TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ተጨማሪ 11 ሆቴሎች ተለይተዋል!

ከውጭ ሀገር ለሚገቡ መንገደኞች ለ14 ቀናት ማረፊያ የሚያገለገሉ ተጨማሪ 11 ሆቴሎች መለየታቸውን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

ሆቴሎች በድምሩ ከአንድ ሺህ በላይ አልጋ እንደሚያቀርቡ የተገለጸ ሲሆን በጤና ሚኒስቴር ባለሙያዎች ክትትል ይደረግላቸዋል ተብሏል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

ከነገ መጋቢት 19/2012 ዓ/ም ጀምሮ በትግራይ ክልል ውስጥ ከከተማ ወደ ከተማ መንቀሳቀስ አይፈቀድም። ከገጠር ወደ ገጠር፣ እንዲሁም ከገጠር ወደ ከተማ ወይም ከከተማ ወደ ገጠር መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው። ከነገ ጀምሮ ባለንበት ቦታ ነው የምንቀመጠው።

#DrDebretsionGebremichael #TigraiTV
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

ወደ ትግራይ የሚያስገቡ ዋና መንገዶች አይዘጉም። ነገር ግን ክትትል እና ቁጥጥር ይደረግባቸዋል። አንድ ሰው መቐለ ገብቶ ወደ አዲግራት ወደ አድዋ ወይም ወደ ሽሬ መሄድ የሚባል ጉዳይ አይኖርም። በአንድ መስመር ሰው ከገባ እዛው ቦታ ብቻ ነው መቀመጥ ያለበት። መንቀሳቀስ አይፈቀድም። ይህንን አዎቆ ነው ወደ ትግራይ መግባት የሚቻለው።

#DrDebretsionGebremichael #TigraiTV
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

"በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የተጠረጠረ ማንኛውም ግለሰብ 'የመመርመር ግዴታ' ተጥሎበታል። በተጨማሪ አንድ ሰው ተጠርጥሮ አልያም ተመርምሮ ቫይረሱ ከተገኘበት ወደ ማቆያ አልገባም ማለት አይችልም፤ በህግም የተከለከለ ነው። ቤቴ ነው ምቆየው ፣ የፈለኩበት ሆስፒታል ነው ምቆየው ፣ የሚባል ነገር አይሰራም " - አቶ አማኑኤል አሰፋ (የትግራይ ክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ASMERA

በኤርትራ ከቦታ ቦታ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እና መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት ታግደው አስመራ ይህን መስላ ውላለች።

የዝዉዉር እገዳዉ እና የመደበኛ ትምህርት (ከህፃናት መዋያ እስከ ኮሌጆች) መቋረጡ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የሚደረገው ጥረት አካል ነው።

የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት የሁሉም ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እንዲሁም ከቦታ ቦታ የሚደረግ ዝውውር ላልተወሰነ ግዜ ታግዷል። ትእዛዙን የሚጥስ ቅጣት ይጠብቀዋል። እገዳው በተመሳሳይ አዋጅ እስካልተሻረ ድረስ ስራ ላይ ይቆያል።

PHOTO : AHMEDIN MOHAMMED

[የኤርትራ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ DW]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በመጨረሻም መልዕክት ለቲክቫህ አባላት፦

#FightCOVID19

እያንዳንዳችን #ጦርነት ላይ እንደሆንን አምነን መቀበል ይኖርብናል። መዘናጋት የህይወት ዋጋ ነው የሚያስከፍለን። የኛ ጤና መሆን የምንወዳቸው፣ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ሁሉ ጤና መሆን ነው። የምናደርገውን በመጠንቀቅ እናድርግ። በጤና ባለሞያዎች የሚሰጠውንም ትዕዛዝ እናክብር!

ኮሮና ቫይረስ እስካሁን መድሃኒት አልተገኘለትምና በተሳሳቱ አረዳዶች ተዘናግተን ጦርነቱን እንዳንሸነፍ፣ እጃችንንም ለኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] እንዳንሰጥ አደራ! አደራ!

መንግስት ለህዝብ የሚሰጣቸው መረጃዎች ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ በዚህ አጋጣሚ እናስገነዝባለን። የሚሰጡት መረጃዎችም ወቅታቸውን የጠበቁ ቢሆን መልካም ነው።

ጦርነቱን ከፊት ሆነው ህይወታቸውን ሰጥተው የሚመሩት፣ የሚታገሉና የሚያታግሉት የጤና ባለሞያዎቻችን አስፈላጊው ሁሉ የህክምና ቁሳቁሶች እንዲሟላላቸው ካልተደረገ እጅግ በጣም ከፍተኛ ዋጋ መክፈላችን አይቀርምና ይታሰብበት!

ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኝላችኃለን!
ሰላም እደሩ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እንደምን አረፈዳችሁ?

በ10,000 ሺህ የሚቆጠሩ በ @tikvahethiopiaBot የተከማቹ መልዕክቶችን እየተመለከትን ነበር። ከመላው ሀገሪቱ ክፍል ማለት ይቻላል።

ትላንት ምሽት 'ሻይቅጠል በጥብጣችሁ ጠጡ፣ የሻይቅጠል ፈልጋችሁ በስኴር አድርጋችሁ ጠጡ' ለኮሮና መድሃኒት ነው ተብለን ነበር የሚሉ መልዕክቶችን ተመልክተናል።

እውነቱ ግን ብቸኛ የአሁኑ መፍትሄ የጤና ባለሞያዎችን ምክር መስማት ብቻ ነው። በተለያየ መልኩ በሚደርሳችሁ መልዕክቶች ሁሉ የምትረበሹ ከሆነ ይህን የኮሮና ቫይረስ መቆጣጠር ፍፁም አዳጋች ነው የሚሆነው።

#ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት የሚደረጉ ጥረቶች ቢደነቁም እውነታው ግን ኮሮና ቫይረስ መድሃኒት የሌለው ገዳይ ወረርሽኝ መሆኑ ነው። መድሃኒት ቢገኝለት የሁላችን ደስታ ነው ፤ ግን መድሃኒት የለውም ፤ አልተገኘለትም! ከበሽታው የምንተርፈው በጤና ባለሞያዎች ምክር ብቻ ነው።

መዘናጋት ከምንነግራችሁ በላይ ትልቅ ዋጋ ያስከፍላልና ጥንቃቄ ይደረግ። ባልተሟላ የህክምና ቁሳቁስ ፣ እራሳቸውን አደጋ ላይ ጥለው የእኛን ህይወት ለመታደግ ዝግጁ በሆኑት የጤና ባለሞያዎቻችን ላይ ስቃያቸውን እንዳናበዛ የሚሉትን እንስማ።

መልካም ቀን!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኮሮና ሀገር፣ ብሄር፣ ዘር የለውም፤ ሃይማኖት፣ ቀለም አይለይም! ከሰሞኑ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የቻይና እና አሜሪካ እርስ በእርስ መወቀቅስ አይሎ ነበር። ቻይና ቫይረሱን ያመጡብኝ የአሜሪካ ወታደሮች ናቸው ማለቷ አይዘነጋም። ለቻይና ምላሽ በሚመስል መልኩ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ይህ ቫይረስ 'የቻይና ቫይረስ' ነው ሲሉ ተደምጠዋል። ቻይና በአሜሪካ ወታደሮች ነው ሀገሬ የገባው ማለቷም አስቆጥቷቸው ነበረ።…
"ቻይናን እናከብራታለን!" - ዶናልድ ትራምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው ፕሬዘዳንት ሺ ጂፒንግ ጋር በጣም ጥሩ ንግግር አድርገናል ብለዋል።

'ከፕሬዘዳንት ሺ ጂፒንግ ጋር ብዛት ያለውን የዓለማችንን አካባቢ እያዳረሰ ሳላለው ስለኮሮና ቫይረስ በደንብ አድርገን በዝርዝር ተወያይተናል' ያሉት ዶናልድ ትራምፕ፤ 'ቻይና በወረርሽኙ ብዙ አሳልፋለችና ቫይረሱን በሚገባ ጠንቅቃ ተረድታዋለች፤ አሁን አብረን በቅርበት እየሰራን ነን፣ እናከብራታለን' ሲሉ ተደምጠዋል።

ባለፉት ገለፃዎቻቸው ግን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለቻይና ያን ያህል አክብሮት አልነበራቸውም። የወረርሽኙን አያያዟን ሲያንቋሽሹ ቫይረሱንም 'የቻይናው ቫይረስ' ብለው ሲጠሩ ነበር።

በዩናይት ስቴትስ በከባዱ በተጠቃችው ኒውዮርክ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ከ45,000 አልፏል። በየቀኑ የተያዦቹ ቁጥር ቢያንስ በ3,000 ገደማ እየጨመረ መሆኑን ነው ባለስልጣናት የሚገልፁት።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Italy

በየዕለቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በሚረግፉባት ጣልያን የ101 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ አዛውንት ከሪሚኒ ከኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] አገግመው ከሆስፒታል መውጣታቸው ተሰምቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጄኔራል ሞተርስ ለኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ታማሚዎች የሚያገለግል የመተንፈሻ መሳሪያ እንዲያመርት ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

እርምጃው አሜሪካውያንን ከኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ለመታደግ የተወሰደ መሆኑንም ፕሬዚዳንቱ የገለጹት። በአሜሪካ የመተንፈሻ አካላትን በሚያጠቃው የኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ለመታደግ የሚያገለግለው የመተንፈሻ መሳሪያ (ቬንትሌተር) እጥረት መኖሩ ይነገራል።

ይህን ተከትሎም ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኩባንያዎችና ሃገራት ይህን መሳሪያ እያመርቱና እንዲያቀርቡ ጠይቀው ነበር። ጄኔራል ሞተርስ በበኩሉ ከቀጣዩ ሚያዚያ ወር ጀምሮ በየወሩ 10 ሺህ ቬንትሌተሮችን አመርታለሁ ማለቱ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ,ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ስላሴ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሊያመጣ የሚችለውን ጉዳት ያግዝ ዘንድ በሁሉም ድርጅቶቹ ስም 1.5 ሚሊየን ብር ለግሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኒውዮርክ በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ600 በልጧል። በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥርም 46,262 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ 13 ዋና ዋና መንገዶች ላይ የፀረ ተዋህስ መድሃኒት ርጭት በነገው ዕለት ይደረጋል።

በተመረጡት መንገዶች ላይ የመከላከያ መድሃኒት ርጭት ወይንም ዲስኢንፌክት የማድረግ ስራ የሚከናወን ይሆናል።

በዚህም መሠረት፦

- መስቀል አደባባይ - ቦሌ ፣
- መስቀል አደባባይ - ጦር ሃይሎች ፣
- መስቀል አደባባይ - 6 ኪሎ ፣
- ከመስቀል አደባባይ - ጎተራ - ሳሪስ
- ከመስቀል አደባባይ - መገናኛ ፣
- ከብሄራዊ - ሜክሲኮ፣
- ከሱፐር ማርኬት - ካዛንችስ - ኡራዔል ፣
- ከምኒልክ አደባባይ - አምባሳደር - መስቀል አደባባይ፣
- ከምኒልክ አደባባይ - ፓስተር፣
- ከምኒልክ አደባባይ - 4 ኪሎ - መገናኛ፣
- ከምኒልክ አደባባይ - 6 ኪሎ ፣
- ከምኒልክ አደባባይ - አውቶብስ ተራ ፣
- ከምኒልክ አደባባይ - ተክለሃይማኖት
ያሉት መንገዶች የመድሀኒት ርጭት የሚካሄድባቸው ይሆናል።

የፀረ-በሽታ አምጭ ተዋህስ መድሀኒት ርጭት ሚካሄድባቸው መንገዶች 41 ኪሎ ሜትር የሚሽፍኑ ናቸው። በዚህ ምክንያትም የተጥቀሱት መንገዶች ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ ቀኑ 6 ሰዓት ድረስ ለአገልግሎት ዝግ የሚሆኑ ይሆናል።

#MayorOfficeAA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING ሙሳ ፋኪ መሀማት ራሳቸውን ለይቶ ማቆያ አስገቡ! የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀማት ራሳቸውን ለይቶ ማቆያ ማስገባታቸውን በትዊተር ገጻቸው ገልፀዋል። ሊቀመንበሩ ራሳቸውን 'ለይተው ለማቆየት' የወሰኑት አንድ የኮሚሽኑ ሰራተኛ በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡን ተከትሎ ነው፡፡ ሌሎች ባልደረቦቻቸውም ራሳቸውን እንደለዩ ገልጸዋል፡፡ #AlAin @tikvahethiopiaBot…
#UPDATE

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ሙሳ ፋኪ ማሃማት በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ላይ በተደረገላቸው ምርመራ ከኮሮና ቫይረስ ነጻ መሆናቸው አስታውቀዋል።

ምንም እንኳን ውጤታቸው ነጻ መሆናቸውን ቢያረጋግጥም በሚታዘዘው መሰረት ለቀጣዮቹ 14 ቀናት እራሳቸውን ለይተው እንደሚቆዩ ገልጸዋል።

የኮቪድ-19 ሽታ የተገኘበት ባልደረባቸውን ያለበት ሁኔታን በተመለከተም በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝና ሙሉ ለሙሉ እንዲሻለው ጸሎታቸው እንደሆነ ገልጸዋል።

#BBC #MoussaFakiMahamat
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሊቢያና በሶሪያ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱ አሳሳቢ ሆኗል!

የኮሮና ወረርሽኝ በጦርነት በተጎሳቆሉት ሶርያ እና ሊቢያ መሰል አገሮች የበለጠ ሊስፋፋ እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠንቅቋል።

የጤና ሥርዓታቸው ቀድሞም በደቀቀና ጦርነት በጎዳቸው አገራት በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ የድርጅቱ ምሥራቅ ሜድትራኒያን ቢሮ ዳይሬክተር አሕመድ ማንድሐሪ አስጠንቅቀዋል።

እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ በሶርያ 5 በሊቢያ ደግሞ 1 ሰው በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] መያዛቸው ተረጋግጧል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ከሶሪያው ፕሬዘዳንት በሽር አላሳድ ጋር በኮቪድ-19 ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። በዚህ ፈታኝ ወቅት UAE ከሶሪያ ህዝብ ጋር እንደምትቆም እና እገዛ እንደምታደርግ አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከ7,400 በላይ አልጋዎች ያሏቸው ሁለት ግቢዎቹን ለኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝ መከላከል ማዘጋጀቱን አስታውቋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኝ ዩኒቨርሲቲው ለለይቶ ሕክምና ምቹ እንደሆኑ ያመነባቸውን የዘንዘልማ እና ይባብ ግቢዎች 925 ክፍሎች ለዚሁ ተግባር ዝግጁ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡

ዶክተር ፍሬው እንዳሉት በእነዚህ ክፍሎች 7 ሺህ 400 ተማሪዎች የሚስተናገዱባቸው የየራሳቸው አልጋዎችና ፍራሾች፣ የጋራ የንጽሕና መጠበቂያ ክፍሎች የተሟሉ ናቸው፡፡

ዩኒቨርሲቲው ሁኔታዎችን እያየ ካሉት ሰባት (7) ግቢዎች ሌሎችንም ለመሠል ተግባር ሊያመቻች እንደሚችልም ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ!

በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ስጋት ምክንያት የተቋረጠው መደበኛው የመማር ማስተማር ሂደት በሬድዮና በድረ ገጽ ከሰኛ ጀምሮ እንደሚቀጥል የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ። ቢሮው ዛሬ እንደገለፀው የመማር ማስተማር ሂደቱ ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚያጠቃለል ነው።

ዶ/ር ገብረመስቀል ካሕሳይ የገለጹት፦

- የትምህርት ተቋማት መዘጋታቸውን ተከትሎ የተፈጠረው የመማር ማስተማር መቋረጥ በክልሉ በሚገኙ ስምንት ኤፍ ኤም ሬድዮዎች አማካኝነት ለማስቀጠል ዝግጅት ተጠናቅቋል።

- የመማር ማስተማር ሂደቱ ከመጪው ሰኞ እስከ እሁድ ባለው ጊዜ ለአንድ የትምህርት ዓይነት 20 ደቂቃ በመመደብ እንዲሰጥ ይደረጋል።

- ተማሪዎቹ በአንድ ቀን 6 የትምህርት ዓይነቶች በአጭር ሞገድ የሬድዮ ስርጭት/ኤፍ ኤም ሬድዮ /ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የጊዜ ሰሌዳ ወጥቷል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የመጀመሪያዋ በኮቪድ-19 የተያዘችው ድመት!

ይህ የSkyNews ዘገባ በዓለማችን የመጀመሪያዋ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ 'ድመት' ቤልጂየም ውስጥ እንደተገኘች ይገልፃል። ድመቷ በኮሮና ቫይረስ የተለከፈችው በባለቤቷ እንደሆነም ነው የሚያስረዳው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia