TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ስልክ ሻጮቹ ተያዙ‼️

በሰቆጣ ከተማ ሦስት #ፓኪስታናውያን በሕገ ወጥ የሞባይል ሽያጭ ተሰማርተው እጅ ከፈንጅ ተያዙ፡፡
.
.
‹‹ሦስት ፓኪስታናውያን በሕገ ወጥ #የሞባይል_ሽያጭ ተሰማርተው እጅ ከፈንጅ ይዣለሁ።›› የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት

‹‹ፓኪስታናውያኑ የሸጡልን ሞባይሎች ሲም ሲገባ የማይሠሩ ናቸው።›› ገዥዎች
.
.
ከሁለት ቀናት በፊት በሰቆጣ ከትመው ‹‹መንገደኞች ነን፤ ገንዘብ #አጥሮን›› በማለት አገልግሎት የማይሰጡ ሞባይል የሚሸጡ ሦስት ፓኪስታናውያንን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ደጀን ወዳጅ አስታወቁ።

ፓኪስታናውያኑ ተጠርጣሬዎች የተያዙት በሰቆጣ ከተማ ነጋዴዎች ሱቅ ድረስ በመሄድ ‹‹ገንዘብ አጥሮን ነው፤ ግዙን›› እያሉ ሲዘዋወሩ ነው። ነዋሪዎችም የገዙት ሞባይል የማይሠራ በመሆኑ ‹‹ይጣራልን›› ማለታቸውን ተከትሎ ሕጋዊ ፍተሻ መደረጉ ታውቋል። በፍተሻውም 26 ስማርት ስልኮች፣ 52 ሺህ የኢትዮያ ብር፣ መጠኑ ያልተገለፀ የፈረንሳይ ገንዘብ እና 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላሮችን ይዘው ተገኝተዋል።

ተጠርጣሬዎች ስልኮችን ከገንዘብ በተጨማረ በወርቅ እየቀየሩም በመያዛቸው በቁጥጥር ሥር ውለዋል፤ ሲመረመሩም ግንበኞች እንጂ ተንቀሴቃሽ ነጋዴዎች እንዳልሆኑ ተረጋግጧል።

ኢንስፔክተር ደጀን ‹‹ፖሊስ ከኅብረተሰቡ ያገኘውን ጥቆማ እና ቅሬታ ተከትሎ ተጠርጣሬዎችን በሕግ እንዲጠየቁ የማድረጉን ሥራ ጀምሯል›› ሲሉ ለአብመድ ተናግረዋል።

አብመድ ያነጋገራቸውና ስማርት ስልኩን ገዝተው እንደማይሠራ ለፖሊስ ካመለከቱት መካከል አቶ መርሻ ገብረኪዳን እና ታደሰ መልኩ ‹‹በየሱቃችን መጥተው ግዙን እያሉን ነበር›› ብለዋል።

‹‹ሦስቱ ፓኪስታናውያን የሸጡልን ሞባይሎች ሲም ሲገባ የማይሠሩ ናቸው። ‹20 ሺህ ብር የሚሸጥ ሞባይል ነው፤ ገንዘብ ስላጠረን ግዙን› ብለው 5 ሺህ ብር ገዛን፤ ግን አይሠሩም ነበር፡፡ በኋላ ላይ በየሱቁ ሌሎችንም ግዙን ሲሉ ለፖሊስ አመልክተናል›› ብለዋል።

የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊሰ ጽሕፈት ቤት ኃላፊው ‹‹ድርጊቱ ‹ነጭ ስለሆንን አንጠረጠርም› ብለው አስበው እንደነበር ያመላክታል፤ ይሁን እንጂ ደሴ እና መቀሌ ተመሳሳይ ሥራ መሥራታቸውን መረጃዎች ያሳያሉ›› ብለዋል።

ኢንስፔክተር ደጀን ወንጀሉ ወደሌሎች ከተሞች እንዳይስፋፋ ኅብሰተሰቡ ያደረሰው መረጃ የሚመሠገን እንደሆነም ገልጸዋል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia