TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
«አፍሪቃ ለክፉ ቀን መዘጋጀት አለባት» - ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

«አፍሪቃ ለክፉ ቀን መዘጋጀት አለባት» ሲሉ የዓለም የጤና ድርጅት ዳሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም የኮሮና ወረርሽን በከፍተኛ ፍጥነት እየተሰራጨ መሆኑን አስጠንቅቀዋል።

ዶክተር ቴድሮስ ትላንት በሰጡት መግለጫ «አፍሪቃ ንቂ» አህጉሬ ንቂ» ሲሉ አፅዕኖት ሰጥተውም አሳስበዋል። 116 ታማሚዎች ላይ ተህዋሲውን ባረጋገጠችው ደቡብ አፍሪቃ ስድስት እድሜያቸው ከ 10 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ይገኙበታል።

ከ54ቱ የአፍሪቃ ሀገራት 30ዎቹ በተህዋሲው የተያዙ ሰዎች እንዳሉ ያረጋገጡ ሲሆን በቅርቡ ደግሞ ጋምቢያ፣ ዛምቢያ እና ጅቡቲ እንዲሁ የመጀመሪያ ያሉትን ሰው አግኝተዋል።

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሀሌሉያ ሆስፒታል እያደረገ ያለው ዝግጅት፦

- የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሙቀት ልየታ እያደረገ ነው። ወደ ሆስፒታሉ የሚመጡ ሁሉም ተገልጋዮች እና የሆስፒታሉ ሰራተኞች በዚሁ የሙቀት ልየት እንዲያልፉ እየተደረገ ነው።

- የሙቀት ልየታ ስራው እየተሰራ ያለው የሆስፒታሉ መግቢያ በሮች በሙሉ ተዘግተው በተዘጋጁ ድንኳኖች ውስጥ ነው፤ ይህን ስራ የሚከውኑትም የሰለጠኑ ባለሙያዎች ናቸው። በተጨማሪ ወደ ውስጥ የሚገቡ ሰዎች የእጃቸውን ንፅህናም እንዲጠብቁ ይደረጋል።

- 400 ለሚሆኑ የሆስፒታሉ ሰራተኞች በሽታውን መከላከል በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎች ሰጥቷል። ለሰራተኞቹ የመከላከያ መሳሪያዎችን ሰጥቷል።

- በሆስፒታሉ በሙቀት ልየታ ምርመራ የሚለዩ እና የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ምልክቶች የሚታዩባቸውን ሰዎች ለይቶ ማቆያ ክፍልም አዘጋጅቷል።

#HallelujahGeneralHospital
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
- በስፔን በ24 ሠዓት ውስጥ የ169 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 767 ደርሰዋል።

- በኢራን በ24 ሰዓት ውስጥ የ149 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 1284 ደርሰዋል።

- በጣሊያን በ24 ሰዓት ውስጥ የ475 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል። በሃገሪቱ በቫይረሱ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 3 ሺህ ተጠግቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዶ/ር ሊያ ታደሰ መልዕክት፦

"የኮሮና ቫይረስ በሽታ ዘር ቀለም እና ሃይማኖት የለውም። ከየትኛውም ሃገርና እና ዜግነት ጋር አይገናኝም። በሽታው በሁላችንም ላይ የመጣ የጋራ ፈተና ነውና ይህንን አስቸጋሪ ጊዜ በመተባበርና በመረዳዳት በፍፁም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ልናሳልፍ ይገባል።"

#SHARE #ሼር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ያልተገቡ ድርጊቶች ሊቆሙ ይገባል!

"ኤፍሬም እባላለሁ የቴክቫህ ቤተሰብ ነኝ ፤ ስራዬ የቱር ሹፌርና ጋይድ ነኝ በስራዬ ብዙ ነገሮች ቢያጋጥሙኝም ያሁኑ ትንሽ ለየት ያለና ከስብእና ውጪ አልፎም ከኢትዬጽያዊነት ስነ ምግባር ውጪ የሆነ ተግባር እያየሁ ነው። ቱሪስቶች እየተዘለፋና እየተሰደቡ ከነሱም አልፎ እኛንም እየተናገሩን ይገኛል፤ ኮሮና ያመጣችሁብን ምትገሉን እናንተ ናችሁ ሂዱልን አትቅረቡን እየተባሉ ይገኛል፤ ለህብረተሰቡ በተቻለ አቅም ከዚህ አይነት አስተሳሰብ እንዲወጡ የተቻለንን ብናደርግ ስል እመክራለሁ!"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"እየተከናወነ ያለው የውል ስምምነት የወሰን ወዝግብ ያለባቸውን ቤቶች አያካትትም" - የአ/አ ከተማ አስተዳደር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ13ኛው ዙር እጣ የወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እየተከናወነ ያለው የውል ስምምነት የወሰን ወዝግብ ያለባቸውን ቤቶች እንደማያካትት አስታውቋል፡፡

ከሰሞኑን በተለያየ የግል ምክንያት የቤት እጣ ወጥቶላቸው ውል ያልተፈራረሙ እድለኞችን ውል የማፈራረም ስራ እተከናወነ እንደሚገኝም ገልጿል፡፡

ቤቶቹን የማስተላለፍ አካል የሆነው የውል ሰምምነት በኦሮሚያ ክልል መንግስትና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መካከል የወሰን ጥያቄ የተነሳባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች አያካትትም ብሏል፡፡

የወሰን ጥያቄ የተነሳባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ጉዳይ በፌዴራል መንግስት በተቋቋመው ኮሚቴ ፤ በኦሮሚያ ክልልና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኩል እየታየ እንደሚገኝም ገልጿል፡፡

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ETHIOPIA

በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋጠ ሰዎች 6ኛዋ የብሪታኒያ ኤምባሲ ባልደረባ መሆናቸውን አምባሳደር አላስቴር ማክፊል አረጋግጠዋል። የኤምባሲው ባልደረቦች መረጃው እንደደረሳቸው ለጤና ሚኒስቴር ማሳወቃቸውን ገልጸዋል።

#EsheteBekele #UKinEthiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እኚህ ሰዎች እንዲህ ተራርቀው የተሰለፉት /የቆሙት/ ለምን ይምስላችኃል ? መልሱ በጣም ቀላልና ግልፅ ነው 'ራሳቸውን ከኮሮና ቫይረስ ለመጠበቅ' ፤ እኚህ ሰዎች ይህን ማደረጋቸው በኮሮና ቫይረስ ከመጠቃት በእጅጉ ያድናቸዋል። እኛስ ምን አይነት ጥንቃቄ እያደረግን ነው ? ያልተገቡ ድርጊቶችን አይተን ታዝበን ማለፍ ብቻ ነው ወይስ ግንዛቤ ለማስጨበጥ፣ ለሰዎች ለምንገር ጥረት እናደርጋለን?

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ዋናው ፅህፈት ቤት!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስትር አቶ መላኩ አለበል፦

እባካችሁ ራሳችን ከረጃጅም ሰልፍና መጨናነቅ እንቆጥብ!

በ18 ኢንደስትሪዎች ከ1.2 ሚሊየን ሊ/ር በላይ ሳኒታይዘር እየተመረተ ነው በፍጥነት ለገበያ ስለሚቀርበት ሁኔታም እየተሰራ ነው።

መከላከያ ለመግዛት ወጥተን ተበክለን እንዳንመለስ እንጠንቀቅ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት፦

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወረ በሚገኘው መረጃ ብዙ እየጠየቃችሁ ነው፤ እንዲህ ያሉ ጤና ነክ ጉዳዮች ኃላፊነት የሚጠይቁ ስነሆኑ፣ በተገቢው መንገድ መረጃው ከጤና ሚኒስቴር ሲደርሰን እናሳውቃለን።

ሀገሪቱ ውስጥ ተጨማሪ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ቢገኝ እንኳን መረጃዎችን አደራጅተው የሚሰጡ አካላት አሉ፤ እንዲህ ያሉ sensitive ጉዳዮች እንደሌሎች መደበኛ መረጃዎች ሊታዩ አይገባቸው።

በኢትዮጵያ የኮቫድ-19 ተጠቂዎች ቁጥር ላይ ምንጫችን ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሆነው ካላገኘናቸው መረጃዎችን ማጋራት አግባብነት አይኖረው።

ይህን መልመድ ያስፈልጋል፤ ትዕግስትም ያስፈልጋል። እንዲህ ያሉ ድርጊቶች ሲደጋገሙ ሀገሪቱን ሙሉ ማመሳቸው ስለማይቀር ጉዳዩን የያዙት ያካላት መረጃዎችን ሲሰጡን እኛ መልሰን እናጋራለን።

በዚህ ቫይረስ ስርጭት መቆጣጠር ላይ ማህበራዊ ሚዲያው ኃላፊነቱን እንደሌሎች ያደጉት ሀገራት መወጣት ካልቻለ፤ እጅግ የከፋ ሁኔታ ውስጥ ይዞን ሊገባ ይችላል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሀዋሳ ከተማ በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥረው በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ 30 ሰዎች ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸውን የክልል ጤና ቢሮ ማስታወቁን DW ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የእስራኤል ፖሊሶች በቤታቸው እንዲቆዩ የታዘዙ የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪዎችን ስልክ እየጠለፉ ቤት ውስጥ መሆን አለመሆናቸውን እያረጋገጡ ነው።

ፖሊሶች በአደባባይ እየዞሩም ተሰባስበው ያገኟቸውን ሰዎች በመበተን ላይ ናቸው። እስራኤል ለአስፈላጊ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ማንም ሰው ከቤት እንዳይወጣ ማዘዟን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የግዜ መቆጣጠሪያ የአሻራ ማሽኖችን የመንግስትም ሆነ የግል መስሪያ ቤቶች መጠቀም ማቆም አለብን!" - አበበ አበባየሁ (የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአማራ ክልል የኮሮና ቫይረስ ምልክት ታይቶባቸው ከነበሩ ስድስት ሰዎች መካከል አራቱ ነፃ መሆናቸው የክልሉ ጤና ቢሮ ማስታውቁን ቢቢሲ ዘግቧል። በክልሉ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ምልክት ታይቶባቸው ከነበሩት መካከል የሁለቱ ውጤት እንደታወቀ ይፋ እንደሚደረግም ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
CGTN AFRICA ከደቂቃዎች በፊት ይዞት በወጣው መረጃ በ34 የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ 733 ኬዞች እንደተመዘገቡ ገልጿል። በምስራቅ አፍሪካ ያለውን ኬዝ ፦ ሩዋንዳ 11፣ ኬንያ 7፣ ኢትዮጵያ 7፣ ሲሸልስ 6፣ ታንዛኒያ 6፣ ሱማሊያ 1 እና ጅቡቲ 1 ሲል ገልጿል። ኢትዮጵያ እስካሁን ባለው አንድ ተጨማሪ ኬዝ ላይ ይፋዊ መረጃ አልሰጠችም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለኮሮና ቫይረስ የባህል መድሃኒት በኢትዮጵያ ተገኝቶለታል መባሉ ሃሰት መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል። በሳይንስ ምንም የተረጋገጠ ነገር ስለሌለ ህብረተሰቡ ከእንዲህ አይነቱ ሀሰተኛ መረጃ ራሱን እንዲጠብቅ የጤና ሚኒስቴር አሳስቧል።

ከኮሮናቫይረስ መከላከል ጋር በተገናኘ ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያዎች የኢትዮጵያዊያን ባህል ሀኪሞች መድሃኒቱን አግኝተዋል በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሐሰተኛ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሰሐርላ አብዱላሂ ገልጸዋል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወደ አፍሪካ እና በማደግ ላይ ያሉ አገሮች እየገሰገሰ ነው። የጤና አግልጋሎቶቻቸው በጣም ደካማ ናቸው። ካደገው ዓለም ጠንካራ ድጋፍ ይሻሉ። ያን ድጋፍ ከተከለከሉ አደገኛ ጣጣ ይገጥመናል። አገሮች አቅም ሳይኖራቸው ቀርቶ ቫይረሱ [COVID-19] በቁጥጥር ሥር ሳይውል ከቀረ እንደ ሰደድ እሳት ሊዛመት ይችላል። በዚህም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ሊሞቱ ይችላሉ" - አንቶኒዮ ጉቴሬዝ

#EsheteBekele
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አለም አቀፏ ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ ስለ ኮሮና ቫይረስ!

የተለይዩ አለም አቀፍ ውድድሮችን ብሎም የሀገር ውስጥ ውድድሮችን በበላይነት በመምራት የምትታወቀው ሊዲያ ታፈሰ ትልቅ መልእክቷን ታስተላልፋለች።

በፈጣን ሁኔታ በአለማችን እየተስፋፋ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ በጋራ እንከላከል ስትል መልእክቷን ለሀገሯ ልጆች አስተላልፋለች።

ቲክቫህ ስፖርት ከ ሀትሪክ ስፖርት ጋር በመሆን በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ በስፖርት አፍቃሪያን ዘንድ እየሰሩ ያሉትን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እንዲሁም አዲስ መረጃዎች በ @tikvahethsport መከታተል ትችላላችሁ።

@tikvahethsport @tikvahethiopia
የጥቁር አንበሳ ተማሪዎች የኮሮና ስጋት!

የጥቁር አንበሳ ተማሪዎች ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘ እጅግ ጥንቃቄ በሚያስፈልግበት በዚህ ወቅት የዋርድ ተግባራት] ህሙማን ተኝተው በሚታከሙባቸው የመኝታ ክፍሎች ውስጥ የሚደረግ የመማር ማስተማር ሂደት] ላይ እንድንሳተፍ መወሰኑ ኃላፊነት የጎደለው ውሳኔ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ አሰምተዋል።

ይህ ተግባር የመሰብስብ እና ከታካሚዎች እንዲሁም ከአስታማሚዎች ጋር ቀጥታ የሚያገናኝ ስራ መሆኑ እየታወቀ በቂ የሆነ የንፅህና መጠብቂያዎች (እንደ ጓንት ፣ አልኮል፣ ፌስ ማስክ ፤ እንዲሁም በቂ የውሃ አቅሮቦት) እንኳን በቅጡ ባልተሟለበት ሁኔታ እንዲህ ያለ ውሳኔ መወሰኑ እንዳሳዘናቸው ገልፀዋል።

ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት የቅሬታ መልዕክት ለእኛም፣ ለቤተሰቦቻችንም ፣ ለታካሚዎች (በተለይም ለፅኑ ህሙማን) እንዲሁም ለዜጎችም በምንም መስፈርት የማይበጅ ዉሳኔ በመሆኑ አጥብቀን እንቃወማለን ፤ ሰሚ ካለ በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጠን እንጠይቃለን ብለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia