#COVID19
እነዚህ 'ከጥቁር አንበሳ' በርካታ ተማሪዎች ዛሬ ጥዋት የተላኩ መልዕክቶች ናቸው። የጤናችንን ሁኔታ አደጋ ላይ የሚጥል ውሳኔ ተወስኗል ነው የሚሉት፤ የሚመለከተው፣ ለዜጎቹ ጤንነት ግድ የሚለው አካል ካለም አንድ ይበልልን ሲሉ አሳስበዋል። በቂ የሆነ የንፅህና መጠበቂያ በሌለበት፣ እጅግ የሰው ቁጥር በሚበዛበት፣ ጥቁር አንበሳ ግቢ በአሁን ሰዓት ተማሪዎች ዋርድ ላይ እንዲሳተፉ የተወሰው ውሳኔ እጅግ ኃላፊነት የጎደለው እንደሆነም ገልፀዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

አውስትራሊያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በማሰብ ከሀገሯ ዜጋ ውጭ የሆኑ የሌላ ሀገር ዜጎች ወደሀገሪቱ እንዳይገቡ አግዳለች። በተጨማሪ የሀገሯን ድንበር ለ6 ወር እንዲዘጋ ወስናለች።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮስታሪካ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ሞት ተመዝግቧል። እንደ ሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ ሟቹ የ87 ዓመት አዛውንት ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA
የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ከኮቪድ-19 ስርጭት ታራሚዎችን ለመጠበቅ ሲባል ለመጪዎቹ 15 ቀናት ታራሚዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙ እግድ መጣሉን ኢዜአ ዘግቧል።
ታራሚዎች የከፋ የጤና ችግር ካልገጠማቸው በስተቀር ወደ ሆስፒታሎች በሪፈራል እንደማይላኩም ነው የተነገረው።
አስተዳደሩ በማረሚያ ቤቶች አካባቢ ሊከሰት የሚችለውን ችግር ቀድሞ በመለየት ለመከላከል ሂደቱ የተለያዩ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል።

ጤና ሚኒስቴር፦
"የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በማረሚያ ቤቶች ለህግ ታራሚዎች የግል ንጽህና መጠበቂያ ሳሙናና አልኮል በማቅረብ ራሳቸውን ከኮሮና ቫይረስ እንዲጠብቁ ለማድረግ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡"

ሞሪሽየስ ለየትኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ ድንበሬ ዝግ ነው ስትል አሳውቃለች። የሞሪሺየስ ጠቅላይ ሚኒስትር 3 የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች መገኘታቸው በመረጋገጡ ነው ይህን ጥብቅ ውሳኔ ያሳለፉት።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ደቡብ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የጉዞ እገዳ ያደረገችባቸው ሀገራት 9 ደርሰዋል። ሀገራቱ ፦ ቻይና ፣ ፈንሳይ ፣ ጀርመን ፣ ጣልያን ፣ ደቡብ ኮሪያ ፣ እንግሊዝ ፣ አሜሪካ ፣ ስፔን እና ኢራን ናቸው። ከዚህ ቀደም በእገዳው ውስጥ ያልተካተተችው #ፈረንሳይ እገዳው ተጥሎባታል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሩሲያ የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ሞት ሪፖርት አደረገች። ሞስኮ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው እንዳለፈ የተነገረው የሰባ ዘጠኝ (79) ዓመት አዛውንት ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኤርትራ 'ብሔራዊ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ' ፈተና ለ14,960 ተማሪዎች እየተሰጠ ይገኛል። ጅዳና ሪያድ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ይሰጥ የነበረው ፈተና በኮሮና ሳቢያ መሰረዙን የኤርትራ ብሔራዊ ፈተና ማዕከል ዳይሬክተር ብስራት ገብሩ ተናግረዋል።
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ እሸቴ በቀለ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ እሸቴ በቀለ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ እና የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናዎች የጊዜ ሰሌዳ በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ስርጭት ስጋት ምክንያት እንደሚራዘም ትምህርት ሚኒስቴር መናገሩን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል። ሚኒስቴሩ ትክክለኛ የመፈተኛ ጊዜዎቹን ትምህርት ሲጀመር አሳውቃለሁ ብሏል፡፡
ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

"በአዲስ አበባ የውጭ አገራት ዜጎች ሲንቀሳቀሱ ኮሮና ቫይረስ [COVID-19] አመጣችሁብን ፣ በእናንተ ምክንያት ነው በቫይረሱ የተጠቃነው በሚል ነዋሪዎች ጥቃት እያደረሱ ነው" - የአሜሪካ ኤምባሲ
"ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የውጭ ሚድያ ጋዜጠኞችን ፎቶ በመለጠፍ "ኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የያዛቸው ናቸው" ተብሎ ሀሰተኛ መረጃ ሶሻል ሚድያ ላይ እየተለጠፈ ነው።" - ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የውጭ ሚድያ ጋዜጠኞችን ፎቶ በመለጠፍ "ኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የያዛቸው ናቸው" ተብሎ ሀሰተኛ መረጃ ሶሻል ሚድያ ላይ እየተለጠፈ ነው።" - ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በነገራችን ላይ ...
ከመዲናችን አዲስ አበባ አቅራቢያ በምትገኝ አንዲት ከተማ ውስጥ ከውጭ ሀገራት ዜጎች ጋር የሚሰራ የቲክቫህ አባል የታዘበውንም አካፍሎናል።
ላለፉት 5 ዓመታት ከውጭ ዜጎች ጋር መስራቱን የሚናገረው ይኸው የቤተሰባችን አባል ኢትዮጵያ ውስጥ ኮሮና ገባ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ አብሯቸው በሚሰራ የስራ ባልደረቦቹ ላይ መገለል፣ ዘለፋ፣ ስድብ፣ የሰውን ክብር የሚነኩ ድርጊቶች እየተፈፀሙባቸው እንደሆነ ነግሮናል።
እጅግ በጣም በሚያሳዝን መልኩ ደግሞ አንዳንድ ሰዎች የስራ ባልደረቦቹን በመንገድ ላይ በሚሄዱበት ወቅት 'ኮሮና' እያሉ ሲጠሯቸው እንደታዘበ ገልጾልናል።
ሰዎች ከእንግዲህ ያለ የወረደ ተግባር እንዲቆጠቡ መልዕክት አስተላልፉንኝ ያለን ይኸው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል፤ እንዚህ ሰዎች በብዙ መልኩ እየረዱን ያሉ ታታሪ ሰራተኞች ስለሆኑ ክብራቸውን የሚነኩ ሰዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሲል መልዕክት አስተላልፏል።

የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኮሮና ቫይረስ ምላሽ ለመስጠት በመላው ኢትዮጵያ ያለመታከት እየሰሩ ነው ላሏቸው የጤናና የህብረተሰብ ጤና ባለሙያዎች እና የድጋፍ ሰጬ ሰራተኞች ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሃሌሉያ አጠቃላይ ሆስፒታል፦
ሃሌሉያ አጠቃላይ ሆስፒታል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መልዕክት ዛሬ ጥዋት ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የሰራው ዜና ሀሰተኛ እና ከእውነት የራቀ ነው ብሏል። ሆስፒታሉ የሙቀት ልየታ እያደድረግ እንደሚገኝ ከመግለፅ በዘለለ ሬድዮ ጣቢያው ለህዝብ እንዲሰራጭ ያደረገው መረጃ ስህተት እንደሆነ አስገንዝቧል። ሆስፒታሉ ፥ ህዝቡም ይሄን ይወቅልኝ ብሏል።

ራዲሰን ብሉ ሆቴል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መልዕክት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሆቴሉ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ እንዳለ ተደርጎ የሚነዛው ወሬ ሀሰተኛ መሆኑን አሳውቋል።
#SHARE #ሼር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SHARE #ሼር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በየአካባቢው ያልተቋረጡት ስብሰባዎች፦
ዛሬ የተለያዩ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ የፌስቡክ ገፆችን ዞር ዞር እያልን እየተመለከትን ነበር፤ የብልፅግና ፓርቲ እንዲሁም ሌሎች ስብሰባዎች እየተደረጉ እንደሆኑ ይገልፃሉ። በአንድ በኩል ህዝቡ ከመጠጋጋት እንዲቆጠብ መልዕክት እየተላለፈ፣ በሌላ በኩል መሰል ብዙ ሰዎች የተሰበሰቡበት ስብሰባዎችን እየተመለከትን ነው።