TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አልሰማሁም፤ አላየሁም እንዳትሉ...
(TIKVAH-ETHIOIA)

የጥላቻ ንግግር የዘር ማጥፋት ዋነኛ መሰረት ነው። የጥላቻ ንግግር ከጀርባው #ያላስተናገደ አንዳች አይነት የዘር ማጥፋት በዓለማችን አልተፈፀመም፡፡

#ናዚ በአይሁዳዊያን ላይ ከፍተኛ የዘር ማጥፋት መፈፀም ከመጀመሩ በፊት #ጀርመናዊያን በአይሁዶች ላይ የከፋ ጥላቻን እንዲያዳብሩ ሰፊ የፕሮፖጋንዳ መደላድልን ሰርቷል፡፡

#በሩዋንዳ በ1990ዎቹ መጀመሪያ ከደረሰው የዘር ማጥፋት ጀርባ #በሬዲዮ ፕሮፖጋንዳ ጭምር የታገዘ #የጥላቻ_ንግግር_ዘመቻ ነበር፡፡

(በተሾመ ታደሰ)

#StopHateSpeech

TIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በመላው ሀገሪቱ እያደረግን ያለነውን #የፀረ_ጥላቻ_ንግግር ዘመቻ #እንድትደግፉን እንለምናለን!!

ስልክ፦ 0919 74 36 30

🇪🇹ኑ ኢትዮጵያን በፍቅር እንገንባ🇪🇹

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በናይጄሪያ የዘር ግጭት ያሰጋል...

ኦባሳንጆ በናይጄሪያ የዘር ግጭት እንደሚያሰጋቸው ገለፁ፡፡ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚደንት የነበሩት ኦሊሴንጎል ኦባሳንጆ #በሩዋንዳ የተከሰተው አይነት የዘር ግጭት በናይጄሪያ እንዳይከሰት ስጋት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡

ኦባሳንጆ አሁን በስልጣን ላይ ለሚገኙት ፕሬዚደንት ሞሃመድ ቡሃሪ በፃፉት ይፋዊ ደብዳቤ ‹‹ናይጄሪያ እጅግ በፈጠነ ሁኔታ ወደ አደገኛ ቁልቁለት እየተጓዘች ትገኛለች ፣ይህንን አደጋ ሊከላከል የሚችለውም የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ብቻ ነው›› ሲሉ ማስጠንቀቂያ አዘል መልእክት ማስተላለፋቸው ነው የተገለፀው፡፡ ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ የፉላኒ እረኞችና አርሶ አደሮች መሀከል በተቀሰቀሰ ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ይህም ብቻ ሳይሆን ከ 3 ቀናት በፊት ዮሩባ በመባል የሚጠራው ብሄረሰብ ከፍተኛ መሪ ሩቤን ፋሶራንቲ ልጅ የሆኑት የ58 አመቷ ኦሊኩንሪን ግድያ ተከትሎ ብዙዎችን ከስጋት ከቷል፡፡

የቀድሞው ፕሬዚደንት ኦሊሴንጎል ኦባሳንጆም ከቀናት በፊት ባደረጉት ንግግር ‹‹ይህ በቀላሉ የሚታይ ጉዳይ አይደለም…ሀገሪቱን በሩዋንዳ ለተከሰተው አይነት የዘር ፍጅት የሚያጋልጥ ነው›› ሲሉ ገልፀው ነበር፡፡

በትላንትናው እለትም ጉዳዩ ያሳሰባቸው ኦባሳንጆ የተለያዩ ጎሳዎች በጥላቻና ቂም ለበቀል እየተነሳሱ ነው…ይህም እጅጉን አስጊ ነው ሲሉ ለፕሬዚደንት ቡሃሪ ማስጠንቀቂያ አዘል ደብዳቤ መፃፋቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

Via CTGN/zamiradio/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት #በሩዋንዳ 806 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁሉም ከኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia