TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#COVID19

የተባበሩት መንግሥታት 'የሰብዓዊ መብቶች' ከፍተኛ ኮሚሽነር በምዕራብ ኦሮሚያ ያለው የኢንተርኔት መቋረጥ እንደሚያሳስበው ገለፀ።

ለረዥም ጊዜ ኢንተርኔትና ስልክ ማቋረጥ በተለይ ደግሞ እንደ ኮቪድ-19 ያለ ወረርሽኝ ባለበት ሰዓት ስለበሽታው የሚሰጡ መረጃዎችን ዜጎች እንዳያገኙ ያደርጋል በማለት ባለስልጣናት እንዲሁም የሕክምና ባለሙያዎች ትክክለኛ መረጃዎችን ለመስጠት እንዲችሉ አገልግሎቶቹ ክፍት እንዲሆኑ ጠይቋል።

ኮሚሽኑ በድረገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ እንዳለው ኢትዮጵያ ከታህሳስ 28/2012 ዓ/ም አንስቶ በምዕራብ ኦሮሚያ ከተሞች ከደህንነት እና ፀጥታ ጋር በተገናኘ የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት መቋረጡን በመግለጽ፤ ይህም በአካባቢው የሚኖሩ ዜጎች መረጃ እንዳያገኙ፣ እንዲሁም ከወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር እንዳይገናኙ ማድረጉን ገልጿል።

መግለጫው ኢንተርኔት የምታቋርጠው ኢትዮጵያ ብቻ አለመሆኗን በመጥቀስ ሁሉም አገራት በፍጥነት ኢንተርኔትና ስልክ ማቋረጣቸውን እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርቧል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በመላው ዓለም የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 607,239 ደርሷል። 27,674 ሰዎች በቫይረሱ እንደሞቱ የተመዘገበ ሲሆን 134,288 ሰዎች ደግሞ አገግመው ከሆስፒታል ወጥተዋል።

ከፍተኛ የተጠቂ እና ሟቾች የተመዘገበባቸው፦

• አሜሪካ
- 104,256 ተጠቂዎች
- 1,704 ሟቾች

• ጣልያን
-86,498 ተጠቂዎች
- 9,134 ሟቾች

• ቻይና
- 81,394 ተጠቂዎች
- 3,295 ሟቾች

• ስፔን
- 65,719 ተጠቂዎች
- 5,138 ሟቾች

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AFRICA

በአፍሪካ 46 ሀገራት የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ተጠቂዎች ቁጥር 3,778 ደርሷል። 109 ሰዎች በቫይረሱ ሞተዋል። በተጠቂዎች ቁጥር ደቡብ አፍሪካ የቀዳሚውን ስፍራ ይዛለች በሀገሯ 1,170 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በስፔን ተጨማሪ 832 ሰዎች ሞቱ!

ስፔን በ24 ሰዓት ውስጥ በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] 832 ሰዎች መሞታቸውን ሪፖርት አድርጋለች። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 5,690 ደርሷል። በተጨማሪ በ24 ሰዓት 6,529 ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸውን ተከትሎ 72,248 ደርሰዋል።

ምንጭ፦ የስፔን ጤና ሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ 'ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት' የተወሰኑ የህግ ታራሚዎች ለማምለጥ ያደረጉት ሙከራ መክሸፉን የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ገለጸ።

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን እንዳስታወቀው፤ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ለማምለጥ ሙከራ ያደረጉ የህግ ታራሚዎች ሁከት ለመፍጠር ሞክረዋል።

በዚህም ማረሚያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ባለ አንድ ዞን እሳት ተነስቶ የነበረ ሲሆን በማረሚያ ፖሊስ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ውሏል። የማምለጥ ሙከራ ያደረጉት የህግ ታራሚዎች በህግ የሚጠየቁ መሆኑንም ኮሚሽኑ ገልጿል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮቪድ-19 የተጠቃችው የ10 ዓመት ታዳጊ...

ኢኳቶሪያል ጊኒ ውስጥ የ10 ዓመት ታዳጊ በቫይረሱ መያዟ ተነግሯል። ይህች ታዳጊ የጉዞ ታሪኳ እንደሚያሳየው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ማርች 13 ነበር ከስፔን ወደ ኢኳቶሪያል ጊኒ የተመለስችው። ታዳጊዋ በዋና ከተማዋ በሚገኝ ሆቴል ተለይታ እንድትቀመጥ የተደረገ ሲሆን አሁን ላይ በሐገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ብዛት 13 ደርሷል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

አንድ (1) ሰው ከኮሮና ቫይረሱ ማገገሙን የጤና ሚንስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ላይ ባወጡት መረጃ አሳውቀዋል።

የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦

• የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው - 797
• በአሁን ሰዓት በለይቶ ማቆያ ያሉ - 13
• ፅኑ ህሙማን - 0
• ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ያገገሙ - 1
• በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ድምር - 16

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አንድ ሰው ከኮሮና ቫይረስ አገገመ የሚባለው መቼ ነው?

አንድ ታማሚ ከኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] በሽታ ሙሉ ለሙሉ አገገመ የሚባለው ለሶስት (3) ተከታታይ ቀናት ምንም አይነት ምልክት ሳይኖረው ሲቆይ እና በሚደረግለት ሁለት ተከታታይ የላብራቶሪ ምርመራ ነጻ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡

ምንጭ፦ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የቻይና የጤና ባለሞያዎች ወደ UK አቀኑ!

የቻይና 15 የጤና ባለሞያዎች የህክምና ቁሳቁሶችን በመያዝ ወደUK አምርተዋል። የጤና ባለሞያዎቹ በUK የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዙ ነው የተነገረው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በለይቶ ማቆያ የነበሩ 3 ሰዎች ነጻ ሆነዋል!

ከጅቡቲ ከተመለሱ 814 #ኢትዮጵያዊያን መካከል በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ተጠርጥረው በለይቶ ማቆያ የነበሩ 3 ሰዎች ነጻ መሆናቸው መረጋገጡን የድሬዳዋ ጤና ቢሮ ኃላፊ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል። የቢሮ ኃላፊ ዶክተር ፉአድ ከድር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል አዋሳኝ ከሆነው የሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን ጋር በተቀናጀ መንገድ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#NIGERIA

81 ሰዎች በCOVID-19 በተጠቁባት ናይጄሪያ (ሌጎስ ከተማ) ህመምተኞችን ለማከም ስቴዲየም ውስጥ ይህ የህክምና ማዕከል እየተገነባ ይገኛል።

#BINI #EMMANUEL
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጥቂት ስለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት፦

- እዚህ ገፅ ውስጥ የተቀላቀላ ግለሰብ የቤተሰቡ አንድ አባል ተደርጎ ነው የሚቆጠረው። አባል ብቻ ሳይሆን የዚህ ገፅ ባለቤት ነው። የጎደለውን መሙላት፣ ጣፋቶችን ማረም፣ ስህተቶችን ማስተካከል ይጠበቅበታል።

- ቲክቫህ ኢትዮጵያ መደበኛ ሚዲያ ወይም ዜና ማሰራጫ ሳይሆን ለቲክቫህ ቤተሰቦች አንድም ከአባላቱ በሌላ በኩል ከመገናኛ ብዙሃን መረጃ አሰባስቦ ያስቀምጣል፤ ያከማቻል፣ ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን፣ ለሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች፣ እንዲሁም እንዚህ ፅሁፍ ላይ ለማንገልፃቸው አካላት ቀጥታ ጥቆማ ያደርሳል።

- ዜና ማሰራጫዎች በማህበራዊ ሚዲያ ስፍር ቁጥር የላቸውም ፣ ከአንዱ እየተወሰደ የአንዱን ፣ የአንዱን አሰራር እየተከታተሉና እየኮረጁ ብዙ ገፆች ተፈጥረዋል። በተጨማሪ መረጃ መከታተያ የቴሌቪዥን እና ሬድዮ ጣቢያዎች በርካታ ናቸው። የቤተሰባችን አባላት የመረጃ እጥረት ችግር የለባቸውም!

- የኛ ኃላፊነት ይህን ቤተሰብ መጠብቅ ነው። የቤተሰቡ አባል የምንጠብቀው ከሀሰተኛ መረጃዎች ፣ ከጥላቻ ፣ ከአሉታዊ አስተሰቦች፣ በስውር ተፅእኖዎች፣ የአንድ ሀገር ዜጋ ሆኖ ከመከፋፈል፣...ወዘተ ነው። አባላቱ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚያጠፉትን ጊዜ መቆጠብ ደግሞ ትልቁ ኃላፊነታችን ነው።

- ለቤተሰባችን አባላት አስፈላጊ የሆኑ በሁሉም እድሜ ክልል፣ በሁሉም አቅጣጫ፣ በሁሉም ሙያ፣ የሚሰራጩ መረጃዎችን ከመገናኛ ብዙሃን አሰባስበን በአንድ ቦታ እናስቀምጣለን። በሀገራችን ጉዳይ ማሳሰቢያ፣ ማስጠንቀቂያ፣ ጥቆማ፣ ትኩረት የሚፈልጉ ጉዳዮችን እንገልፃለን።

የዚህ ገፅ ባለቤት አንተ፣ እኔ፣ አንቺ፣ እኛ ነን!
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ፦

በትናትናው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ ሀያ የሚደርሱ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል፡፡

አስከሬናቸውም ወደ ኮሌጃችን ፎረንሲክ እና ቶክሲኮሎጂ ዲፓርትመንት (Forensic Medicine and Toxicology) መጥቶ ምርመራ ተደርጉለት ለቤተሰባቸው ተሰጥቷል፡፡

ይሁን እንጂ አንዳንድ ሐላፊነት የጎደላቸው ግለሰቦች በማህበራዊ ገጻቸው ከእውነት የራቀ ዜና ጽፈዋል፡፡ እውነታው ግን በአስከፊው የመኪና አደጋ ሳቢያ የተከሰተ እንደሆነ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
BGI 3.5 ሚሊዮን ብር እገዛ አደረገ!

ቢጂ.አ.ይ ኢትዮጵያ በላከልን መልዕክት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እንዲረዳ በማሰብ 3.5 ሚሊዮን ብር በቀን መጋቢት 18, 2012 ለኮሮና ሚቲጌሽን ትረስት ፈንድ ገቢ እንዳደረገ አሳውቆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከሰላም ሚኒስቴር የተላከ መልዕክት፦

በመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ሥም እናመሰግናለን!

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ ቦትላንት እና በዛሬው እለት በጎ አድራጊ ወገኖች በሰላም ሚኒስቴር ተገኝተዉ አበርክተዋል፡፡

- ንብ ባንክ የ5,000,000.00 (አምስት ሚሊዮን) ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

- ንብ ኢንሹራንሽ ኩባንያ ለዚሁ ዓላማ የሚውል የ1,000,000.00 (አንድ ሚሊዮን) ብር

- ቢ.ጂ.አይ ኢትዮጵያ በበኩሉ የ3,500,000.00 (ሶስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ) ብር

- የዋን ውኃ አምራች ድርጅት የሆነው አባ ሐዋ ትሬዲንግ የ1ሚሊየን ብር ድጋፍ

- አብሃም ትሬዲንግ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት 1 ሚሊየን ብር

- አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ 2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

- እናት ባንክ 2 ሚሊየን ብር

- አዋሽ ባንክ 10 ሚሊየን ብር

- የኤንስሪ ኤች ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት 1500 ጠርሙስ የንፅህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር

- የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ የ10,000,000.00 (አስር ሚሊዮን) ብር ድጋፍ በሰላም ሚኒስቴር በኩል አድርጓል፡፡

የሀገርን ጥሪ አክብራችሁ ላደረጋችሁት ድጋፍ በኢትዮጵያ ህዝብ ስም እጅግ እናመሰግናለን!

የሰላም ሚኒስቴር!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አሞሌ፣ ኤም ብር እና ሄሎ ካሽ በጋራ የሰጡት መግለጫ!

አሞሌ፣ ኤም ብር እና ሄሎካሽ ደንበኞቻቸው የኮሮና በሽታን ለመከላከል የሚያግዝ የነፃ አገልግሎት ማቅረባቸውን አስታውቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia