TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አርበኞች ግንቦት 7⬇️

የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች ከመስከረም 5/2011 ጀምሮ #መቀሌ#አዳማና #አዲስ አበባን ጨምሮ በ32 ከተማዎች ሕዝባዊ ስብሰባ እንደሚያካሂዱ ተገለጸ፡፡

ከአቀባበል ኮሚቴ በተገኘው መረጃ እሁድ ጳጉሜ 4/2010 ብርሀኑ ነጋን (ፕ/ር) ጨምሮ አመራሮቹ ኢትዮጵያ እንደገቡ በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሕዝቡ ንግግር ያደርጋሉ፤ የስታዲየሙ ንግግር በኢሳትና ሌሎች ቴሌቪዥን ጣቢያዎች #በቀጥታ ይተላለፋል ተብሏል፡፡ በስታዲየሙ የሚገኘውን የሕዝብ መጨናነቅ ለመቀነስ በመስቀል አደባባይ በስክሪን ንግግሩ ይተላለፋል፡፡

መስከረም 6 እና 7 በባሕርዳር እና ጎንደር፣ መስከረም 12 በአዳማ አመራሮቹ የሚገኙበት ሕዝባዊ ትዕይንት ከተካሄደ በኋላ በተከታታይ ቀናት #በመቀሌ#ወልዲያ#ደሴ እና #አምቦ ተመሳሳይ ፕሮግራም ይኖራል፡፡

ንቅናቄው አቀባበሉን በተመለከተ ትናንት በሰጠው መግለጫ “በዕለቱ ሥነ ሥርዓት ለማስከበርና የሕዝብን ደሕንነት ለመጠበቅ ከተሰማሩ የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ታሪካዊ የአቀባበል በዓሉ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲካሄድ” ጥሪ አቅርቧል፡፡

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🎂TIKVAH ETHIOPIA~2 ዓመት🎂

#ደብረ_ብርሃን #ወሎ #ጅማ #ሀረማያ #ሀዋሳ #ወልቂጤ #መቐለ #ወልዲያ #ወላይታ_ሶዶ #አርባምንጭ #ሆሳዕና/#ዋቸሞ/

📎የሰውልጅ በሰውነቱ የሚከበርበት፤ የግለሰቦች አመለካከት፣ እምነት፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ የኔ ነው የሚሉት ሁሉ የሚከበርበት፤ ፍቅር፣አንድነትና መተባበር የነገሰበት፣ የሰው ልጅ ሁሉ መሰብሰቢያ የሆነች ከጥላቻ የራቀች ሀገር እንገነባለን!! ተባብረን እንሰራለን፤ ለመጭው ትውልድ ኢትዮጵያን እናወርሳለን!!

እኛ ስንኖር ኢትዮጵያ ትኖራለች፤ ኢትዮጵያ ስትኖር እኛም እንኖራለን!

#ድፍን_ሁለት_ዓመት_በፍቅር_በመተባበር!

ነገ 6:00 አበበች ጎበና የህፃናት እንክብካቤ እና ልማት ድርጅት እንገናኝ፤ ከእናታችንም ምርቃት እንቀበል!! ሁላችሁም የዚህ ገፅ ባለቤቶች ናችሁ!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የTIKVAH-ETH #የStopHateSpeech ሀገር አቀፍ ዘመቻዎች/በዩኒቨርሲቲ ደረጃ/ና በየተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ውስጥ የተደረጉ ጉብኝቶችን ለመከታተል #የዩትዩብ ቻናላችንን ይጎብኙ!

#ሀረማያ #ጅማ #ወልቂጤ #ሀዋሳ #ወላይታ_ሶዶ #አርባምንጭ #መቐለ #ዋቻሞ #ወሎ #ደብረብርሃን #ወልዲያ

Watch ""የአንድ እናት ልጆች ነን" በመቐለ ዩኒቨርሲቲ #TIKVAH_ETHIOPIA" on YouTube
https://youtu.be/qjyt56okb3U
የዛሬ የህዳር 10/2012 ዓ/ም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባልት እና ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተሰባሰበ መረጃ👇
https://telegra.ph/ETH-11-20-4

(TIKVAH-ETHIOPIA)

#ድሬዳዋ #ሀረማያ #ወልዲያ #መቱ #ASTU
#መደወላቡ #ባህርዳር #ደባርቅ #ደብረታቦር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው ..

- ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣
- የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ
- የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ
- ወልዲያ
- ሪፍትቫሊ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች በዛሬው እለት እያስመረቁ ነው።

#ባህርዳር_ዩኒቨርሲቲ

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 363 ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።

ተማሪዎቹ በመደበኛ፣ በተከታታይ እና በክረምት መርሐ-ግብሮች፤ በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ ዲግሪ፣ በሶስተኛ ዲግሪ እና የስፔሻሊቲ ህክምና የሰለጠኑ ናቸው።

#አሶሳ_ዩኒቨርሲቲ

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 237 ተማሪዎችን ነው በማስመረቅ ላይ የሚገኘው።

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ለ8ተኛ ጊዜ ሲሆን የዛሬዎቹ ተመራቂዎች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ የሰለጠኑ ናቸው።

#የኢትዮጵያ_ሲቪል_ሰርቪስ_ዩኒቨርሲቲ

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲም በተለያየ የትምህርት መስኮች በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሐ-ግብሮች ያሰለጠናቸውን ከ2 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።

ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ ሁለተኛ ዲግሪ እና በፒ.ኤች.ዲ የተማሩ ናቸው።

ከእለቱ ተመራቂዎች ውስጥ 153 የሚሆኑት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን በውጭ ግንኙነት ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የሰለጠኑ እጩ ዲፕሎማቶች ናቸው።

#ወልዲያ_ዩኒቨርሲቲ

ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2,537 ተማሪዎችን አስመርቋል።

#ሪፍትቫሊ_ዩኒቨርስቲ

የሪፍትቫሊ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ ትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 16, 967 ተማሪዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም አስመርቋል።

መረጃው የetv ነው።

@tikvahethiopia
#ወልዲያ

የወልዲያ ከተማ ሰላም መሆኗን የከተማ አስተዳደሩ አሳውቋል።

በፀጥታ ስጋት ምክንያት ከተማይቱን ለቀው ወደአጎራባች ከተሞች የሄዱ ዜጎች መኖራቸው የታወቀ ሲሆን የከተማ አሰተዳደሩ ነዋሪዎቹን ለመመለስ እንደሚሰራ ገልጿል።

በአሁን ሰዓት በከተማዋ ምንም የተለየ የፀጥታ ችግር እንደሌለ የተገለፀ ሲሆን የከተማው የፀጥታ ኃይል እና ወጣት በቀንና በማታ ጥብቃ እያደረጉ መሆኑን ለማወቅት ተችሏል።

በተለይም በከተማው የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣ የመግቢያ እና መውጫ ኬላዎች ፍተሻና ጥበቃ እየተደረገ ነው።

በፕሮፖጋንዳ እና በሀሰተኛ መረጃ ምክንያት አካባቢያቸውን ለቀው የወጡ ሰዎች ወደቤታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ከሄዱበት ከተማ ጋር ንግግር እየተደረገ ይገኛል።

ሁሉም የከተማው ነዋሪው አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ እና ከሀሰተኛ መረጃ እና አሉባልታ እራሱን እንያቅብ ጥሪ ቀርቧል።

በአሁን ሰዓት የሀገር መከላከያ፣ የአማራ እና የሌሎች ክልል ልዩ ኃይሎች በጋራ በጉባላፍቶ ወረዳ እና በራያና ቆቦ ወረዳ አካባቢ ግዳጅ ላይ ተሰማርተው ስምሪት ወስደው ትግል ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

እስካሁን ባለው ሁኔታ ወደከተማው እየቀረበ ያለ የተለየ ሁኔታ እንደሌለ እና ሰላማዊ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ መቀጠሉን የወልዲያ ከተማ አስተዳደር አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ወልዲያ

• ንግድ ፍቃድ ያላሳደሳችሁ አሳድሱ ፤ ጊዜው ካለፈ 20 ሺህ ብር ቅጣት ትከፍላላችሁ።

በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የንግድ ስራ ፈቃዳቸውን ባላሳደሱ ነጋዴዎች ላይ በአዋጁ የተቀመጠውን የገንዘብ ቅጣት ተግባራዊ እንደሚያደርግ የወልዲያ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ።

ታህሳስ 30 2014 ዓ.ም ለማጠናቀቅ የታቀደው የንግድ ፈቃድ እድሳት ሰራ በአካባቢው በነበረው የሰላም እጦት ምክኒያት ወደ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም አራዝሞ የለምንም ቅጣት አገልግሎቱን እየሰጠ እንደሚገኝ የግለፀው ፅ/ቤቱ ከሃምሌ1 ቀን 2014 ዓ.ም በኃላ ለማሳደስ የሚመጡ ነጋዴዎች በአዋጁ መሰረት 20 ሸህ ብር ቅጣት እንደሚከፍሉ አሳስቧል።

በተያዘው ዓመት 6 ሽ 101 ነጋዴዎች ፈቃዳቸውን እንዲያሳድሱ ታቅዶ እስካሁን 4 ሽህ 248ቱ ብቻ ማሳደሳቸውን የተገለፀ ሲሆን በተለያዩ ምክኒያቶች ያላሳደሱ ነጋዴዎች በከተመዋ በሚገኙ 3 የንግድ ማዕከላት በመገኘት እንዲያሳድሱ ጥሪ ቀርቧል።

መረጃው የወልዲያ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia