TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETH ~ 246,000+ #የቤተሰብ አባላት ከመላው ኢትዮጵያ እና ከተለያዩ የውጭ ሀገራት!! ቻናሉ ከቀን ወደ ቀን የአባላት ቁጥር እያደገ ይገኛል ለዚህ ደረጃ መድረስም ሙሉውን ድርሻ የምትወስዱት እናተው ናችሁ እና ከልብ አመሰግናለሁ!!
.
.
#ETHIOPIA
#EHRC

" ... ጉዳዩ ከዚህ የበለጠ ሳይባባስ ፓርላማው የመንግስት አስፈፃሚ አካሉን በአስቸኳይ ሊያሳስብ ይገባል " - ዶ/ር ዳንኤል በቀለ

ዛሬ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የ9 ወራት የእቅድ አፈፃፀሙን ሪፖርት ለህ/ተ/ም/ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርቧል።

በዚህም ወቅት የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፥ በአማራ ክልል የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች አሳሳቢ እንደሆኑ ቀጥለዋል ብለዋል።

ከቅርብ ጊዜ አንስቶ መንግሥት በአማራ ክልል እያካሄደ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከሰብዓዊ መብቶች አንፃር በጣም የሚያሰጋነው ሲሉ ገልጸዋል።

ዋና ኮሚሽነሩ ፤ በአሁን ወቅት በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ #በሲቪል ሰዎች ላይ ፦
- የሞት፣
- የንብረት መውደም፣
- የመፈናቀል ጉዳት መድረሱን በዚህም የሰብዓዊ መብት ስጋቱም መቀጠሉን አንስተዋል።

" መንግሥት የፀጥታ እርምጃ በአማራ ክልል በማካሄድ ላይ የሚገኝ መሆኑን አሳውቋል ፤ " ያሉት ዶ/ር ዳንኤል " ነገር ግን ይህ ወታደራዊ እርምጃ የሰብዓዊ መብት እንድምታ ስላለው ፣ የሰብዐዊ መብት ተፅእኖ ስለሚፈጥር ይሄን በቅርበት እየተከታተልን ነው " ብለዋል።

" እስካሁን ባለው መረጃ በመነሳት ከሰብዓዊ መብቶች አንፃር በጣም የሚያሰጋ ስለሆነ ኢሰመኮ #ውይይት እና #ሰላማዊ መፍትሄ አስፈላጊነትን አበክሮ በማሳሰብ ጉዳዩ ከዚህ የበለጠ ሳይባባስ ፓርላማው የመንግስት አስፈፃሚ አካሉን በአስቸኳይ ሊያሳስብ ይገባል። " ሲሉ አክለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ዶ/ር ዳንኤል ባቀረቡት ሪፖርት የዘፈቀደ እስር ፣ ሰዎች ሲታሰሩ የሚያዙበት መንገድ፣ ለሰብዓዊ ጉዳዮች አሳሳቢ ሆኖ ቀጥሏል ብለዋል።

ዶ/ር ዳንኤል ፤ " በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈፀመው የዘፈቀደ እስር እና በእስር ወቅት የሚፈፀሙ ተገቢ ያልሆኑ አያያዞች / አንዳንድ ቦታዎች ድብደባን ጨምሮ ተገቢ ያልሆነ አያያዝና እስራት እንዲሁም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለመከበርም ቀጥሏል "  ብለዋል።

ዋና ኮሚሽነሩ ፤ አንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚፈፀሙት የዘፈቀደ እስሮች #የቤተሰብ አባላትን ጭምር ለማጥቃት የሚውሉ ናቸው ሲሉ ለፓርላማው በሪፖርታቸው አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia