TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ህፃን ሚሊዮን🔝

ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ #ዝናሽ_ታያቸው እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ህጻን ሚሊዮንን #በጉዲፈቻ ለማሳደግ ያቀረቡት ጥያቄ በፍርድ ቤቱ ተቀባይነት አገኘ።

ቀዳማዊ ቤተሰቡ ህጻን #ሚሊዮንን ከክበበ ህጻናት ማሳደጊያ ተቀብሎ #ለማሳደግ ጥር 14 ቀን 2011 ዓ.ም ለፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 7ኛ የወንጀል ችሎት የህጻናትና ሴቶች ጉዳይ በፅሁፍ ማመልከቻ አቅርቦ ነበር። በማመልከቻቸው አመልካቾች የተፈራረሙበት የጉዲፈቻ ውል #እንዲጸድቅላቸው ጠይቀዋል።

ቀዳማዊ ቤተሰቡ ለህጻኑ #መልካም አስተዳደግ እንደሚሰጥና ህጻኑን ለማሳደግ በቂ ኢኮኖሚያዊ አቅም እንዳለው ጠቅሷል። ፍርድ ቤቱም ህጻን ሚሊዮን ከሁለት አመት እድሜ በታች በመሆኑ ችሎት ፊት ቀርቦ አስተያየት መስጠት ስለማይችል ችሎቱ የተለያዩ ማስረጃዎችን መርምሮ፥ አመልካቾች ህጻኑን በጉዲፈቻ ቢያሳድጉት ችግር የለውም ወይም መልካም ነው ብሎ በመወሰን ጥር 14 ቀን 2011 ዓ.ም የተፈራረሙትን ውል ተሻሽሎ በወጣው የቤተሰብ ህግ 213/92 አንቀጽ 93 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት አጽድቆላቸዋል።

የውሳኔውን ግልባጭም ጉዳዩን ችሎት ፊት ቀርበው ለተከታተሉት ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው እንዲደርሳቸው ተደርጓል። የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ለቀዳማዊ ቤተሰቡ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። አያይዘውም በጉዲፈቻ ልጅ ለማሳደግ መወሰናቸው ለሌሎች አርዓያ እንደሚሆንና ልጅ ማሳደግ ትልቅ ሃላፊነት መሆኑን እንዲሁም ህጻናትን በጉዲፈቻ ለማሳደግ ሁሉም እንዲያስብ ያደርጋል ብለዋል።

በእድሜያቸው ሶስት መንግስታት ማየታቸውን ያነሱት ፕሬዚዳንቷ ከፍተኛ የሃገር መሪዎችና ሃላፊዎች ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸውን ሲያስፈጽሙ አይተው እንደማያውቁም ተናግረዋል። ቀዳማዊት እመቤቷ #ችሎት ፊት ቀርበው ጉዳያቸውን ማስፈጸማቸው ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል መሆኑን ያመላክታልም ነው ያሉት።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia