TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GRAPHIC_CONTENT ከላይ በፎቶው የምትመለከቱት ኢትዮጵያዊ ዜጋ በፖሊሶች የተያዘበት መንገድ በርካቶችን አስቆጥቷል፤ በርካቶች በማህበራዊ ሚዲያ እየተቀባበሉት ነው፤ በርካቶችም ድርጊቱን አውግዘዋል።

በዛሬው ዕለት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ስለጉዳዩ ተጠይቆ ይህን ምላሽ ሰጥቷል፦

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ፅህፈት ቤት ሃላፊ ኮማንደር #ታዬ_ግርማ  ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ችግር እንደተፈጠረ ተደርጎ በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተሰራጨ ስላለው ምስል በኮሚሽኑ በኩል በትክክል አለመረጋገጡን ተናግረዋል። ከዚህ ባለፈ ግን ችግሩ በማን እና እንዴት እንደተፈጠረ #እያጣራ እንደሚገኝም ነው የገለጹት። የክልሉ ፖሊስ ለኦሮሞ ህዝብ አለኝታውና መከታው ሆኖ በርካታ ችግሮችን እየተጋፈጠ ሲታገል የቆየና አሁንም በዚያው ቁርጠኝነት እያገለገለ እንዳለም አስረድተዋል፡፡ ድርጊቱ የክልሉን ፖሊስ ስም ለማጥፋት የተፈጸመ በመሆኑ የፖሊስ ኮሚሽንም ይሁን ሌላ አካል ጉዳዩን በፈጸሙ አካላት ላይ #እርምጃ እንደሚወስድ ገልጸዋል። በምስሉ ላይ የሚታዩ ግለሰቦችንም የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንን የደንብ ልብስ ከመልበሳቸው ውጭ ማንነታቸውን ማረጋገጥ እንዳልተቻለም ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbaba 🛬 #DireDawa

በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET248 ድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፍያ ለማረፍ በዝግጅት ላይ ሳለ በአውሮፕላኑ ውስጥ #ጢስ መታየቱን አየር መንገዱ አሳውቋል።

አውሮፕላኑ በድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፍያ በሰላም እንዳረፈም ገልጿል።

መንገደኞችን በተለመደው መልኩ ከአውሮፕላኑ ማውረድ መቻሉን ገልጾ አየር ጢሱ የተነሳበትን ምክንያት በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ጠቁሟል።

ለተፈጠረው ክስተት መንገደኞቹን ይቅርታ ጠይቋል።

ከዚህ ቀደም (ከወራት በፊት) ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ አውሮፕላን ውስጥ ጭስ መታየቱን ፤ ነገር ግን አውሮፕላኑ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ በተመደበለት የመንገደኞች ማስተናገጃ በር ያለ ምንም እክል መቆሙ መንገዶኞቹም ከአውሮፕላን ላይ ደህንነታቸው እንደተጠበቀ መወርዳቸው መገለጹ የሚዘነጋ አይደለም።

በወቅቱም ጢሱ ከእሳት ወይም ከሌላ ነገር ጋር የተያያዘ ሳይሆን አዉሮፕላን ዉስጥ ያለዉ ዘይት ተቃጥሎ የተፈጠረ መሆኑን ይህም አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ችግር እንደሆነ አስረድቶ ነበር።

ዛሬ ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ በነበረውና ድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፍያ ለማረፍ በዝግጅት ላይ በነበረው አውሮፕላኑ ውስጥ የታየው #ጢስ ምክንያት ምን እንደሆነ #እያጣራ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።

@tikvahethiopia