TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና‼️

በደጀን ዙሪያ ወረዳ በደረሰ #የመኪና_አደጋ የሰዎች ህይዎት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። አደጋው የደረሰው በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ዙሪያ ወረዳ ነው።

ዛሬ ጠዋት #የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን አሳፍሮ ከደብረ ታቦር ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከቆመ ሲኖ ትራክ ጋር በመጋጨቱ ነው አደጋው የተከሰተው። በዚህም #የሁለት_ተማሪዎች ህይዎት ወዲያውኑ አልፏል።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳው ለአብመድ እንደተናገሩት ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ተጎጅዎች ወደ ደጀን እና ደብረ ማርቆስ ሆስፒታሎች ተወስደው እገዛ እየተደረገላቸው ነው።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia