#HARAR
በሀረር ከተማ የሚገኙ የንግድ ማዕከል ባለቤቶች ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የንግድ ስራው በመቀዛቀዙ ለተከራዮቻቸውን የወራት ቤት ኪራይ ስረዛ አድርገዋል።
የአውሃኪም የንግድ ማዕከል ባለቤት አቶ አብዱልሃኪም መሀመድ በሀረሪ ክልል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በክልሉ የሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎች፣ አረጋዊያንና አቅመ ደካሞችን የክልሉ መንግስት ድጋፍ እንዲያደርጉ በጠየቃቸው መሰረት 100 ሺ ብር ለግሰዋል።
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የንግድ ስራ መቀዛቀዝ በመታየቱና ችግሩን ለመጋራት በማሰብ በንግድ ማዕከላቸው ውስጥ ያከራያኋቸውን 10 ተከራይ ነጋዴዎችን ሁለት ወራት ከኪራይ ነጻ እንዲሰሩ አድርገዋል።
የኦሬንታል ትሬዲንግ የንግድ ማዕከል ባለቤት አቶ ኑሜር አብዱላዚዝ በንግድ ማዕከሉ ውስጥ ለሚሰሩ ለ26 ግለሰቦች የአንድ ወር የቤት ኪራይ ነጻ ሆነው ስራቸውን እንዲያከናውኑ አድርገዋል። በወር አጠቃላይ የማገኘው 480 ሺህ ብር ነው።
ምንጭ፦ የሀረሪ ክልል ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

አዲስ አበባ ከተማ ጀሞ 1 ደንይሽር የገበያ ማእከል የኑሮ ጫና እንዳይፈጠር የሁለት ወር የቤት ኪራይ ለተከራዮች በሙሉ ነፃ አድርጓል። በተጨማሪ ለተከራይ በሙሉ 20 ኪሎ ዱቄት፣ 5 ሊትር ዘይት እና 5 ኪሎ እሩዝ እና አካባቢው ላይ ያሉ በኑሮ አነስተኛ የሆኑ በሙሉ ዱቄት እሩዝ ዘይት አግዟል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የኑሮ ጫና እንዳይፈጠር የተለያዩ የንግድ ማዕከላት የቤት ኪራይ ነፃ እያደረጉ እንደሆነ ይታወቃል አንዳንዶች የአንድ ወር፣ ሌሎች እስከ ሶስት ወር ድረስ ነፃ እያደረጉ ነው።
በሌላ በኩል ገበያ በተቀዛቀዘበት በዚህ ወቅት በአስቸኳይ የሶስት ወር የቤት ኪራይ እንዲከፍሉ እየተገደዱ ያሉ ዜጎች እንዳሉንም ነግረውናል።
ከዚህ በተጨማሪ የህንፃ ባለቤቶች አንድም የነጋዴዎችን ጫና ለመቀነስ እንዲሁም የህብረተሰብ ኑሮ ላይ ያለው ጫና እንዲቀስ በሚወስዱት እርምጃ እየተመሰገኑ ቢሆንም የቤት ኪራይ ነፃ የተደረገላቸው አንዳንድ ነጋዴዎች ከልክ ያለፈ የዋጋ ጭማሪ ሲያደርጉ መታዘባቸውን የቤተሰባችን አባላት ገልፀውልናል።
ነጋዴዎችም እንተሳሰብ ተብላችኃል!

የቤት ለቤት የኮቪድ-19 ምርመራ ሊጀመር ነው!
በአዲስ አበባ ከተማ የቤት ለቤት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ሊጀመር ነው። ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ እንደገለጹት ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሁሉም ወረዳዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ይጀመራል።
ምርመራው ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ ተብለው ከተለዩ ወረዳዎች የሚጀምር መሆኑን ገልጸው በመዲናዋ 117ቱም ወረዳዎች ይከናወናል ብለዋል።
ለምርመራው ጡረታ ላይ የነበሩና በሞያው ልምድ ያላቸው ከ1 ሺህ 200 በላይ ሃኪሞች የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው ካሉት ሃኪሞች ጋር ተጨማሪ ሃይል በመሆን ዝግጁ መሆናቸውንም ከንቲባው ገልጸዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

#EngTakeleUma
በሚቀጥለው ሳምንት ተማሪዎች በያሉበት ሆነው ትምህርት እንደሚጀምሩና የምገባ መርሃ ግብሩም እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ አረጋግጠዋል።
በተያዘው መርሃ ግብር መሰረት ከ7ኛ ክፍል በታች የሚማሩ ተማሪዎች ትምህርቱን በሬዲዮ የሚከታታሉ ይሆናል ተብሏል። ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች ደግሞ ትምህርታቸውን በፕላዝማ የሚከታተሉ ይሆናል።
በዚህ ሂደት ተማሪዎችና መምህራን የተለያዩ መረጃዎችን የሚለዋወጡበት የአሰራር ስርአትም መሰርጋቱ ተገልጿል።
የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብርም በተለያዩ አካባቢዎች 1 ሺህ 200 ተማሪዎች የሚመገቡባቸው የምግብ ባንኮች ተዘጋጅተዋል፤ ለምግብ አቅርቦቱም 30 ሺህ ወጣቶች ዝግጁ ሆነዋል ተብሏል።

#AddisAbaba
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የደንበኛ ድርቅ የመታቸው የአዲስ አበባ ሆቴሎች ያጡት ገቢ እየተጠና መሆኑን አሀዱ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
የአገልግሎት ዘርፍ የሆነውና ከቱሪዝም ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንዳለው የሚታመነው የሆቴል ዘርፍ የኮቪድ-19 መከሰትን ተከትሎ የገቢ ማጣት ጉዳት እየደረሰበት ነው።
የአዲስ አበባ ሆቴል ባለንብረቶች ማኅበር ማኔጂንግ ዳይሬክተር ቢንያም ብስራት እንደተናገሩት በከተማዋ ያሉ ሆቴሎች የደረሰባቸው የጉዳት መጠን በገንዘብ ለማወቅ ጥናት እየተደረገ ነው።
ቫይረሱ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተከሰተ በኋላ እንግዶች ወደ ሆቴሎች እየመጡ ባለመሆኑ፤ የሚያጡት ገቢ ከፍተኛ እንደሚሆን መገመት አዳጋች አይደለም ተብሏል።
በማኅበሩ ሥር የሚወከሉ 130 ሆቴሎች ውስጥ የሚሰሩ 15 ሺሕ ሰራተኞች ያሉ ሲሆን ሥራቸውን እንዳያጡ ጥረት እየተደረገ ስለመሆኑም ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።
ምንጭ፦ አሐዱ ቴሌቪዥን

ከመጋቢት 27 - ሚያዚያ 2 ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ!
በኢትዮጵያ የካሮና ቫይረስ ምርመራ ከዕለት ወደዕለት ከፍ እያለ መጥቷል። በዛው ልክ በየእለቱ ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎችም እየጨመረ ነው።
• መጋቢት 27/2012 ዓ/ም የወጣው መግለጫ - 'ባለፉት 24 ሰዓት 59 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አምስት (5) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል'
• መጋቢት 28/2012 ዓ/ም የወጣው መግለጫ - 'ባለፉት 24 ሰዓት 164 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አንድ (1) ሰው በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል'
• መጋቢት 29/2012 ዓ/ም የወጣው መግለጫ - 'ባለፉት 24 ሰዓት 264 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ስምንት (8) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል'
• መጋቢት 30/2012 ዓ/ም የወጣው መግለጫ - 'ባለፉት 24 ሰዓት 225 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሶስት (3) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል'
• ሚያዚያ 1/2012 ዓ/ም የወጣው መግለጫ - 'ባለፉት 24 ሰዓት 294 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አንድ (1) ሰው በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል'
• ሚያዚያ 2/2012 ዓ/ም የወጣው መግለጫ - 'ባለፉት 24 ሰዓት 442 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ዘጠኝ (9) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል'

በትግራይ ቤት ለቤት ምርመራ ሊጀመር ነው!
በትግራይ ክልል ሁሉም ወረዳዎችና ከተሞች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያለመ የቤት ለቤት ዳሰሳ ከሚቀጥለው ሰኞ ሚያዚያ 5 ቀን 2012 ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት እንደሚካሄድ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል።
የቢሮው ሀላፊ ዶክተር ሓጎስ ጎደፋይ እንደገለፁት፥ በዳሰሳው 23 ሺህ የጤና ባለሙያዎች ይሳተፋሉ። ህብረተሰቡ ቫይረሱ የሚያስከትለው ጉዳት፣ ለመከላከል የሚያስችል ግንዛቤና በክልሉ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚመለከት ያለው ግንዛቤ በእያንዳንዱ ቤት ይዳሰሳል ነው ያሉት።
በተጨማሪም ከክልሉ ውጭ የመጡ ሰዎች ካሉ እያንዳንዱን ቤት በመፈተሽ ምርመራ ይደረግላቸዋል። ሁሉም ባለሙያ በክልሉ ባሉት 92 ወረዳዎች የተመደበ ሲሆን፥ በዚህም በገጠር በቀን ከ15 እስከ 20 እንዲሁም በከተማ ከ25 እስከ 30 ቤቶች ለማጥናት እቅድ ተይዟል ብለዋል።
ዳሰሳው በመቐለ ከተማ ነገ እንደሚጀመር በመጠቆምም ህብረተሰቡ ለዳሰሳው እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ

ከኬር አውድ ኢንተርናሽናል ሆቴል የደረሰን መልዕክት ፦
- ሆቴሉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት በሚደረገው ጥረት ሀገራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል።
- በሀዋሳ ከተማ ሆቴሉ ባለበት ክፍለ ከተማ ለሚገኙ 720 ለሚጠጉ ነዋሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር እገዛ አድርጓል።
- የቫይረሱ ወረርሽኝ በሀዋሳ ከተማ ከተከሰተ እና ገፍቶ ከመጣ ደግሞ ሆቴሉ 100 ለሚሆኑ የጤና ባለሞያዎች ለአንድ ወር ነፃ የምሳ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን አሳውቋል።
- ወረርሽኙን ለመግታት በሚደረገው ጥረት እስከመጨረሻው ድረስ ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጎን በመቆም ማህበራዊ ግዴታዬን እወጣለሁ ብሏል።
- በተጨማሪ በድርጅቱ ስር በሻሸመኔ ከተማ ሱቆች ተከራይተው ለሚሰሩ ዜጎች በሙሉ የአንድ ወር የቤት ኪራይ ነፃ አድርጓል።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ አራት (4) ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው!
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 345 ግለሰቦች መካከል አራቱ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ እስካሁን ባለው ሂደት በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ለሶስት ሺህ 500 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው አራቱም ግለሰቦች ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውንም ነው የገለጹት።
ሁለቱ ወንድ ሁለቱ ደግሞ ሴቶች ሲሆኑ ሶስቱ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው።
ከእነዚህም መካከል አንድ የ30 ዓመት ሴትና አንድ የ29 ዓመት ወንድ ኢትዮጵያዊያን ከዱባይ መጥተው በለይቶ ማቆያ ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ መሆኑን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
አንድ የ33 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊት ደግሞ የአሜሪካ አገር የጉዞ ታሪክ ያላት ናት።
ሌላኛው ግለሰብ የ42 ዓመት እድሜ ያለው ኢትዮጵያዊ ነው ብለዋል። ግለሰቡ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌለው ሲሆን፤ በህመሙ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳለውና እንደሌለው እየተጣራ መሆኑን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 10 ደረሱ!
በኢትዮጵያ ቫይረሱ እንዳለባቸው ተረጋግጦ ክትትል እያደረጉ ከሚገኙ ግለሰቦች መካከል ተጨማሪ ስድስት ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ዶ/ር ሊያ ይፋ አድርገዋል። ይህን ተከትሎም በአጠቃላይ ከህመሙ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ወደ 10 ከፍ ብሏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ቫይረሱ እንዳለባቸው ተረጋግጦ ክትትል እያደረጉ ከሚገኙ ግለሰቦች መካከል ተጨማሪ ስድስት ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ዶ/ር ሊያ ይፋ አድርገዋል። ይህን ተከትሎም በአጠቃላይ ከህመሙ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ወደ 10 ከፍ ብሏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse
ባለፉት 24 ሰዓት 345 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 69 ደርሷል።
የታማሚዎች ሁኔታ ፦
ታማሚ 1 - የ33 ዓመት ኢትዮጵያዊት ከአሜሪካ የመጣችና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለች።
ታማሚ 2 - የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊት #ከዱባይ የመጣችና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለች።
ታማሚ 3 - የ29 ዓመት ኢትዮጵያዊ #ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 4 - የ42 ዓመት ኢትዮጵያዊ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌለው፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት እንዳለውና እንደሌለው እየተጣራ ነው።

#DrMercyMwangangi
ባለፉት 24 ሰዓት በኬንያ 491 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁለት (2) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አንደኛው ኬዝ ከናይሮቢ ሲሆን ሌላኛው ከሞንባሳ እንደሆነ ተገልጿል።
በአሁን ሰዓት በኬንያ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 191 የደረሰ ሲሆን ከነዚህ መካከል 109ኙ ወንዶች ሰማንያ ሁለቱ (82) ደግሞ ሴቶች ናቸው።

በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ሁለት (2) ተጨማሪ ሰዎች በማገገማቸው አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 24 ድርሷል።

በጅቡቲ ሀለተኛው (2) ሞት ተመዝግቧል!
በጅቡቲ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ሁለት ሆኗል። በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓት 277 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 37 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችም 187 ደርሷል። ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም 36 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅቡቲ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ሁለት ሆኗል። በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓት 277 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 37 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችም 187 ደርሷል። ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም 36 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19
- ደቡብ ሱዳን አራተኛውን (4) የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ሪፖርት አድርጋለች።
- በሱዳን ደግሞ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 17 ከፍ ብሏል፤ በትላንትናው ሪፖርት መሰረት።

#StateofEmergency
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈፀሚያ ደንብን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ይፋ አደረገ።
ክልከላን በሚመለከት፦
- ማንኛውም ሃይማኖታዊ ይሁን ፖለቲካዊ ስብሰባዎች፣ እድር፣ ደቦ፣ እቁብና ሌሎችም ከ4 ሰው በላይ ስብሰባዎች ክልክል ናቸው።
-አራት ሰዎችም ቢሆኑ ሁለት የአዋቂ ሰው እርምጃ የጠበቀ መሆን አለበት።
- ቀብርና ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮች ሲኖሩ ግን እየታዩ ሊፈቀዱ የሚችሉበት አሰራር ይኖራል።
- ታራሚዎች ከጠበቆቻቸው ጋር አስፈላጊው ጥንቃቄ ተደርጎ እንዲገናኙ የሚፈቀድ ቢሆንም ጥየቃ ለሚሄዱ ሰዎች አይፈቀደም።
- በፖሊስ የተያዙ እስረኞችንም ስንቅ ከማቀበል በስተቀር መገናኘት የተከለከለ ነው።
- በድንበር አካባቢ ከካርጎ፣ የደረቅና ፈሳሽ ጭነት አገልግሎቶች በስተቀር ሌሎች እንቅስቃሴዎች ዝግ ተደርገዋል።
- የቤት ተከራዮች በራሳቸው ፍላጎት ካልወጡ በስተቀር ማስወጣትና ኪራይም መጨመር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተከልክሏል።
- ሰራተኞችን መቀነስና የስራ ቅጥር ውል ማቋረጥም ተከልክሏል።
- ተማሪዎችና መምህራን በኦን ላይን ካልሆነ በአካል እንዲገናኙ አይፈቀድም።
MORE @TIKVAHETHMAGAZINE
#ENA

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦
• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 3,577
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 345
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 4
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ያሉ - 54
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• አዲስ ያገገሙ - 6
• አጠቃላይ ያገገሙ - 10
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 69
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦
• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 3,577
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 345
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 4
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ያሉ - 54
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• አዲስ ያገገሙ - 6
• አጠቃላይ ያገገሙ - 10
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 69
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ምርመራ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ!
በጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ላብራቶሪ ማዕከል በሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ዛሬ ተምርቋል።
በቫይረሱ የሚጠረጠሩ ግለሰቦች ናሙናን ወደ አዲስ አበባ በመላክ ምርመራ ይደረግ እንደነበር ያነሱት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በዛሬው እለት ተመርቆ ስራ የጀመረው ማእከል ምርመራውን በክልሉ ለማድረግ የሚያስችል በመሆኑ ተናግረዋል።
ምንጭ፦ የሱማሌ ክልል ቴሌቪዥን ጣቢያ