TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ItsMyDam #ItsOurdam #GERD

"እኔ እናት ነኝ ለልጄ የተሻለች አገር እፈልጋለሁ! ሰላም እፈልጋለሁ! ለዚህም ካለኝ ላይ ለህዳሴው የምችለውን አድርጌያለሁ። ተማሪ ሆኜ የ3 ወር ቁርሴን፣ ሠራተኛም ሆኜ የ3 ወር ደሞዜን ሰጥቻለሁ። በህዳሴው የመጣ በአይኔ መጣ! ወገኖቼ እኛ እርስ በእርስ ሰንባላ ለጠላት ደስታ ነው፡፡ ሁሉንም ትተን አንድ ሆነን ስለ ህዳሴው እንቁም! የአድዋን ድል ማክበር ብቻ ሳይሆን አድዋን እንድገም መባላት ትተን ለሠላም ለብልፅግና እናብር ያኔ ጠላትም ይፈራናል።" - #GenetHailu

#ItsMyDam #ItsMyBlood
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD

"የኅዳሴ ግድብ ድርድር ከምርጫ በኋላ ይከናወን" - አቶ ጃዋር መሀመድ

ምርጫ 2012 እስከሚካሄድ ድረስ ኢትዮጵያ ከኀዳሴ ግድቡ ድርድር እንድትወጣ ፖለቲከኛ አቶ ጃዋር መሀመድ ጥሪ አቀረቡ። ዩናይትድ ስቴትስ ምርጫውንና በቅርቡ በአበዳሪ የገንዘብ ተቋማት ለኢትዮጵያ ቃል የተገባውን ብድር በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ላይ ጫና ለማሳደር እየተጠቀመችበት ነው ብለዋል ፖለቲከኛው።

በዋሽንግተን ዲሲ በተደረገው የመጨረሻው ዙር ድርድር ላይ ኢትዮጵያ እንዳትሳተፍ ጠቅላይ ሚንስትሩ መወሰናቸው ትክክል ነበር ያሉት ፖለቲከኛው ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ በአቋማቸው ሊፀኑ ይገባል ብለዋል።

ግብፅና ሱዳን አስቸጋሪ የአገር ውስጥ ጉዳይ በገጠማቸው ወቅት ድርድሩ ተቋርጦ እንደነበረ ያስታወሱት አቶ ጃዋር መሃመድ፤ ኢትዮጵያ ያሉባትን አንገብጋቢ የአገር ውስጥ ጉዳዮች (ምርጫው 2012ን ጨምሮ) እስከምታጠናቅቅ ድርድሩ ላልተወሰነ ጊዜ ሊራዘም ይገባል ብለዋል። መንግሥት የድርድሩን ጉዳይ ወደ አፍሪካ ኀብረት በመውሰድ የአባል አገራቱን ድጋፍ እንዲሰበስብም አቶ ጃዋር መሃመድ መክረዋል።

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam #GeduAndargachew

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው የአሜሪካ ግምዣ ቤት በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ድርድር ላይ ያወጣው መግለጫ "ተቀባይነት የሌለው እና እጅጉን ለአንድ ወገን ያደላ ነው" ሲሉ ወቅሰዋል።

#EsheteBekele
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam #NAMA #GERD

ታላቁ የህዳሴ ግድብ የዓለም አቀፍ ድጋፍ እና እርዳታን ለማግኘት ማስያዣ መሆን እንደሌለበት አብን አስታወቀ።

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ጣሂር መሃመድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 እንዳሉት ግብጽ እስካሁንም የ1929ኙና የ1959ኙ ኢትዮጵያን ያገለለዉ ስምምነት እንዲመለስ ነዉ የምትፈልገዉ ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ጠንካራ አቋም ሊኖረዉ ይገባል ብለዋል።

ይህ የሉዓላዊነት ጉዳይ በመሆኑ መንግስት ከህዝቡ ጋር መምከርና ቀደም ሲል በነበረበት አቋም ጸንቶ ነዉ መቀጠል ያለበት ብለዋል፡፡

ንቅናቄዉ አሁን ላይ በተለይም ከአረቡ ዓለም ጋር መስመር የሳቱ የሚመስሉ ግንኙነቶች አሉ ብሎ እንደሚያምን ገልጾ በፖለቲካ ዓለም ዉስጥ ፍጹም ታማኝ ወዳጅ ባለመኖሩ ግንኙነታችን ግልጽ መስመር ሊኖረዉ ይገባል ብሏል፡፡

#ኢትዮኤፍኤም #ሙሉቀንአሰፋ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 80ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ስለተወሰነዉ የቋንቋ ልማትና አጠቃቀም ረቂቅ ፖሊሲ ተጨማሪ ማብራሪያ፦

እንደሚታወቀው አማርኛ የፌደራሉ የሥራ ቋንቋ በመሆኑ እርስ በእርሳችን እንድንግባባ በማደረግ ረገድ ሚናው ትልቅ ነው።

አማርኛ ቋንቋ በሀገር ወስጥ ያለው የተናጋሪዎች ብዛትና የተደራሽነት ስፋት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ አንድ የፓለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ተግባቦትን ለማሳለጥ ተጨማሪ የሥራ ቋንቋዎችን መጠቀም አንዱ መንገድ ነው።

ለዚህም በሀገር ውስጥ ያለውን ትሥሥር ከማጎልበት አልፈው ከጎረቤቶቻችን ጋር ጭምር የሚያስተሣሥሩንን ቋንቋዎች ከአማርኛ ጎን ለጎን ብንጠቀም ይበልጥ ተጠቃሚ እንሆናልን።

ይሄንንም የዘርፉ ባለሞያዎች ሲመክሩ ኖረዋል። የአማርኛ ቋንቋን ይበልጥ በማሳደግ ተጨማሪ ቋንቋዎችን ለፌዴራል የሥራ ቋንቋነት መጠቀም፣ በሌሎች ሀገራትም እንደታየው ሀገራዊ ጠቀሜታው የላቀ ነው።

ስለሆነም አፋን ኦሮሞ፣ ትግርኛ፣ ሶማሊኛ እና አፋርኛ የፌደራል የሥራ ቋንቋዎች ቢሆኑ ልሳነ ብዙ ሀገረ መንግሥት ከመገንባትም ባሻገር ውስጣዊና ቀጣናዊ ትሥሥር ያፋጥናል። ብሎም ኅብራዊውን የብሔረ መንግሥት ግንባታ ያቀላጥፋል። የሕዝቦችንም መግባባት ያሳድጋል።

አራቱ ለተጨማሪ የፌደራል የሥራ ቋንቋነት የታጩ ቋንቋዎች፣ ማለትም አፋን ኦሮሞ፣ ትግርኛ፣ ሶማልኛ እና አፋርኛ በሀገር ወስጥ ከሽግግር ጊዜ ጀምሮ የክልል መንግሥታት የሥራ፣ የትምህርትና የአስተዳደር ቋንቋዎች በመሆን አገልግለዋል ።

ተጨማሪ ያንብቡ : https://telegra.ph/FBC-02-29

የጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተጨማሪ የፌደራል የስራ ቋንቋዎች...

በዛሬው ዕለት በተካሄደው የሚኒስትሮች ምክር ቤት 80ኛ መደበኛ ስብሰባ የቋንቋና ልማት የአጠቃቀም ፓሊሲ ማፅደቁ ይታወቃል። ይህም የኦሮሚኛ፣ የአፋርኛ፣ የትግርኛና የሶማሌኛና አፋርኛ ቋንቋዎች ከአማርኛ ቋንቋ ጋር በአንድ ላይ የፌደራል የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል ነው የተባለው፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahethiopia
#Mekelle

ከቀናት በፊት በመንግስት ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር የተፈቱት የቀድሞው የኢንሳ ም/ዳይሬክተር ሌተናል ኮሎኔል ቢንያም ተወልደ እንዲሁም ዩኩኖኣምላክ ተስፋይ ዛሬ መቐለ ሲገቡ በመቐለ ነዋሪዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

#ቲክቫህ_ቤተሰቦች_መቐለ

PHOTO : BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አዲስ ለሚገነባው የሀዲስ አለማየው ልዩ አዳሪ ትምህርት ዛሬ ላይ የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን እየተካሄደ ይገኛል! በአንጋፋው ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ ተሰይሞ በትውልድ መንደራቸው በደብረማርቆስ ከተማ በ100,000 ካሬ ሜትር ላይ ሊገነባ የታሰበውና 2,000 የሚያህሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ለተባለለት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ማስገንቢያ አስመልክቶ ዛሬ በኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴል የገቢ ማሰባሰቢያ…
#UPDATE

ለሀዲስ ዓለማየሁ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ በመጀመሪያው ዙር ከ72 ሚሊዮን ብር በላይ ቃል ተገባ!

ዛሬ በአዲስ አበባ ኢንተር ኮንቲነንታል ሆቴል በተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ የመጀመሪያ "ቴሌቶን" ለግንባታው ከሚያስፈልገው 200 ሚሊዮን ብር ውስጥ ከ 72 ሚሊዮን ብር በላይ ቃል ተገብቷል።

ሁለት ባለሀብቶች ደግሞ ከትምህርት ቤቱ የሁለት ሕንፃዎችን ግንባታ ከነቁሳቁሳቸው እንደሚችሉ ቃል ገብተዋል። ለግንባታው የደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር 100 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ መስጠቱም ታውቋል።

ለአጠቃላይ ግንባታው 200 ሚሊዮን ብር ለሚያስፈልገው ልዩ የአዳሪ ትምህርት ቤት በቀጣይ በደብረ ማርቆስ፣ በባሕር ዳር፣ በጎንደር፣ በሰሜን አሜሪካና በአውሮፓ ከተሞች የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን እንደሚያዘጋጅ ታውቋል።

#አብመድ

PHOTO : #TikvahFamily
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ህዝብ አሸብሮ የዩትዩብ ገንዘብ መሰብሰብ...

ከዩትዩብ ገንዘብ ለማግኘትና እውቅና ለማትረፍ ሲባል ብቻ ያልተፈጠሩ ነገሮችን እንደተፈጥሩ አስመስሎ፣ እንዲሁም ተመልካች ለማግኘት ሲባል የተጋነኑ ርእሶችን በመጠቀም ህዝቡን በማህበራዊ ሚዲያ የሚያሸብሩ አካላት አንድ ሊባሉ ይገባል።

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና የጤና ሚኒስቴር በየወቅቱ በቂ መረጃ በዋና ዋና መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ ለህዝብ እያደረሱ ነው።

የተጠርጣሪዎችን ናሙና የመረመሩ ይመስል፤ እንዲሁም የጠለቀ የህክምና እውቀት ያላቸው ይመስል የተሰሳተ መረጃ የሚያሰራጩ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ከደርጊታቸው ቢቆጠቡ መልካም ነው።

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ምርመራ አድርገው ለህዝብ ማሳወቅ ያለባቸው አካላት እያሉ ከመሬት እየተነሱ ህዝቡን ማሸበር ተገቢ አይደለም።

ኮሮና ቫይረስ ሀገሪቱ ውስጥ ቢገባ እንኳን መናገር ያለባቸው፣ መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች ማሳወቅ የሚገባቸው የጤና ባለሞያዎች እያሉ ጭምጭምታዎችን ብቻ እየሰሙ ማራገቡም ተገቢ አይደለም።

የቲክቫህ ቤተሰቦች በማህበራዊ ሚዲያዎች በተለይም በፌስቡክ እና ዩትዩብ ላይ የሚዘዋወሩትን ያልተረጋገጡ መረጃዎች አይተው የታዘቡትን እያካፈሉ ይገኛሉ።

በማህበራዊ ሚዲያ ህዝብን የሚያሸብሩ ፣ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች መበራከታቸው እንዳሳዘናቸው በላኩት የፅሁፍ መልዕክቶች ገልፀዋል።

#TikvahFamily

ሀሳብ መቀበያ : @tikvahethiopiaBot

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NewsAlert

በአሜሪካ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ [#COVID19] ሞት መመዝገቡ ከደቂቃዎች በፊት ተሰምቷል። ሞቱ የተመዘገበው በዋሽንግቶን ስቴት እንደሆነም ተነግሯል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና!

አንጋፋው የማስታወቂያ ባለሞያ ጋሽ ውብሸት ወርቃለማሁ ባደረባቸው ፅኑ ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከደቂቃዎች በፊት ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ውስጥ ህይወታቸው ማለፉን ታዲያስ አዲስ የተሰኘው የሬድዮ ፕሮግራም ዘግቧል።

#AccessAddis
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ የማስታወቂያ አባት አርፈዋል!

የአንበሳ ማስታወቂያ ባለቤትና የዘርፉ ግንባር ቀደም ውብሸት ወርቃለማሁ በቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ህክምና ሲረዱ ቆይተው ከደቂቃዎች በፊት ህይወታቸው አልፏል።

ጋሽ ውብሸት በጥቁር ካባቸው ተውበው በአገራዊ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባልነት ፣ በቻምበር ኦፍ ኮሜርስ ሃላፊነት እንዲሁም ፣ በቀይ መስቀልና ደም ባንክ አምባሳደርነት አገልግለዋል።

ነፍስ ይማር!

#GetuTemesgen
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TIKVAHFAMILY #HATRICKSPORT

የሀገር ውስጥ የእግር ኳስ እንቅስቃሴዎችን ፤ ቁጥራዊ መረጃዎችን ፤ የወሩ ምርጥ ሽልማቶችን ባማረ አቀራረብ ወደ እናንተ ቤተሰቦቻችን ለማድረስ ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ የሚገኘው ቲክቫህ ስፖርት ከዛሬ ጀምሮ በይፋ ከተባባሪ አጋራችን ሀትሪክ ስፖርት ድህረ-ገፅ ጋር በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰናል።

www.Hatricksport.net

በዚህም መሰረት ያልተሰሙ የሀገር ውስጥ መረጃዎችን ፤ የተጫዋቾች ዝውውሮች ፤ ቁጥራዊ መረጃዎች ፤ ቃለ መጠይቆች እንዲሁም ሌሎች አበይት ጉዳዮች ወደ እናንተ ቤተሰቦቻችን በጋራ የምናደርስ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ኮሮና ቫይስ የቤት እንስሳትን ባለቤት አልባ እያደረገ ነው!

በጎ አድራጊዎች በቻይና በኮሮናቫይስ ምክያት የሚጣሉ የቤት እንስሳትን መሰብሰብ ከአቅማችን በላይ ሆነ እያሉ ነው። በቫይረሱ የተያዙ እና በለይቶ ማቆያ የሚገኙ ሰዎች የቤት እንስሳት በተለይም ውሾች እየተጣሉ ይገኛሉ።

ከዚህ በተጨማሪ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው እንዲወጡ ስለማይፈቀድላቸው የእንስሳት ምግብ መግዛት አልቻሉም። በዚህም የቤት እንስሳቱ እየተጣሉ ይገኛሉ። በኮሮና የሞቱ ሰዎች ባለቤት የነበሩ እንስሳትም የሚደርሳቸው እጣ ተመሳሳይ መሆኑ ተጠቁሟል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ኮሮና ቫይረስ ሶስት ተጫዋቾችን ይዟል !

በጣልያን እግር ኳስ ልይ ትልቅ ጫናን እያሳደረ የሚገኘው ይህ ቫይረስ ሶስት ተጫዋቾች መያዛቸው ይፋ ተደርጓል ::

የሦስተኛ ደረጃ የጣሊያን እግር ኳስ ክለብ የሆነው ፒያኔሱ ክለብ ሶስት ተጫዋቾችን በኮሮና ቫይረስ በሽታ መያዛቸውን በትላንትናው ዕለት አረጋግጠዋል ፡፡

@tikvahethsport @kidusyoftahe @GoitomH
#ATTENTION

በቅርቡ በሰሜን ሜጫ ወረዳ ተከስቶ የነበረው የአንበጣ መንጋ ከትናት በስቲያ ጀምሮ በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰሜን አቸፈር ወረዳ 8 ቀበሌዎች ማለትም በእስቱሚት፣ በቁንዝላ፣ ለግዲ፣ ጉግ፣ አንበሸን ወንበሪያ እየሱስ እና ቆንገሪ ቀበሌዎች ላይ የአንበጣ መንጋ ተከስቷል፡፡

መንጋው በስቱሚትና በቁንዝላ ቀበሌዎች ባልደረሱ ሰብሎች ላይ በጓያ እና በአትክልትና ፍራፍሪዎች ላይ ቀላል ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡ ሁሉም የወረዳው የህብረተሰብ ክፍል ወደ ሌሎች ቀበሌዎች ከመዛመቱ በፊት ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ADWA

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የዐድዋ ድል መታሰቢያ በዓልን በተመለከተ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያስተላለፉት መልዕክት!

#PMOEthiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia