TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተማሪዎችን ፈተና የሚያጣራ ቡድን ወደ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አግልግሎት መላኩን ዛሬ አስታወቀ። የ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የክልሉ ተማሪዎች የውጤት ችግር መግጠሙን ተከትሎ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል ብሏል። የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ችግሩን ለመፍታት በርካታ ተግባራትን ሲፈጽም መቆየቱን ገልጾ በአሁን ሰዓት ፦ 👉 ከክልሉ ትምህርት…
የ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ሂደት ላይ የቀረቡ ቅሬታዎችን እንዲያጣራ ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተላከው ኮሚቴ ምንድነው ያለው ?

የ2013 የትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት አስመልክቶ የአማራ ክልል ትምህርት ባቀረባቸው ቅሬታዎች ላይ የተደረሰበት ሂደት ኮሚቴው ለህዝብ አሳውቋል።

በዚህም መሰረት ፤ በጦርነት አውድ ውስጥ ቆይተው ፈተና እንዲወስዱ የተደረጉ በክልሉ የሁሉም ዞን ተማሪዎች በውጤታቸው ላይ የተለየ ተፅዕኖ የተፈጠረ መሆኑ እና ጉዳዩ በልዩ ሁኔታ መታየት እንዳለበት #ከትምህርት_ሚኒስቴር ጋር አስፈላጊው መግባባት መፈጠሩን ገልጿል።

በትምህርት ቢሮው በኩል በጦርነት ተጽዕኖ ምክንያት ውጤታቸው የቀነሰባቸው ተማሪዎች ዝርዝር መረጃ እና አስፈላጊ ማስረጃዎች ሁሉ ለትምህርት ሚኒስቴር መቅረቡን ገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴርም በቀረበለት መረጃ እና ማስረጃ መሰረት ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ እያየው እንደሆነና ውሳኔውን #በቅርብ_ቀናት የሚያሳውቅ መሆኑን ኮሚቴው ለህዝብ አሳውቋል።

ሌላው ኮሚቴው የተለያዩ መረጃዎችን አደራጅቶ ወደ ፈተናዎች ኤጀንሲ በመሄድ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምርመራ ያደረገ ሲሆን የደረሰበትን በዝርዝር አሳውቋል ፤ (በዚህ ያንብቡ https://telegra.ph/Amhara-Education-Bureau-04-15)

ተማሪዎች ፣ ወላጆች እና መላው ማህበረሰብ የትምህርት ሚኒስቴርን የመፍትሄ ሃሳብ በትግስት እንዲጠብቅ ኮሚቴው ጥሪውን አቀርቧል፡፡

በሌላ በኩል ፤ የ2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በተፈጠረው ችግር ሳይዘናጉ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ እንዲዘጋጁ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ጥሪውን አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" በትግራይ ክልል ካሉ ብፁዓን አባቶች ጋር  የተፈጠረውን ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት እየተሠራ ነው " - የሰላም እና የስምምነት ኮሚቴ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰላም እና ስምምነት ኮሚቴ ፤ በትግራይ ክልል ካሉ ብፁዓን አባቶች ጋር የተፈጠረውን ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት እየተሠራ እንደሆነ ዛሬ አሳውቋል።

ኮሚቴው ፤ " በክልል ትግራይ የሚገኙ ብፁዓን አባቶቻችን ለሃይማኖታቸው አንድነትና መስፋፋት እንዲሁም ለቀኖና ቤተ ክርስቲያን መጠበቅ የከፈሉትን መስዋዕትነት መሠረት በማድረግ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናቸው አንድነትና ሉዓላዊነት በጽናት በመቆም ተፈጠሩ የሚባሉ ችግሮችን ሁሉ በዝርዝር ለማቅረብ ለውይይት ዝግጁ እንድትሆኑ " ሲል ጥሪ አስተላልፏል።

የሚያቀርቧቸውን የውይይት ነጥቦችን መሠረት በማድረግ ችግሮቹን በስምምነት ለመፍታት ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናን ዝግጁ መሆኗን ኮሚቴው #አረጋግጧል

በዚህም የውይይትና የሰላም መልእክት ቤተ ክርስቲያኗ ያስተላለፈችውን ጥሪ በመቀበል በትግራይ ያሉ ብፁአን አባቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውይይትና ለስምምነት ዝግጁ እንዲሆኑ ጥሪ የቀረበ ሲሆን #በቅርብ ቀናት ውስጥ የሰላም ልዑክ ለውይይት ወደ ክልል ትግራይ መቐለ ከተማ እንደሚጓዝ ኣሳውቋል።

በዚህም በጋራ በሚደረገው ቦታና ጊዜ የውይይትና የስምምነት ጉባኤ የሚደረግ ይሆናል ብሏል።

የፌዴራል መንግሥትና የክልል ትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርም ችግሩ በሰላማዊ መንገድና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በጠበቀ መልኩ መፍትሔ ያገኝ ዘንድ የሚደረገውን ጥረት ሁሉ በመደገፍና ለውይይቱ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር አስፈላጊውን ትብብር ጥሪ ቀርቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia