TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHIOPIA #GERMANY

ኢትዮጵያና ጀርመን የ2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የእርዳታ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ገንዘቡ በኢትዮጵያ ያለውን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ለማሳደግ፣ የስራ ፈጠራን ለማስፋት እንዲሁም ከስደት የተመለሱ ዜጎችን ለማቋቋም ይውላል ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያና የጀርመን ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱ በፊርማው ሥነ ሥርዓት ላይ ተገልጿል፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Germany #Ethiopia

ጀርመን ለኢትዮጵያ የ352.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ለገሰች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት የጀርመን የኢኮኖሚያዊ ትብብር ሚኒስትር ዶ/ር ገርድ ሙለርን እና የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ሁበርተስ ሄሊን በእንግድነት ተቀብለዋል። በተጨማሪም የጀርመን መንግሥት የግብርናን ዘዴ ለማሻሻል ይረዳ ዘንድ 144 የግብርና መሣሪያዎችን ከነመለዋዎጫቸው ለግሷል።

#PMOEthiopia
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Germany #Ethiopia

ጀርመን በኢትዮጵያ የምታከናውነውን የልማትና የድጋፍ ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች።

የጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና የልማት ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዩርገን ሃርት ለዶይቼ ቨለ ሬድዮ በሰጡት ቃል ፥ በኢትዮጵያ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ድጋፍ የሚያስፈልገው ህዝብ ቁጥር አሻቅቧል ብለዋል።

በመሆኑም የጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና የልማት ሚኒስቴር ከለጋሽ አገራትና ከአውሮጳ ኅብረት ጋር በመቀናጀት በኢትዮጵያ የጀመረውን የልማት ትብብር የሚቀጥል ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል።

ዮርገን ሃርት የጀርመን መንግሥት በኢትዮጵያ ለሚያከናውናቸው ሥራዎች የ100 ሚልዮን ዩሮ የልማት ትብብር በጀት መመደቡ አስታውሰው ፥ “አሁንም ዓላማችን የአገሪቱን ህዝብ በተቻለን መጠን ተንቀሳቅሰን መደገፍ ነው” ብለዋል።

አፍሪካና ጀርመንን በንግድ፣ ኢንቨስትመንትና በግሉ ኢኮኖሚ ዘርፍ የሚያስተሳስረው የ (Compact with Africa) መርሃ ግብር አባል የሆነችው ኢትዮጵያ የጀርመን የልማት ትብብር ከፍተኛ ተጠቃሚ አገር ናት።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ/ENA

@tikvahethiopia
#Germany

ኦላፍ ሾልስ የጀርመን መራኄ መንግሥት ሆነው ተመረጡ።

የ63 ዓመቱ ሾልስ በፖለቲካ አቋማቸው ሶሻል ዴሞክራት ናቸው።

በምርጫው ከፍተኛ ድምፅ ካገኙት ከአረንጓዴ ፓርቲ እና ከነጻ ዴሞክራቶች ፓርቲዎች ጋር በመቀናጀት ሀገራቸውን ለመምራት ተስማምተዋል።

ሾልስ ዛሬ በጀርመን ምክር ቤት በተካሄደው ምሥጢራዊ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ከ707 አባላት የ395ቱን በማግኘት ኦላፍ ሾልስ አዲሱ የጀርመን መሪ ሆነው ተመርጠዋል።

እንዲያም ሆኖ የተጣማሪ ፓርቲዎቹን አባላት ሙሉ ድምፅ አላገኙም። በምርጫው ሂደት 303 አባላት ተቃውመዋል፤ ስድስት የምክር ቤት አባላት ደግሞ ድምፅ አልሰጡም።

ከድምፅ አሰጣጡ ሥርዓት በኋላ ወደ ፕሬዝደንቱ መኖሪያ በመሄድ የሹመት ደብዳቤያቸውን ተቀብለዋል።

ዛሬ ከፕሬዝደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር የመራኄ መንግሥትነት ሥልጣናቸውን የተቀበሉት ሾልስ ወደ ምክር ቤት በመሄድ ቃለመሃላ ፈጽመዋል።

የካቢኔ አባሎቻቸውን በማቅረብም አዲስ ሚኒስትሮቻቸውን በይፋ ሰይመዋል።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ

@tikvahethiopia
#Germany #Ethiopia

የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር አውር ስቴፓን ጋር ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ስቴፓን በውይይቱ ወቅት ጀርመን ለኢትዮጵያ የ80 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ እንደምታደርግ ይፋ አድርገዋል፡፡

የገንዘብ ድጋፉ ኢትዮጵያ ለምታከናውናቸው ፦
- የምግብ ዋስትና ፕሮግራም፣
- ለመልካም አስተዳደር፣
- ለመሬት አጠቃቀም፣
- ለግብርና ሜካናይዜሽን እንዲሁም ድርቅን ለመቋቋም ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ይውላል ተብሏል፡፡

ምንጭ ፦የገንዘብ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#Russia #Poland #Germany

አዲስ አበባ ያለው የሩስያ ኤምባሲ ያሰራጨው መልዕክት መነጋገሪያ ሆኗል፤ በኤምባሲዎች መካከልም ውዝግብ ፈጥሯል።

የሩስያ ኤምባሲ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ለሩስያ ድጋፋቸውን የሚገልፁ በየዕለቱ ብዙ ደብዳቤዎች ፣ በመቶዎች የሚቆጠር አስተያየት እንደሚደርሰው ገልጿል።

ይህ መልዕክት እየደረሰው ያለው ከገፁ ተከታዮች መሆኑን አመልክቷል።

ኤምባሲው " ሀገሮቻችን በችግር ጊዜ በመደጋገፍ እና በመረዳዳት እንደዚህ አይነት ጠንካራ ፣ ረጅም ጊዜ የሚቆይ ፣ ወዳጃዊ ግንኙነት ስላላቸው ኩራት ይሰማናል " ብሏል።

አክሎም " ልክ አያቶቻችን ከ80 ዓመታት በፊት እንዳደረጉት ናዚዝምን እየተዋጋን ባለንበት በአሁን ጊዜ ያሳያችሁን ድጋፍ እና ከሩስያ ጎን ለመቆም ስለመረጣችሁ በእጅጉ እናደንቃለን " ብሏል።

የሩስያ ኤምባሲ ይህንን መልዕክት ካሰራጨ በኃላ የሌሎች ሀገራት ኤምባሲዎች ምላሽ ሰጥተዋል ፤ ምላሽ ከሰጡት መካከል የፖለንድ ኤምባሲ አንዱ ነው።

ፖላንድ ኤምባሲ ፤ ሩስያ የሀሰተኛ መረጃ እያሰራጨች ነው ሲል ወቅሷል።

ኤምባሲው " የናዚ መስፋፋት የጀመረው በ1939 በፖላንድ ላይ በተደረገ ሕገ-ወጥ ወረራ ነው ፤ በወቅቱም ሞስኮ እንደ አጋር ነበረች ብሏል።

" ሩስያ በዩክሬን ላይ ከፈፀመችው ህገ-ወጥ የሆነ ጥቃት ጋር በተያያዘ ፤ ማን ከናዚዎች ጋር መነፃፀር እንዳለበት ሁለት ጊዜ ማሰብ ይገባል " ሲል ኤምባሲው ገልጿል።

ሌላው ለሩስያ ኤምባሲ ምላሽ የሰጠው የጀርመን ኤምባሲ ሲሆን ኤምባሲው በጉዳዩ ዙሪያ ዝም ሊል እንደማችል ገልጿል።

" ናዚዝም " ን እንዋጋለን በሚል ሉዓላዊ ሀገርን መውረር ፣ ሰላማዊ ዜጎችን እና ሆስፒታሎችን ማፈንዳት (ልክ ትላንት በማሪፖል በሚገኘው የእናቶች እና ህፃናት ሆስፒታል እንደተደረገው) የሚያሳዝን እና የሀሰተኛ መረጃ ማሳያ ነው ብሏል።

ይህ ጦርነት " ናዚዝም " ን ለመዋጋት እንዳልሆነ ይታወቃል ያለው የጀርመን ኤምባሲ ጦርነቱ ለአምባገነን ስርአቶች ትልቁ ፈተና እና ስጋት የሆነውን ዲሞክራሲን፣ የፕሬስ ነፃነትን እና የህዝብ ድምጽን መዋጋት ነው ብሏል።

ኤምባሲው ፤ " የሩሲያ ታንኮች ሰላም ፣ ውሃ ወይም ምግብ አያመጡም ፤ መከራ እና ጥፋት ብቻ ነው የሚያመጡት " ብሏል።

@tikvahethiopia
#Germany #Ethiopia

ጀርመን በኢትዮጵያ መንግሥት ጥያቄ ከቀረበላት አገራዊ የምክክር ሂደቱን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን አሳውቃለች።

ሀገሪቱ ይህን ያሳወቀችው ኢትዮጵያ በሚገኙት አምባሳደሯ ነው።

በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፋን አወር ለኢዜአ በሰጡት ቃል ፤ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር የአገሪቷን መሰረታዊ ችግሮች ለመፍታት ጥሩ የመፍትሔ አማራጭ ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ጥያቄ ከቀረበላት የፌዴራል ስርዓት የምትከተለው ጀርመን በሚቻለው አቅም ሁሉ አገራዊ የምክክር ሂደቱን ለመደገፍ ዝግጁ ናት ሲሉ አረጋግጠዋል።

" በኢትዮጵያ የሚስተዋሉትን ውስጣዊ ችግሮች በመፍታት መፍትሔ ለማበጀት በጋራ መምከር ያስፈልጋል " ያሉት አምባሳደሩ " ኢትዮጵያ የምታካሂደው አገራዊ ምክክር ሁሉንም አሳታፊና አካታች ሆኖ ሲካሄድ ልዩነቶችን በመነጋገርና በመፍታት በቀላሉ ብሔራዊ መግባባት መፍጠር ያስችላል " ብለዋል።

በአገራዊ ምክክሩ ለጋራ ችግሮች መንስኤ የሆኑ ጉዳዮች ምንድን ናቸው? የሚለውን ቁልፍ ጥያቄ በማንሳትና በግልጽ መነጋገር የጋራ መፍትሔ ማምጣት ይቻላል ሲሉም አክለዋል።

አምባሳደር ስቴፈን ፤ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የምክክር ሂደቱን ሁሉን አቀፍ ለማድረግ እየሰራ መሆኑ የሚደነቅ ነው ብለዋል።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Germany

• ጀርመን ከWFP መጋዘን ህወሓት የፈፀመውን በኃይል የነዳጅ ክምችት የመውሰድ ድርጊት " አፀያፊ " ስትል አወገዘች።

የጀርመን መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ ለ5 ወራት የዘለቀው የተኩስ አቁም ስምምነት መጣሱና ጦርነቱ እንደገና መጀመሩ በእጅጉ እንዳሳዘነው ገልጿል።

በግጭቱ ውስጥ ያሉ ሁሉም አካላት አሁኑኑ መሳሪያቸውን አስቀምጠው ወደ ተኩስ አቁም በፍጥነት መመለስ አለባቸው ብሏል።

" ግጭቱ ሊፈታ የሚችለው በድርድር ጠረጴዛ ዙሪያ ብቻ ነው " ያለው የጀርመን መንግስት የአፍሪካ ህብረት የማሸማገል ጥረቶችን አሁንም መደገፉን እንደሚቀጥል እና ይህም ስራ አሁን መጠናከር እንዳለበት ገልጿል።

የትግራይ፣ የአማራ እና የአፋር ህዝብ በቂ ስቃይ ደርሶበታል ያለው የጀርመን መንግስት ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ በጣም ብዙ ንፁሃን ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል ወይም ለከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሰለባ ሆነዋል ብሏል።

ግጭቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ተገደዋል ፤ ሚሊዮኖችም በረሃብ እየተሰቃዩ ነው ሲል የጀመን መንግስት ገልጿል።

ከዚህም ዳራ አንፃር ህወሓት (TPLF) አስቸኳይ ህይወት አድን ሰብአዊ እርዳታን ለማከፋፈል የሚውልን ነዳጅ መውሰዱ " አስጸያፊ ነው " ስትል አውግዛለች።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #Germany

ዛሬ የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሹልዝ  አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ኦላፍ ሹልዝ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ነው።

ከእሳቸው ጋር የጀርመን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ ባለሀብቶች ፣ የተቋማት መሪዎች እንዲሁም በርከት ያለ የልዑካን እንደሚመጡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

ለጀርመኑን መራሄ መንግሥት አቀባበል ለማድረግ ከቦሌ ኤርፖርት ጀምሮ ያለው መንገድ ዝግጁ መደረጉን ተዘዋውረን ለመመልከተ ችለናል።

@tikvahethiopia