TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አልሰማሁም፤ አላየሁም እንዳትሉ...
(TIKVAH-ETHIOIA)

የጥላቻ ንግግር የዘር ማጥፋት ዋነኛ መሰረት ነው። የጥላቻ ንግግር ከጀርባው #ያላስተናገደ አንዳች አይነት የዘር ማጥፋት በዓለማችን አልተፈፀመም፡፡

#ናዚ በአይሁዳዊያን ላይ ከፍተኛ የዘር ማጥፋት መፈፀም ከመጀመሩ በፊት #ጀርመናዊያን በአይሁዶች ላይ የከፋ ጥላቻን እንዲያዳብሩ ሰፊ የፕሮፖጋንዳ መደላድልን ሰርቷል፡፡

#በሩዋንዳ በ1990ዎቹ መጀመሪያ ከደረሰው የዘር ማጥፋት ጀርባ #በሬዲዮ ፕሮፖጋንዳ ጭምር የታገዘ #የጥላቻ_ንግግር_ዘመቻ ነበር፡፡

(በተሾመ ታደሰ)

#StopHateSpeech

TIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በመላው ሀገሪቱ እያደረግን ያለነውን #የፀረ_ጥላቻ_ንግግር ዘመቻ #እንድትደግፉን እንለምናለን!!

ስልክ፦ 0919 74 36 30

🇪🇹ኑ ኢትዮጵያን በፍቅር እንገንባ🇪🇹

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እንገናኝ!
(ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ)

ውድ #የሀዋሳ_ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ውድ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች በፍቅር ሀገር እንገንባ #የጥላቻ_ንግግር በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ ይቁም በሚል ልዩ መድረክ ተዘጋጅቷል። በዝግጅቱ ከፍተኛ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ #አመራሮች ይገኛሉ። ወጣት ተማሪዎች መልዕክቶችን ያስተላልፋሉ። ባለሞያዎች ስለማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ግንዛቤ ይሰጣሉ።

N.B በዝግጅቱ #ተሳታፊ የሚሆኑ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ #አባላት ለዲላ፣ መቀለ እና ቡሌሆራ ጉዞ ይመዘገባሉ!

ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች እንመጣለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጥላቻ ንግግርን በመቃወም ደሜን እለግሳለሁ!

3ተኛው የሲቪል ማህንዲሶች ቀን ከትላት አርብ ጀምሮ እስከ እስከ ነገ እሁድ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ አዘጋጅነት እየተከበረ ይጋኛል፡፡ በትላንትናው መርኃግብር ላይ የግጥም ውድድር የተካሄደ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ የአስፉልት ላይ ሩጫና የደም ልገሳ ይደረጋል፡፡ በመዝጊያው ቀን እሁድ የመምህራን እና የተማሪዎች የእግር ኳስ ጫወታ፣የፓናል ውይይትና የፈጠራ ሥራ ውድድር በቴክኖሎጂ ተማሪዎች መካከል ይደረጋል፡፡ በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስቴዲየም እንደሚካሄድ የወጣው መርኃግብር ያሳያል፡፡ በዛሬው ዕለት በሚካሄደው የደም ልገሳ ላይ የወላይታ ሶዶ #stop_hate_speech_movement አባላት #የጥላቻ_ንግግርን_በመቃወም_ደም_እንለግሳለን በሚል መሪ ቃል ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ሲቪል ምህንድስና ተማሪዎች ማህበር ጋር በመተባበር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅተዋል፡፡

Via #Bereket
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፌስቡክ የጥላቻ ንግግሮችን እያስወገደ ነው...

ፌስቡክ በስድስት ወራት ውስጥ 3 ቢሊዮን የሀሰት አካውንቶችን ማጥፋቱን አስታወቀ፡፡ ከሰባት ሚሊዮን በላይ #የጥላቻ_ንግግሮችን በማስወገድም በታሪኩ ከፍተኛ የተባለለትን እርምጃ ወስዷልም ተብሏል፡፡

ፌስቡክ ጥላቻ ንግግርና በሀሰተኛ መረጃዎች እየቀረበበት ያለውን ወቀሳ ተከትሎ ለጀመሪያ ጊዜ ምን ያህል ሀሰተኛ አካውንቶችንና ልጥፎችን ጭምር እንዳጠፋ በግምገማዊ ሪፖርቱ አስታውቋል፡፡

የፌስ ቡክ ዋና አስተዳዳሪው #ማርክ_ዙከርበርግ በትላንተናው ዕለት ፌስቡክን ለመቆጣጠር በተለያየ መልኩ ተከፋፍሎ እንዲደራጅ ለቀረቡለት ጥሪዎች ችግሩን ለመፍታት አሰራሮችን ማዘመን ብቸኛው መፍትሄ ነው ሲል መልሷል፡፡

እንዲወገዱ የተደረጉት የሀሰተኛ አካውንቶች ሁሉም በሚባል ደረጃ በማኅበራዊ አውታር "ንቁ" ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ ዕድል ከማግኘታቸው በፊት ካለፈው ጥቅምት እስከ መጋቢት ድረስ እርምጃው እንደተወሰደባቸው ተመልክቷል፡፡

ፌስቡክ እንዳለው ሪፖርቱ የሚያሳየው የኩባንያውን ግልጽነትና ለተጠቃሚዎቻችን ተጠያቂነታችንን እና ምላሽ ሰጭነታችንን ለማሳየትና እምነት ለመገንባት የሚያስችለን ነው፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የጥላቻ_ንግግር #facebook የጀርመን ባለስልጣናት የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጽ የሆነው ፌስቡክ የሀገሪቱን የጥላቻ ንግግር ህግ በመጣሱ በ2 ነጥብ 3 ሚሊየን የአሜሪካ እንዲቀጣ ውሳኔ ማሳለፋቸውን አስታውቀዋል።

ባለስልጣናቱ በፌስቡክ ላይ ቅጣቱን በትናንትናው እለት ያሳለፉ ሲሆን፥ ቅጣቱ የተላለፈውም ህጉን የጣሱ ይዘቶችን በፌስቡክ ገፅ ላይ ሲሰራጩ ምንም አይነት የማስተካከያ እርምጃ ባለመውሰዱ ነው ተብሏል። የጀርመን የፌደራል ፍትህ ቢሮ ባወጣው መግለጫ፥ ፌስቡክ የጥላቻ ንግግር ህግ የጣሱ ይዘቶች እና ህዝቡን የሚረብሹ ምስሎች ሲለቀቁ እርምጃ ባለመውሰዱ ውሳኔው እንደተላለፈበት አስታውቋል።

ፌስቡክ ህገ ወጥ የተባሉ ይዘቶች ላይ የወሰደውን እርምጃም ግልጽ አድርጎ በሪፖርት እንዳላቀረበም ነው ቢሮው ያስታወቀው። በጀርመን ህግ መሰረት ፌስቡክን ጨምሮ ሁሉም የማህበራዊ ትስስር ድረ ገፆች በበድረ ገፆቻቸው ላይ የሚያጋጥሙ ህገ ወጥ ይዘቶች ላይ የሚወስዷቸውን እርምጃዎች በየስድስት ወሩ በሪፖርት ማሳወቅ እንዳለባቸው ተደንግጓል።

ፌስቡክን ለቅጣት ከዳረጉት ምክንያቶች ውስጥም አንዱ የተሟላ ሪፖርት አለማቅረቡ አንደሆነም ነው እየተነገረ ያለው። የፌስቡክ ኩባንያ ግን በተላለፈበት የቅጣት ውሳኔ ላይ እስካሁን ምላሽ እንዳልሰጠ እና የይግባኝም አንዳልጠየቀ ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት።

ምንጭ፦ www.cnet.com
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የጥላቻ_ንግግር የሚያሰራጩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀመረ፡፡ በአሜሪካ የሚኖሩና በማህበራዊ ሚዲያ ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት የጥላቻ ንግግር የሚያሰራጩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት አስታውቋል። የምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ተጠሪ አቶ አምሳሉ ፀጋዬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት መረጃ ምክር ቤቱ በአሜሪካና በመላው ዓለም የኢትዮጵያውያንን መብትና ጥቅም ለማስከበር እየሠራ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ ቀደም HR-128 የተሰኘው የውሣኔ ሐሳብ በአሜሪካ ኮንግረስ እንዲፀድቅ መሥራታቸውን አስታውሰው አሁን በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ በመደገፍ ቀጣይነቱ እንዲረጋገጥ እየሠሩ መሆኑንም አቶ አምሳሉ ተናግረዋል።

Via #አዲስ_ዘመን
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአሜሪካ #የጥላቻ_ንግግርን የሚያሠራጩ ኢትዮጵያዊያን እንዴት በህግ ይጠየቃሉ
.
.
በአሜሪካ የጥላቻ ንግግር የሚያሰራጩ ኢትዮጵያዊያንን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን የኢትዮጵያ አሜሪካዊያን የዜጎች ምክር ቤት አስታውቋል።

ያነጋገርናቸው የምክር ቤቱ ህዝብ ግንኙነት አቶ አምሳሉ ፀጋዬ፤ ወንድም ወንድሙን በማጣላት፤ ብሔር ከብሔር በማጋጨት እንደ ሃገር ለመቀጠል ፈታኝ ሆኗል፤ ይህንን የሚያደርጉ ግለሰቦችን ለማስተማር ብዙ እየተሞከረ ቢሆንም ነገሩ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ስለመጣ ምክር ቤቱ ግለሰቦቹን ወደ ህግ ለማቅረብ መዘጋጀቱን ይናገራሉ።

እርሳቸው እንደሚሉት በአሜሪካ የጥላቻ ንግግር በሌላ ማህበረሰብ በማሰራጨት፤ ሞትና መፈናቀልን ማስከተል በሕግ እንደሚያስቀጣ ይገልፃሉ።በዚህ ረገድ የሚጠቅሱት ፈርስት አመንድመንት የተሰኘው የአሜሪካ ህግን ነው።

እሳቸው እንደሚሉት ምንም እንኳን በፈርስት አመንድመንት የመናገር ነፃነት የተጠበቀ ቢሆንም በዚሁ ህግ ላይ በመናገር ነፃነት የማይካተቱ ድርጊቶችም ተዘርዝረው ይገኛሉ።

"ግድያ፣ ዛቻ፣ ማስፈራሪያ፣ ብሔርን ከብሔር (ማኅበረሰብን ከማኅበረሰብ) የሚያጋጭ ከሆነ፤ የጥላቻ ንግግሩ ያስከተለው የጉዳት መጠን ተለይቶ ግለሰቦቹን ተጠያቂ ለማድረግ ይቻላል" ይላሉ አቶ አምሳሉ።

የሕግ ሂደቱን የሚከታተል የጠበቆች ቡድን ያለ ሲሆን በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ማስረጃዎችን በማቅረብ የጥላቻ ንግግርን የሚያሰራጩ ሕግ ፊት እንዲቀርቡ እንደሚያደርጉም ያክላሉ።

"አብዛኞቹ እዚህ የሚኖሩ ለአገር የሚያስቡ ናቸው፤ ነገርግን የመጡበትን ማህበረሰብ በመርሳት ያ - ማህበረሰብ ቢፈርስ ደንታ የሌላቸው ጥቂቶች አሉ " የሚሉት አቶ አምሳሉ በህጉ መሰረት ቅጣቱ ከእስር ወደ አገር ተጠርንፎ እስከመመለስ የሚደርስ እንደሆነ ይናገራሉ።

በሕጉ መሠረት ጥላቻን መንዛት ፤ የግድያ ዛቻና ቅስቀሳ፣ የወሲብ ፊልም፤ ወንጀል ለመፍጠር መደራጀትን መሠረት ያደረገ ቅስቀሳን የሚያደርግ ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ ያስረግጣሉ።

እርሳቸው እንደሚሉት እንቅስቃሴው አሜሪካን አገር ብቻ ለሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን ትኩረት ያደረገ ነው። ይሁን እንጂ በሌሎች አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተመሳሳይ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ እየተነጋገሩ መሆናቸውንም ገልፀውልናል።

ጉዳዩን በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ንግግር አድርገው ከሆነ ጥያቄ ያነሳንላቸው አቶ አምሳሉ" ምንም ምክክርም ሆነ ንግግር አላደረግንም" በማለት የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት ብቻ እንቅስቃሴውን እንደጀመሩ ነግረውናል።

ከምክር ቤቱ ጋር ግንኙነት ባይኖራቸውም በሚኖሩበት ሜኒሶታ ግዛት ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደ ጀመሩ የነገሩን ደግሞ የአንድ ጥብቅና ቢሮ ባልደረባ የሆኑት አቶ ነጋሳ ኦዱዱቤ ናቸው።

እርሳቸውም ከአቶ አምሳሉ ጋር ተመሳሳይ ኃሳብ ነው ያላቸው፤ 'ፈርስት አመንድመትን' ጠቅሰው የጥላቻ ንግግር የሚያሰራጩን ከሕግ ፊት ማቅረብ እንደሚቻል ያረጋግጣሉ።

"በአሜሪካ የመናገርና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ለብዙ ዘመናት የተከበረ ነው፤ ይሁን እንጂ 'ፈርስት አሜንድመንት' ላይ የተወሰኑ ገደቦች አሉበት" ይላሉ።

ከእነዚህም መካከል የሀሰት ንግግር፣ ስም ማጥፋት፣ ለወንጀል የሚያነሳሱ ንግግሮች፣ ወደ ኃይል ተግባር የሚያነሳሱና የሌላውን መብት የሚጥሱ ንግግሮች በሕጉ ተገድበው ይገኛሉ።

ተፅዕኖው ኢትዯጵያ ውስጥ በሚታይ ድርጊት ግለሰቦችን አሜሪካ ላይ ፍርድ ቤት ማቅረብ የሚያዋጣ ክርክር ነው ወይ? ስንል የጠየቅናቸው አቶ ነጋሳ " የጁሪዝዲክሽን (የፍርድ ቤቶች የማየት ስልጣን) ጉዳይ አከራካሪ ነው። ነገር ግን ከሶ ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ መከራከር ይቻላል፤ ውጤቱ ኢትዮጵያ ነው ብሎ መከላከል ይቻላል" ሲሉ ይህ በፍርድ ሂደት እንደሚታይ ይናገራሉ።

ከዚህም ባሻገር አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የሚኖረው ጥገኝነት ጠይቆ በመሆኑ ይህንን ከሚቆጣጠረው 'አሜሪካ ኢምግሬሽን ሰርቪስ' (ዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ) በክስ ሂደቱ ሊካተት እንደሚችል ይናገራሉ።

"እንደ ኢትዮጵያዊያን አገሪቷ ወደ ፍቅርና ሰላም እንድታመራ የሞራል ግዴታ አለብን" የሚሉት አቶ ነጋሳ ነገሩን ወደ ህግ ከመውሰድ ይልቅ የሚያዋጣው የኢትዮጵያ ደህንነት ግድ እንደሚለው ዜጋ መመካከር ነው ይላሉ።

Via #BBC
🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የጥላቻ_ንግግሮች: የማህበራዊ ትስስር ድረ ገፅ የሆነው ትዊተር የጥላቻ ንግግር የሚነዙ ተጠቃሚዎችን ከገጹ እንደሚያግድ አስታወቀ። በተለይም ከሀይማኖት ጋር በተያያዘ ሰብአዊነትን የሚያጎድፉ ይዘት ያላቸው መረጃዎችና እና ጽሁፎችን የሚለቁ አካላትን ሙሉ በሙሉ ከገጹ እንደሚያግድ ነው ያስታወቀው። ኩባንያው ይህንን ለማድረግ የሚረዳው አዲስ #ህግ ማውጣቱም ተነግሯል።

በአዲሱ የትዊተር ሀግ መሰረት ከዚህ በፊት በገጹ የተለቀቁ የጥላቻ ንግግሮችም ከገጹ እንዲነሱ እንደሚደረግ ታውቋል። ሆኖም ግን ግለሰቦቹ የጥላቻ ንግግሮቹን የለቀቁት ህጉ ከመውጣቱ በፊት በመሆኑ ከገጹ እንደማይታገዱ ተነግሯል።

ትዊተር ከዚህ ቀደምም የመተግበሪያውን ህግና ደንብ የሚተላለፉ የሃገር መሪዎችና ፖለቲከኞች የሚያሰራጩትን መልዕክት ሊደብቅ መሆኑን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

ትዊተር ይህን ውሳኔ ያሳለፈው የተለያዩ ተፅዕኖ ፈጣሪ ፖለቲከኞች የመተግበሪያውን ህግና ደንብ በመጣስ ተገቢ ያልሆኑ መረጃዎችን ለተከታዮቻቻው በማሰራጨታቸው እንደሆነም ነው በወቅቱ የተጠቀመው።

ከዚህ በተጨማሪም #ሀሰተኛ መረጃዎች እየተበራከቱ በመምጣታቸው ተከትሎ ችግሩን ከስሩ ለማድረቅ ትዊተር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሀሰተኛ አካውንቶችን ማገዱም ይታወሳል።

ምንጭ፦ www.cnet.com---/#fbc/
🗞ቀን ሃምሌ 3/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተ.መ.ድ #የጥላቻ_ንግግር እንዲቆም ጥሪ አቀረበ!

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይህን ጥሪ ያቀረበው የኔልሰን ማንዴላ አለም አቀፍ ቀን በተከበረበት ግዜ ነው፡፡ በዓሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ማሪያ ፈርናንዳ ኢስፒኖሳ ጋሬስ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘረኝነት እና የጥላቻ ንግግርን መታገል ይኖርበታል ብለዋል፡፡

የደርባን የድርጊት መረሃ ግብር በመተግበር እና በቅርቡ በተ.መድ በጥላች ንግግር ላይ ያወጣውን ስትራተጂ በመጠቀም “ ዘረኝነት እና የጥላቻ ንግግርን ለማስወገድ መስራት ይኖርብናል” ብለዋል ፕሬዚዳንቷ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ደርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በበኩላቸው በዓለም ዙሪያ የጥላቻ ንግግር እየጨመረ በመጣበት በዚህ ወቅት የማዲባን የማህበራዊ ትስስርን ማጠናከር እና የሰላም ባሕልን ማዳበር ጥሪ መተግበር ጠቃሚ ነው ብለዋል፡፡

ኔልሰን ማንዴላን ስናስታውስ በጋር ለሰላም እና መረጋጋት፣ዘላቂ ልማትና ሰብአዊ መብትን በማረጋገጥ ነው ብለዋል አንቶኒዮ ጉተሬዝ፡፡ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1918 የተወለዱት ኔልሰን ማንዴላን ለመዘከር በየዓመቱ ጁላይ 18 የኔልሰን ማንዴላ አለም አቀፍ ቀን እየተከበረ ይገኛል፡፡

Via ዥንዋ/ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የጥላቻ_ንግግርን_እንግታ

አሳሳቢ የጥላቻ ገለጻዎች በአሜሪካ በሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት!

(Center for Advancement of Rights and Democracy-CARD)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Facebook

CNN ለአሜሪካ ህግ መምሪያ ምክር ቤት የቀረበ አንድ ሚስጥራዊ የፌስቡክ ኩባንያ ሰነድ መመልከቱን አሳውቋል።

ይኸው ሚስጥራዊ ሰነድ ፌስቡክ በኢትዮጵያ ግጭትን እያባባሰ እንደሆነ እያወቀ አንደችም ርምጃ እንዳልወሰደ የሚገልፅ ነው።

የፌስቡክ ኩባንያ ኢትዮጵያን "ለግጭት በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ የሆኑ ሀገራት" በሚለው ምድብ ያስቀመጣት ሀገር ናት።

የኩባንያው ሰራተኞች ፌስቡክ በኢትዮጵያ ግጭትን ለማባባስ እየዋለ መሆኑን ላቀረቧቸው ጥቆማዎች ኩባንያው ምላሽ እንዳልሰጠ ከሚስጥራዊው ሰነድ መመልከቱን CNN ዘግቧል።

ይኸው ሚስጥራዊ ነው የተባለው የፌስቡክ ሰነድ የውጭ መንግስታት እንዲሁም ድርጅቶች በኢትዮጵያ #የጥላቻ_ንግግር እና ግጭትን ለመስበክና ለማሰራጨት ፌስቡክን እንደተጠቀሙበት ያሳያል ሲል CNN ባወጣው ዘገባ ጠቅሷል።

ሙሉ የCNN ሪፖርት በዚህ ተያያዟል : https://edition.cnn.com/2021/10/25/business/ethiopia-violence-facebook-papers-cmd-intl/index.html?utm_content=2021-10-25T11%3A51%3A04&utm_term=link&utm_medium=social&utm_source=twCNN

Credit : CNN/WAZEMA

@tikvahethiopia
ተፈትኖ የወደቀው ፌስቡክ

ፌስቡክ ፤ በኢትዮጵያ ሶስት ብሔሮች ላይ ያነጣጠሩ #የጥላቻ_ንግግሮች ያዘሉ ማስታወቂያዎች ይለይ እንደሆነ የተሰጠውን ፈተና መውደቁ ተሰምቷል።

ፌስቡክን የሙከራ ማስታወቂያዎችን በመጠቀም የፈተኑት " ግሎባል ዊትነስ " እና " ፎክስ ግሎቭ " የተባሉ ሁለት ተቋማት ከቀድሞው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት መምህር ዳግም አፈወርቅ ጋር በመተባበር ነው። 

ምርመራው የተከናወነው የፌስቡክ የጥላቻ ንግግር መለያ ምን ያህል ጥሩ እንደሆነ ለመፈተን እና የኩባንያው የደህንነት መቆጣጠሪያ ስልቶች ሁከት የሚያባብሱ ማስታወቂያዎችን መከላከል ይችል እንደሁ ለመፈተሽ ነበር።

በአማርኛ ቋንቋ በፌስቡክ የተጻፉ 12 የከፉ የጥላቻ ንግግሮችን የለዩት ምርመራ አድራጊዎቹ እነዚሁኑ ይዘቶች ለኩባንያው እንደ ማስታወቂያ በማቅረብ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴው ለመለጠፍ ይፈቅድላቸው እንደሁ ሙከራ አድርገዋል።

የኩባንያውን የቁጥጥር አቅም ለመፈተሽ በምሳሌነት የተመረጡት የጥላቻ ንግግሮች የተካተቱባቸው ማስታወቂያዎች፤ የአማራ፣ የትግራይ እና የኦሮሞ ብሔሮች ላይ እኩል ያነጣጠሩ ናቸው።

በማስታወቂያዎቹ አረፍተ ነገሮች መካከል " ሰዎች እንዲገደሉ፣ እንዲራቡ ወይም ከአንድ አካባቢ እንዲጠፉ በቀጥታ ጥሪ የሚያደርጉ፤ ሰዎችን ከእንስሳት ጋር የሚያነጻጽሩ እና ሰብዓዊነት የጎደላቸው” ገለጻዎች እንዳሉበት ተገልጿል።

አብዛኞቹ የማስታወቂያዎቹ ይዘቶች የዘር ማጥፋት እንዲፈጸም ጥሪ የሚያቀርቡ መሆናቸውም ተገልጿል። ከእነርሱ ውስጥ አንዳቸውም ለመተርጎም ውስብስብ እንዳልነበሩ ተመላክቷል።

ግሎባል ዊትነስ ፤ " የትኞቹንም ማስታወቂያዎች አላተምናቸውም። የሚታተሙበትን ቀን ወደ ፊት እንዲሆን በማድረግ፤ ፌስቡክ ማስታወቂያዎቹን መቀበል እና አለመቀበሉን ካሳወቀን በኋላ አጥፍተናቸዋል " ብሏል።

የጥላቻ ንግግሮቹ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴው ለህዝብ ይፋ አለመደረጋቸውን አረጋግጧል።

በምርመራው መሰረት ፌስቡክ የቀረበሉትን 12ቱንም የጥላቻ ንግግሮች በማስታወቂያ መልክ በገጹ እንዲቀርቡ ፈቃድ ሰጥቷል።

ሁሉም ማስታወቂያዎች ፌስቡክ በአጠቃቀም መመሪያው (community standards) የጥላቻ ንግግር ብሎ ከሚበይናቸው ውስጥ የሚካተቱ ናቸው።

በሙከራ ደረጃ ፌስቡክ የተፈተነባቸው ማስታወቂያዎች በማህበራዊ መገናኛ ዘዴው ላይ ለዕይታ ቢበቁ ኖሮ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከ57 አመታት በፊት የጸደቀውን ስምምነት የሚጥሱ ነበሩ።

ስምምነቱ ማናቸውም አይነት የዘር መድሎዎ ለማስወገድ የጸደቀ ነው።  

በድርጅቶቹ ምርመራ የተገኘው ውጤት በስተመጨረሻ የቀረበለት ፌስ ቡክ፤ ማስታወቂያዎቹ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴው እንዲታተሙ መፈቀድ እንዳልነበረበት ማመኑን ግሎባል ዊትነስ አሳውቋል።

ፌስቡክ ለኢትዮጵያ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች የደህንነት ቁጥጥሩን ለማጥበቅ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን መግለጹንም ምርመራውን ካከናወኑት ድርጅቶች አንዱ የሆነው ግሎባል ዊትነስ አመልክቷል።

Credit - www.ethiopiainsider.com

@tikvahethiopia