሰዎች ደግሞ መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።
- በሩዋንዳ 842 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 2 ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ሁለቱም ቀድሞ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው ናቸው። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 120 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት 11 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል። አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎችም 18 ደርሰዋል።
- በዩጋንዳ 555 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁሉም ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል። ከበሽታው አገግመው ከህክምና ማዕከል የወጡ ሰዎች ደግሞ 4 ደርሰዋል።

#StateOfEmergency
የባንክ አገልግሎት በሚሰጥባቸው አካባቢዎች፣ በገበያዎች፣ በትራንስፖርት መሳፈሪያ ቦታዎች፣በትራንስፖርት ውስጥ፣ በሱቆች፣ በመድሀኒት መሸጫ አካባቢዎች ፣ ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎች እና ሌሎች ህዝብ በሚበዛባቸው መሰል አካባቢዎች የሚገኝ ማንኛውም ሰው አፍና አፍንጫው ላይ መሸፈኛ የማድረግ #ግዴታ አለበት።
የአፍና አፍንጫ መሸፈን ግዴታ ለዚሁ አላማ ተብሎ በፋብሪካ በተሰራ፣ በቤት ውስጥ ከተለያዩ ጨርቃጨርቆች በተዘጋጀ ወይም በማናቸውም አይነት ልብሶች ሊፈጸም ይችላል።
#PMOEthiopia

የጨርቅ ማስክ አዘገጃጀትና ለመስራት የሚመረጡ የጨርቅ አይነቶች፦
ይህንን በተመለከተ ጥቂት ጥናቶች ቢኖሩም አንዱ ካንዱ እንደሚሻል በእርግጠኝነት መናገር ያስቸግራል፡፡ የጨርቁ ውፍረት በጨመረ ቁጥር የተሻለ የመከላከል አቅም አለው ተብሎ ይታሰባል፡፡
ጨርቁን በመያዝ በደንብ የሚያበራን የመብራት ብርሀን ምን ያህል እንደሚያስተላለፍ በመመልከት (light test) የጨርቁን ውፍረት መመዘን ይቻላል፡፡ በቀላሉ ብርሃን የማያስተላልፉ ጨርቆች የተሻለ ይመረጣሉ ማለት ነው፡፡
በአገራችን ሁኔታ ቀላሉ እና ለመተግበር የሚመቸው የጥጥ (cotton) ጨርቆችን መጠቀም ሲሆን በቂ ውፍረት እንዲኖረው ሁለት ተመሳሳይ ልኬት ያላቸውን ጨርቆች መደረብ የተሻለ ነው፡፡
የጨርቅ ማሰክ አስተጣጠብ የጨርቅ ማስክ እንዴት መታጠብ አለበት ከሚለው አንፃር ጥናቶች ባይኖሩም እንደተለመደው በሳሙናና የሞቀ(ትኩስ)ውሃ ማጠብ ቫይረሱን እንደሚገድለው ይጠበቃል፡፡
መረሳት የሌለባቸው ጉዳዮች ማስክ ማድረግ ብቻውን ከኮቪድ19ም ይከላከላል ብሎ ማሰብ ስህተት ነው፡፡ ማስክ መልበስ ከመሰረታዊ ጥንቃቄዎች ጋር ሲቀናጅ የተሻለ ውጤታማ ያደርጋል፡፡
እነዚህም፦
• አካላዊ መራራቅን መተግበር
• አካላዊ ንክኪዎች ማስቀረት
• በተደጋጋሚና በአግባቡ እጅን መታጠብ/በአልኮል ማፅዳት
• ሰዎች በሚበዙባቸው/በሚሰበሰቡባቸውን ቦታዎች አለመገኘት
የጤና ባለሙያዎች ካላቸው የተጋላጭነት ደረጃ አንፃር የጨርቅ ማስኮችን እንዲጠቀሙ ፈፅሞ አይመከርም፡፡ በተቻለ መጠን እንዳስፈላጊነቱ ሰርጂካል ማስክ ወይም N-95 ማስክ መጠቀሙ የተሻለ ነው፡፡
https://yetenaweg.home.blog/2020/04/10/አዲስ-መረጃ-update-ስለ-የፊት-ማስክ/amp/?__twitter_imp
ምንጭ፦BROOK ALEMAYHU