TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62K photos
1.58K videos
216 files
4.31K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewsAlert

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ሶስት የሚኒስትርነት ሹመቶችን ሰጡ፦

- ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ [የትምህርት ሚኒስትር]

- አቶ መላኩ አለበል [የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር]

- ዶ/ር አብርሃም በላይ [የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር]

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

- ዛሬ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ለሦስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ወደ የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች አቅንተዋል።

- ዶ/ር ዐቢይ በአቡዳቢ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼህ አብደላ ቢን ዛይድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

- ጠ/ሚ ዶ/ር በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ የተለያዩ አገራት ከተወጣጡ 300 የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በዱባይ ውይይት አካሂደዋል።

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ አንድም ሰው የለም!

በአፍሪካ እስከ የካቲት 6 ቀን 2012 ከቀኑ 8 ሰዓት ድረስ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ አንድም ሰው አለመኖሩን በአፍሪካ የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማእከል (CDC) ዳይሬክተር ዶ/ር ጆን ንኬንጋሶንግ ተናግረዋል። ዳይሬክተሩ ኮሮና ቫይረስን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በአፍሪካ እስከ የካቲት 6 ቀን 2012 ከቀኑ 8 ሰዓት ድረስ በኮሮና ቫይረስ የተረጠሩ 51 ሰዎች እንደነበሩ ተናግረው፣ ሁሉም ከቫረሱ ነፃ መሆናቸው በምርመራ ተረጋግጧል ብለዋል፡፡ የኮሮና ቫይረስ መንስኤ በንድፈ ሐሳብ ደረጃ የውኃ ድብ ወይም የሌሊት ወፍ ሊሆን ይችላል ከማለት ውጭ በትክክል መንስኤው እስካሁን አለመታወቁን ጠቁመዋል፡፡

#EBC
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
"በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎች ህግን በተከተለ መልኩ እልባት እንዲያገኙ ይደረጋል" - ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

የኢህአዴግ የጥልቅ ተኃድሶ ግምገማ በተለያዩ ወንጀሎች የተከሰሱ የመንግስት ባለስልጣናት እንዳሉና አብዛኞቹ የትግራይ ክልል ተወላጆች መሆናቸውን በማስታወስ ጉዳያቸው በእርቅ እና በይቅርታ እንዲታይ የትግራይ ክልል የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ለጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ጥያቄ አቅርበው ነበር።

ጠቅላይ ሚንስትሩም ከዚህ ቀደም በተለያየ ምክንያት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎች ህግን በተከተለ መልኩ እልባት እንዲያገኙ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡ ወንጀለኝነትን ከብሄር ጋር ማያያዝ አይገባም ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ማንኛውም ሰው በሰራው ወንጀል በህግ ይዳኛል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ከስልጤ ዞን ከተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ለመወያየት ወራቤ ገብተዋል፡፡

ከሁሉም የዞኑ ወረዳዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ውይይቱ ለማድረግ በቂ ዝግጅት ተደርጓል፡፡

በውይይቱም የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ትኩረት ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

#PMOEthiopia #EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የኢትዮጵያ መንግስት ለ60 ጉዳያቸውን በህግ ሲከታተሉ ለነበሩ ተጠርጣሪዎች ምህረት ማድረጉን በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክረተሪ አቶ ንጉሱ፦

"መንግስት በቻይነት እና በሆደ ሰፊነት የተለያዩ ጥያቄዎች በመኖራቸው እና ትምህርት ስለተወሰደበት ለ60 ዜጎች ክሳቸው እንዲቋረጥ ወስኗል።"

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ምህረት የተደረገላቸው 60 ዜጎች ክሳቸው የተቋረጠበትን የሕግ አግባብ እና የስም ዝርዝራቸውን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ነገ ዝርዝር መረጃን ይሰጣል።

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

"በጊንጪ ከተማ በሚገኝ የፖሊስ ካምፕ ላይ የቦንብ ጥቃት ደርሷል፤ የከፋ ጉዳት ግን አላደረሰም" - ፖሊስ

በትናንትናው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ጊንጪ ከተማ በሚገኝ የፖሊስ ካምፕ ላይ የቦንብ ጥቃት ደርሷል።

በከተማው ትናንት ከምሽቱ 2 ሰዓት በደረሰው በዚህ ጥቃት በወቅቱ በስራ ላይ በነበሩ ሁለት የፖሊስ አባላት ላይ በጭስ የመታፈን መጠነኛ ጉዳት ከመድረሱ በቀር የከፋ አደጋ አለመድረሱን የክልሉ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ገልፀዋል።

ጥቃቱን በማድረስ የተጠረጠሩ ስድስት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አቶ ጌታቸው በተለይ ለኢቲቪ ተናግረዋል።

በጥቃቱ ተሳትፈዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች ማንነት እስካሁን በተደረገው ምርመራ አለመታወቁን ተናግረዋል።

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በቢሾፍቱ በሚገኘው የኢፌዴሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በዛሬው ዕለት 106 ለሚሆኑ ከፍተኛ መኮንኖች ሹመት እንደሚሰጥ ታውቋል።

በተጨማሪም በዛሬው ዕለት ላለፉት 6 ወራት በስልጠና ላይ የቆዩ የአየር ኃይል ወታደራዊ ፖሊስ አባላት ምረቃ እንደሚኖር ተገልጿል። የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ይልማ መርዳሳ ሹመቱን እንደሚሰጡ ተጠቁሟል።

የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ በስፍራው ተገኝተው ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ባለፉት 6 ወራት በተቋሙ ከፍተኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ሰራተኞችም ሽልማት ይበረከታል ነው የተባለው።

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GAMBELA

በጋምቤላ ክልል በኑዌር ብሄረሰብ ዞን በቀበሌ ሊቀመንበር መገደል ምክንያት የተቀሰቀሰ ግጭት ለ12 ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑ ተነገረ።

ቀስ በቀስ ወደ ጎሳ ግጭት የቀየረው በዚህ ሁከት 21 ሰዎች ሲቆስሉ፣ 400 ቤቶች ተቃጥለዋል፤ ከ300 በላይ የቤት እንስሳቶችም ተዘርፈዋል። በተጨማሪ የግጭቱ ሰለባ የሆኑ የ5 ቀበሌ ነዋሪዎች [7 ሺህ ሰዎች] ተፈናቅለዋል።

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን 858 የሚሆኑ ለአራት ወር ያሰለጠናቸው የክልል ልዩ ኃይል ሰራዊት አባላት በብር ሸለቆ መደበኛ ሠራዊት ማሰልጠኛ የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አሊ ዲኒ በተገኙበት ማስመረቁን ከፌዴራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ዓላማውም በክልሉ የሚካሄደውን 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ከማድረግ አንፃር ያለውን የሰው ኃይል እጥረት በመቅረፍ የክልሉንና የህዝቡን ፀጥታ እና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ በመጠበቅ በክልሉ ያለውን የህግ የበላይነት የበለጠ ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል።

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለሥልጣን የኮሮና ቫይረስን [COVID-19] ለመከላከል ትርፍ በሚጭኑ ታክሲዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ገልጿል፡፡

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ኬዝ 769 ደርሷል!

በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የተያዙ ሰዎች ቁጥር 769 መድረሱን የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቅርንጫፍ አስታውቋል፡፡ በግብጽ 210 ፣ በደቡብ አፍሪካ 150፣ በአልጄሪያ 82 ፣ በሞሮኮ 61 ፣ በቡርኪና ፋሶ 40፣ በቱኒዚያ 39፣ በሴኔጋል 38 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተገልጿል፤ ቀሪዎቹ 148 ታማሚዎች በ26 የአፍሪካ ሀገራት የሚገኙ ናቸው፡፡ በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽ ከተከሰተ በኃላ 19 ሰዎች ሲሞቱ ፣ 69 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸው ታውቋል፡፡

#EBC #WHO
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጣልያን!

"በሌላው ሀገር እየሆነ ያለውን የምትመለከቱ ከሆነ በእናተ በሀገራቹ ማድረግ ያለባችሁ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው። መጀመሪያ ምን ማድረግ እንዳለብን ግራ ተጋብተን ነበር አሁን ላይ ግን ምን እየሆነ እንዳለ አውቀናል። እኛ ጋር የሆነው በእናተ ላይ ሊሆን ይችላልና ለመግታት ማድረግ ያለባችሁን ከወዲሁ ጀምሩ አትቁሙ! የአንዱ ተሞክሮ ለሌላው ትምህርት ነውና ጥንቃቄን መሰረት አድርጋችሁ ተንቀሳቀሱ" - ዶ/ር ኢማኑኤላ #EBC

የኮሮና ቫይረስን [ኮቪድ-19] መግታት ቀላል ነው፦

- የእጅዎን ንፅህና በአግባቡ ይጠብቁ
- ሰዎች በተሰበሰቡበት አይሂዱ
- ማህበራዊ ርቀትዎን ይጠብቁ
- በተጨናነቁ የትራንስፖርት አመራጮችን አይጠቀሙ
- የጤና ባለሞያዎችን ምክር ያዳምጡ
- የጤና ሚኒስቴር መምሪያዎችን ይተግብሩ
- ስለ ኮቪድ ትክክለኛ መረጃ ከWHO፣ ከጤና ሚኒስቴር እና ከህበረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ብቻ ያግኙ!

ተጨማሪ ፦ 8335 / 952 ነፃ የስልክ መስመሮች ናቸው!

ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኝላችኃለን!
ሰላም እደሩ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BREAKING

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሞት መመዝገቡን ኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

አንዲት የ60 ዓመት ታማሚ መጋቢት 19 ፣ 2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ታይቶባቸው በለይቶ ማከሚያ ገብተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የነበረ ሲሆን በመጋቢት 22፣ 2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡ ይታወሳል፡፡

ይሁንና ከመጋቢት 22 አንስቶ ላለፉት ስድስት ቀናት በፅኑ ህክምና ላይ የነበሩ ሲሆን በዛሬው እለት ህይወታቸው አልፏል፡፡

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማውን ሀዘን ገልጾ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ተመኝቷል፡፡

#MoH #EPHI #EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TikurAnbessaSpecializedHospital

ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ክትትል የሚፈልጉ ተመላላሽ ታካሚዎቹ ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተጋላጭ እንዳይሆኑ በማሰብ ባሉበት አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ መጀመሩን አስታውቋል።

የሆስፒታሉ የሕክምና ባለሙያዎች በተመላላሽ ታካሚዎቹ ሞባይል ስልኮች ላይ በመደወል ማማከርን ጨምሮ አስፈላጊውን አገልግሎት እየሰጧቸው መሆኑን ሆስፒታሉ ገልጿል።

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጃንሜዳው አትክልት ተራ ነገ ስራ ይጀምራል!

አትክልት ተራ ሲሰጥ የነበረው የግብይት አገልግሎት ወደ ጃንሜዳ እንዲዛወር የከተማ አስተዳደሩ በወሰነው መሠረት ጃንሜዳን የማዘጋጀት ሥራው መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገልፀዋል።

በዚሁ መሠረት የአትክልት ተራ ከነገ መጋቢት 29/2012 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚዘጋ እና በጃንሜዳ የተዘጋጀው የአትክልት ግብይት ቦታ ሥራ እንደሚጀምር ያስታወቁት ምክትል ከንቲባው ነጋዴዎች እና በችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩ ዜጎች የኅብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ የተወሰነውን ይህን ውሳኔ ማክበር እንደሚኖርባቸውም አሳስበዋል።

#MayorofficeAA #EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዕድገት በህብረት ህንፃ የ2 ወር ኪራይ ነፃ አደረገ!

የምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን የተማፅኖ ጥሪ ተከትሎ ሰባራ ባቡር አካባቢ የሚገኘው ዕድገት በህብረት ህንጻ ባለቤቶች 150 ለሚሆኑ ተከራዮቻቸው ለሁለት ወር በነፃ እንዲገለገሉበት ፈቅደውላቸዋል።

ይህንንም ተከትሎ ምክትል ከንቲባው ለህንፃው ባለቤቶች ያላቸውን አክብሮት ገልፀዋል። ሌሎች አከራዮችም የእነሱን ፈለግ እንዲከተሉ ኢ/ር ታከለ ኡማ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከተማሪዎች የሚያገኙትን ገቢ የወቅቱ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገና ማህበረሰቡን በማይጎዳ የወርሃዊ ክፍያቸው በመግባባት ስሜት እንዲፈጸም በተለይም በቀጣዩቹ ሶስት ወራት የተማሪዎች ክፍያ ላይ ቢያንስ የ25 በመቶ ቅናሽ እንዲያደርጉ እንዲሁም በሌሎች አገልግሎቶች ላይ ቅነሳ ወይም ስረዛ እንዲደርጉ የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ማህበር ወስኗል - #EBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia