ጣልያን!
"በሌላው ሀገር እየሆነ ያለውን የምትመለከቱ ከሆነ በእናተ በሀገራቹ ማድረግ ያለባችሁ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው። መጀመሪያ ምን ማድረግ እንዳለብን ግራ ተጋብተን ነበር አሁን ላይ ግን ምን እየሆነ እንዳለ አውቀናል። እኛ ጋር የሆነው በእናተ ላይ ሊሆን ይችላልና ለመግታት ማድረግ ያለባችሁን ከወዲሁ ጀምሩ አትቁሙ! የአንዱ ተሞክሮ ለሌላው ትምህርት ነውና ጥንቃቄን መሰረት አድርጋችሁ ተንቀሳቀሱ" - ዶ/ር ኢማኑኤላ #EBC
የኮሮና ቫይረስን [ኮቪድ-19] መግታት ቀላል ነው፦
- የእጅዎን ንፅህና በአግባቡ ይጠብቁ
- ሰዎች በተሰበሰቡበት አይሂዱ
- ማህበራዊ ርቀትዎን ይጠብቁ
- በተጨናነቁ የትራንስፖርት አመራጮችን አይጠቀሙ
- የጤና ባለሞያዎችን ምክር ያዳምጡ
- የጤና ሚኒስቴር መምሪያዎችን ይተግብሩ
- ስለ ኮቪድ ትክክለኛ መረጃ ከWHO፣ ከጤና ሚኒስቴር እና ከህበረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ብቻ ያግኙ!
ተጨማሪ ፦ 8335 / 952 ነፃ የስልክ መስመሮች ናቸው!
ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኝላችኃለን!
ሰላም እደሩ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

እንደምን አደራችሁ?
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የተሳፋሪውን ቁጥር 50 በመቶ ቀንሶ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተሰምቷል።
የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ፥ እርምጃው የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ያለመ መሆኑን አስታውቀዋል።
አያይዘውም ህብረተሰቡ የትራንስፖርት ጥግግት መጠንን በመቀነስ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር የድርሻውን እንዲወጣም ጠይቀዋል።
ምንጭ፡ ኤፍ ቢ ሲ

ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ በሚመጡ ሁሉም መንገደኞች ላይ ተፈፃሚ የሚሆነው የ14 ቀናት በልዩ ማቆያ ማዕከል የመቆየት ግዴታ ተጀምሯል።
የጤና ሚኒስቴር ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች በስካይ ላይት እና ጊዮን ሆቴሎች ከዛሬ ጀምሮ ለ14 ቀናት ተለይተው ይቆያሉ ብሏል። ቆይታቸውም በራሳቸው ወጪ የሚሸፈን ይሆናል ተብሏል።
ዲፕሎማቶች በኤምባሲዎቻቸው ተለይተው እንደሚቆዩ የጤና ሚኒስቴር ገልጿል። የትራንዚት ተጓዦችም እስከ ቀጣዩ ጉዟቸው ድረስ በስካይ ላይት ሆቴል ተለይተው ይቆያሉም ነው የተባለው።
ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጤና ሚኒስቴር ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች በስካይ ላይት እና ጊዮን ሆቴሎች ከዛሬ ጀምሮ ለ14 ቀናት ተለይተው ይቆያሉ ብሏል። ቆይታቸውም በራሳቸው ወጪ የሚሸፈን ይሆናል ተብሏል።
ዲፕሎማቶች በኤምባሲዎቻቸው ተለይተው እንደሚቆዩ የጤና ሚኒስቴር ገልጿል። የትራንዚት ተጓዦችም እስከ ቀጣዩ ጉዟቸው ድረስ በስካይ ላይት ሆቴል ተለይተው ይቆያሉም ነው የተባለው።
ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ከዛሬ ጀምሮ በተወሰነው መሰረት በተለያየ መንገድ፣ ለተለያየ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ውጭ የነበሩ ወገኖቻችን ወደ ኅብረተሰቡ ከመቀላቀላቸው በፊት ሁለት ሳምንታት ለየት ብለው የሚቆዩባቸውን ስፍራዎች አሰናድተናል። በተለይም ለቆይታ ጊዜው ወጪያቸውን ለመሸፈን ለማይችሉ ዜጎቻችን ሙሉ ወጪያቸውን እኛ እንሸፍናለን።" - ኢ/ር ከንቲባ ታከለ ኡማ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሀዋሳ ከተማ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ለመከላከል የምሽት መዝናኛ ክለቦች ዝግ እንደሚሆኑ የከተማዋ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ገልጿል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሀዋሳ ከተማ ከምሽት መዝናኛ ቤት እንዲዘጉ ከማድረግ በተጨማሪ የሺሻ እና ጫት ቤቶችን የማሸግ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል ከመሄዶ በፊት እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች ይገንዘቡ፦
- ለአንድ ታካሚ አንድ አስታማሚ ብቻ ነው መግባት የሚፈቀደው
- አሁን ያለውን የ#COVID-19 ስርጭትን ለመግታት ማንኛውንም ታካሚዎች ባሉበት ሆነው በስልክ ብቻ ለመጠየቅ ይሞክሩ
- ለድንገተኛ ህክምና እና የሀኪም ቀጠሮ ከሌላቹ በስተቀር ወደ ሆስፒታላችን ባለመምጣት ከ#COVID-19 ስርጭት እራሶን እና ቤተሰቦን ይጠብቁ
- እድሜያችሁ ከ 40 አመት በላይ ሆኖ ተላላፊ ያልሆነ ህክምና (ስኳር፣ ደም ግፊት፣ ልብ ፣ ኩላሊት) ክትትል ያላችሁ በቀጠሮ ቀን የእርሶ ጤና አስችኳይ ሕመም ከሌሎት መድሀኒቱን የሚወስድሎት ወጣት ሰው ከቀጠሮ ካርድ ጋር አብረው እየላኩ ያለቀቦትን መድሀኒት ያሉበት ሆነው እዲወስድሎት ያድርጉ
- መግቢያ በሮች ላይ የሆስፒታሉ ሰራተኞች አድርጉ የሚሏችሁን በአግባቡ ተግባራዊ አድርጉ (እጅን መታጠብ፤ የሙቀት ልየታ፤ ርቀትን ጠብቆ መሰለፍ . . .)
- በሚያስነጥሱበት እና በሚያስሉበት ጊዜ አፎን እና አፍንጫዎን በክንዶ ወይም መሀረብ/ሶፍት ይሽፍኑ
- አገልግሎት ለማግኘት በሚቆዩበት ጊዜ፤ ሰልፍ እና ወረፋ ሲጠብቁ ርቀቶን ቢያንስ በ1 ሜትር ይጠብቁ
[ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል]

የኮቪድ-19 በሽታ ይስፋፋል በሚል ስፔን በማድሪድ ከተማ የሚገኘውን የሀገሪቱን ትልቁ የኮንፈረንስ ማዕከል ጊዚያዊ ሆስፒታል /ተኝቶ መታከሚያነት/ በመቀየር አልጋ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን አዘጋጅታለች።
#VOA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#VOA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በድሬዳዋ አስተዳደር እስካሁን በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ሰው ባይኖርም ችግሩ ቢከሰት ሊያስከትል የሚችለውን ማህበራዊ ቀውስ ለመቀነስ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎች በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።
በዚህም መሰረት በነምበር ዋን ጤና ጣቢያ ከተዘጋጀው ለይቶ ማቆያ በተጨማሪ የፈረንሣይ ሆስፒታልን ለዚሁ አገልግሎት ለማዋል ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ማግኘት ተችሏል።
#DMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዚህም መሰረት በነምበር ዋን ጤና ጣቢያ ከተዘጋጀው ለይቶ ማቆያ በተጨማሪ የፈረንሣይ ሆስፒታልን ለዚሁ አገልግሎት ለማዋል ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ማግኘት ተችሏል።
#DMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በድሬዳዋ ከተማ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከልና ለመግታት፣ ጥቆማ ለመስጠትና አጠቃላይ መረጃ እንዲሁም ምክር ለማግኘት ከፈለጉ በ6407 ነፃ የስልክ መስመር ይጠቀሙ። በአማርኛ ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በሶማልኛ ቋንቋ የሚያስተናግዱ ባለሞያዎችን በ6407 ነፃ የስልክ መስመር ላይ በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጀርመን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ሲባል ከሁለት (2) ሰው በላይ የሚደረግን ማንኛውንም መሰባሰብ በይፋ ከልክላለች።
ቻንስለሯ አንጌላ ሜርኬል ትናንት ባስተላለፉት መልዕክት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት "የራሳችን ባህሪ ከሁሉም ነገር የበለጠ ውጤታማ ነው" ብለዋል።
ትላንት ከሁለት (2) ሰው በላይ መሰባሰብን የሚከለክለው ጠንከር ያለው እገዳ ከተላለፈ ከጥቂት ቆይታ በኋላ የመራሄተ መንግሥቷ ጽህፈት ቤት ቻንስለሯ ራሳቸውን ለይተው እንዳሉ የተገለፀው።
ባለፈው አርብ ቻንስለር አንጌላ ሜርኬልን የሕክምና ምርመራ ያደረገላቸው ሃኪም በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል።
ቃል አቀባዩ እንዳስታወቁት የ65 ዓመቷ ቻንስለር በቀጣዮቹ ቀናት ተከታታይ ምርመራዎች እየተደረጉላቸው ከቤት ሆነው ሥራቸውን የሚሰሩ ይሆናል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ

ኮሮና ቫይረስ እንዳይስፋፋ መደረግ ከሚገባቸው መሠረታዊ ጥንቃቄዎች መካከል ዋነኛው ማህበራዊ ፈቀቅታ (Social distancing) እንደሆነ ይታወቃል። ይሁን እንጂ በከተማችን ብሎም በሃገራችን ይህን ያለመተግበር ቸልተኝነት ይታያል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ያሉ፦
- መሬት አስተዳደር ፅህፈት ቤት ፣
- ውል እና ማስርጃ ፣
- ትራፊክ ማኔጅመት ፣
- ገቢዎች እና የመሳሰሉ በርካታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በርካታ ባለጉዳዮችን በአንድ ጊዜ የሚያስተናግዱ ከመሆናቸው አንጻር እንዲሁም ከግንዛቤ እጥረት ወይም በቸልተኝነት ምክንያት በባለጉዳዮች የሚፈጠር የከፋ መተፋፈግ አሁንም እየተስተዋለ ይገኛል።
ከኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የስርጭት ፍጥነት እንዲሁም ከህክምና እቅርቦታችን አናሳነት አኳያ የእነዚህ ቦታዎች የቫይረስ አስተላላፊነት እድል ከፍተኛ በመሆኑ ተገቢው አትኩሮት በአስተዳደሩ እንዲሰጠው እኛም እንጠይቃለን።

ከጋሞ ዞን ቲክቫህ አባል፦
በሀገሪቱ ገጠራማ አከባቢዎች ህብረተሰቡ ስለቫይረሱ ስርጪትም ሆነ መከላከያ መንገድ ምንም የሚያዉቀዉ ነገር የለም ይኽ ከላይ የምትለከቱት ፎቶ ከትናንትና በስቲያ በጋሞ ዞን የነበረ ገበያ ነዉ። በአከባቢው ምንም አይነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየተሰራ አደለም ጭራሽ በአንዳንድ ወረዳዎች 'የብልጽግና ፖርቲ' ስብሰባዎች በተጨናነቁ እና ጠባብ አዳራሾች እየተደረገ ስለሆነ ለሚመለከተዉ አካል ብታሳዉቁ ነገሮች ሳይበላሹ ማስተካከያዎች ቢደረጉ ጥሩ ነዉ።

አሁንም በአ/አ በርካታ ቦታዎች የማህበራዊ ርቀትን ጠብቆ የመንቀሳቀስ ነገር መፍትሄ አልተገኘለትም። ይህ ሁኔታ እጅግ አደገኛ እና ለቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ እድል ስለሚሰጥ ጊዜው ሳይረፍድ አንዳች መፍትሄ ቢበጅለት የተሻለ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TurkishAirlines
የቱርክ አየር መንገድ በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝ ምክንያት ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ5 አገሮች በስተቀር ዓለም አቀፍ በረራዎችን እ.ኤ.አ ከመጋቢት 27 ቀን 2020 ጀምሮ እንደሚያቆም አስታውቋል። አየር መንገዱ ወደ ሆንግ ኮንግ፣ ሞስኮ፣ አዲስ አበባ፣ ኒው ዮርክና ዋሽንግተን የሚያደርገው በረራ እንደማይቋረጥ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ቢላል ኢክሲ ማስታወቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
#Reuters #etv

አንድ የቲክቫህ አ/አ ከተማ አባል ከጋሞ ዞን የቲክቫህ አባል ከትናንት በስትያ ስለነበረው ገበያና የህብረተሰቡን ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነት የሚገልፀውን መልዕክት ተመልክቶ ይህን ብሏል፦
"ሩቅ ሳንሄድ እዚሁ መርካቶ ውስጥ ዛሬ ላይ ከዛ በበለጠ ተጨናንቆና ተፋፍጎ እየተገበያየ ነው መንግስት ጠንከር ያለ እርምጃ ውስጥ ካልገባ ማክስና ሳኒታይዘር ማከፋፈሉ እንዲሁም የህክምና ቦታዋችን ማሰናዳቱ ትርጉም የለውም።"
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች 11 ሲሆኑ ሁሉም የሚገኙት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ነው። ይህም ቢሆን በጤና ሚኒስቴር እንዲሁም በጤና ባለሞያዎች እየተሰጡ ያሉ የጥንቃቄ መመሪያዎች ተፈፃሚ እየሆኑ አይደለም።

ይህ ሁኔታችን እና ፍፁም ግድየለሽነታችን በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ከፍተኛ ዋጋ መክፈላችን አይቀርም ፤ እያንዳንዳችን ኃላፊነት ተሰምቶን የምንባለው ካላደርግን ውሎ አድሮ ፀፀቱ አያስቀምጠንም። ፎቶው አሁን ቦሌ ካርጎ ያለውን ሁኔታ የሚያሳይ ነው። ማህበራዊ ርቀት የሚባለው ነገር ጭራሽ ተረስቷል።
እኛም ከመናገር ወደኃላ አንልም!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እኛም ከመናገር ወደኃላ አንልም!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በAAU በኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር አሰፋ አድማሴ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ የተናገሩት፦
የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ወረርሽኝ እንደ ህብረተሰብ የመቆምና ያለመቆም ፤ እንዲሁም የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ ውስጥ የሚከትት በመሆኑ ፤ የግል ፍላጎታችንን ጨምሮ እንቅስቃሴያችን በሙሉ በተለመደው መልኩ መቀጠል የለበትም።
ከዚህ ችግር ለመውጣት ብቸኛው አማራጭ እያንዳንዳችን በሃላፊነት ስሜት ልንቀሳቀስና አንዱ ለሌላው ሊያስብ ይገባል። እንዲሁም ከመንግስት በየጊዜው የሚተላለፉ መልዕክቶችን በመከታተል ተግባራዊ ማድረግ ይኖርብናል።

ኢትዮጵያ ድንበሮቿን ለሰዎች ዝውውር ዝግ አደረገች!
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በአገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ድንበሮች ለሰዎች ዝውውር ዝግ መደረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታውቀዋል።
ወረርሽኙን ለመከላከልም መንግስት አምስት ቢሊዮን ብር መበጀቱንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስታወቁት።
በአውሮፕላን ከውጭ በሚገቡ መንገደኞች ላይ ለ14 ቀናት ተለይው እንዲያቆዩ የሚያስገድደው ውሳኔም ከዛሬ ጀምሮ በመተግበር ላይ ነው።
#etv