TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የታማሚዎች ሁኔታ ፦

- በበሽታው መያዛቸው ከተረጋገጠ ስምንቱ ሰዎች መካከል አምስቱ #ከዱባይ የመጡና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ ናቸው።

- አንድ የዘጠኝ (9) ወር ህጻንና ወላጅ እናቱ ይገኙበታል።

- አንድ የ25 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊት ከታይላንድ መጥታ በለይቶ ማቆያ ክትትል ስታደርግ የነበረች በቫይረሱ መያዟ ተረጋግጧል።

- አንድ የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊ የውጭ አገር ጉዞ ታሪክ #የሌለው ሲሆን የንክኪ ሁኔታውም በመጣራት ላይ ይገኛል። ወጣቱ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳለው ተጠርጥሮ በለይቶ ማቆያ የነበረ ነው።

- ሌላኛዋ የ30 ዓመት ሴት ኤርትራዊት ስትሆን ከእንግሊዝ ለንደን መጥታ በአዲስ አበባ በለይቶ ማቆያ ክትትል እያደረገች የምትገኝ ናት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 2271
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 264
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 8
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ያሉ - 44
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 1
• ያገገሙ - 4
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 2
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 52

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ስምንቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ግለሰቦች፦

• ታማሚ 1 - የ9 ወር ህፃን ኢትዮጵያዊ ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የነበረው።

• ታማሚ 2 - የ36 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ ያለ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የነበረው።

• ታማሚ 3 - የ33 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ ያለ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የነበረው።

• ታማሚ 4 - የ38 ዓመት ኢትዮጵያዊት ከዱባይ የመጣችና በለይቶ ማቆያ የነበረች፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የነበራት።

• ታማሚ 5 - የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ ያለ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያልነበረው።

• ታማሚ 6 - የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊት ከታይላንድ የመጣችና በለይቶ ማቆያ የነበረች፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያልነበራት።

• ታማሚ 7 - የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊ ምንም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌለው፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የነበረው።

• ታማሚ 8 - የ30 ዓመት ኤርትራዊት ከዩናይትድ ኪንግደም፣ ለንደን የመጣችና በለይቶ ማቆያ የነበረች፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላት።

#ETHIOPIA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኬንያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 172 ደረሱ!

የኬንያ ጤና ሚኒስቴር መግለጫ እየሰጠ ይገኛል። በሀገሪቱ ተጨማሪ አስራ አራት (14) ሰዎች በቫይረሱ በመያዛቸው አጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 172 መድረሳቸውን ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በኬንያ 696 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 14 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው ተረጋግጧል። አስራ ሁለቱ (12) የኬንያ ዜጎች ሲሆኑ ሁለቱ (2) የውጭ ሀገር ዜጎች ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#KENYA

በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት ሶስት (3) ታማሚዎች ከበሽታው በማገገማቸውና በተደረገላቸው ምርመራም ውጤታቸው ነፃ [ኔጌቲቭ] መሆኑ በመረጋገጡ ከህክምና ማዕከል እንዲወጡ መደረጉን የኬንያ ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅቡቲ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 121 ደረሱ!

በጅቡቲ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 450 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሰላሳ አንድ (31) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በሀገሪቱ ያሉ አጠቃላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች አንድ መቶ ሀያ አንድ (121) ደርሰዋል።

በተጨማሪ በጅቡቲ ከኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አስራ ስምንት (18) የደረሰ ሲሆን እስካሁን በሀገሪቱ ምንም ሞት አልተመዘገበም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለሥራ ፈላጊዎች የወጣ የቅጥር ማስታወቂያ!

በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ጤና ቢሮ ለጤና ባለሞያዎች የCOVID-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የኮንትራት ቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል።

• በህክምናና በጤና ሙያ ዘርፍ ተመርቃችሁ ወደ ስራ ያልተሰማራችሁ ፦

- አጠቀላይ ሀኪም
- የጤና መኮንን
- የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ባለሞያ
- ነርስ

• ብዛት - 602

የምዝገባ ሂደት በተከታዩ ኢሜል ፦ [email protected]

የምዝገባ ቀን ፦ ከመጋቢት 29/2012 ዓ/ም - ሚያዚያ 6/2012 ዓ/ም

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኬንያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦

• በቫይረሱ የተያዙ ታማሚዎች ብዛት - 172
• ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ያገገሙ - 7
• ህይወታቸው ያለፈ - 6

በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት 3 ሰዎች ከሽታው አገግመዋል። በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዘው በእድሜ ትንሹ ህመምተኛ የ2 ዓመት ህፃን ሲሆን በእድሜ ትልቁ ደግሞ የ72 ዓመት አዛውንት ናቸው።

ምንጭ፦ የኬንያ ጤና ሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች ፦

- ባለፉት 24 ሰዓት ስፔን 743 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 13,798 ደርሷል።

- በእንግሊዝ ባለፉት 24 ሰዓት 758 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 5,655 ደርሷል።

- በስውዲን የሟቾች ቁጥር ወደ 591 ከፍ ብሏል።

- ጠ/ሚ ቦሪስ ጆንሰን አሁንም በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ቢገኙም ሁኔታቸው ጥሩ እንደሆነ ተሰምቷል።

- በኢራን ባለፉት 24 ሰዓት 133 ተጨማሪ ሰዎች ሞተዋል። በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 3,872 ደርሷል።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ1.3 ሚሊዮን በልጧል። ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከ291,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል። ከ75,000 በላይ ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኦሮሚያ ክልል የኮቪድ-19 ምርመራ ተጀመረ!

በኦሮሚያ ክልል የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መጀመሩን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል። የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መንግስቱ በቀለ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በአዳማ ከተማ በተደራጀዉ ላቦራቶሪ ከዛሬ ጀምሮ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማከናወን መጀመሩን አሳውቀዋል።

ምንጭ፦ ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ /OMN/
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ፦

- በኬንያ 696 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 14 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በጅቡቲ 450 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 31 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በኢትዮጵያ 264 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 8 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
CGTN AFRICA በሰበር ዜናው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሶስት (3) የበረራ ሰራተኞች በኮሮና ቫይረስ እንደተያዙና ፤ በጤና ሚንስቴር ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ መናገራቸውን ዘግቧል። የዜና ማሰራጫው በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UGANDA

በዩጋንዳ ለሁለተኛ ቀን አዲስ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ኬዝ እንዳልተመዘገበ የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ባለፉት 24 ሰዓት 150 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁሉም ከኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል።

ትላንት የ231 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁሉም ከኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ነፃ ሆነው መገኘታቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ወረርሽኝ ስርጭት መከላከልን ምክንያት በማድረግ በኦሮሚያ ክልል 13 ሺህ 231 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲለቀቁ ተወስኗል።

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስራ አስፈፃሚ ዛሬ ከሰጡት መግለጫ ፦

- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቫይረሱ በፈጠረው ተጽእኖ ሳቢያ 550 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አጥቷል።

- አየር መንገዱ አሁን ላይ 90% የውጭ በረራዉን ቀንሷል።

- ከ110 መዳረሻዎች የ91 መዳረሻዎች በረራዎችን ቀንሶ በ19 መዳረሻዎች ብቻ እየሰራ ነው።

- የጭነት አገልግሎቱ እና የአውሮፕላን ጥገና ክፍሉ አሁን ላይ ጥሩ እየሰሩ ነው።

- ከቋሚ ሰራተኞች ውጭ ያሉ ሰራተኞች ለጊዜው እንዲያቆሙ ተደርጓል።

- ቋሚ ሰራተኛ ላይ የተደረገም ሆነ የታሰበ ቅነሳ የለም።

- ሌሎች አየር መንገዶች በሃገራት እየተደጎሙ ነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን ፈተናዉን በራሱ ለመወጣት እየጣረ ነው።

ምንጭ፦ አል አይን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ እስካሁን በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] መያዛቸው ከተረጋገጠ 52 ሰዎች መካከል ሶስቱ (3) የአየር መንገዱ ሰራተኞች ሲሆኑ ከእነርሱም አንዷ ማገገሟን አቶ ተወልደ ገ/ማርያም መግለጻቸውን ሲጂቲኤንን ጠቅሶ አልዓይን ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ITALY

የሟቾች ቁጥር ትላንት ከተመዘገበው ቀንሷል። ባለፉት 24 ሰዓት የተመዘገበው የሟቾች ቁጥር 606 ሲሆን አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 17,127 ደርሷል።

በሌላ በኩል በጣልያን ተስፋ ሰጪ ምልክቶች እየታዩ ነው። አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መጥቷል። ባለፉት 24 ሰዓት ሪፖርት የተደረገው 3,039 ኬዝ ነው።

ባለፉት 24 ሰዓት በጣልያን ፦

- የሟቾች ቁጥር ቀንሷል።
- አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎችም ቀንሷል።
- የፅኑ ህሙማን ቁጥር ቀንሷል።
- ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የሚወጡ ጨምረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በድሬዳዋ የህዝብ ትራንስፖርት በፈረቃ ሊጀምር ነው!

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከሚያዝያ 1/2012 ዓ.ም ጀምሮ ተቋርጦ የነበረው የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በፈረቃ ሊጀመር እንደሆነ ተገልጿል።

ከተማ አስተዳደሩ እዚህ ውሳኔ የደረሰው በህብረተሰቡ ውስጥ እየተከሰተ እና ወደፊት ሊከሰት የሚችለውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ከግምት በማስገባት እንደሆነ ተሰምቷል።

በድሬዳዋ 'የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት' እንዲቀጥል የሚደረገው የተለያዩ አስገዳጅ ደንብ እና መመሪያዎችን በማውጣት ነው።

ደንብ እና መመሪያዎቹን በ @tikvahethmagazine ማንበብ ትችላላችሁ። መረጃው የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት #በሩዋንዳ 806 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁሉም ከኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia