TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢትዮ ቴሌኮም ያደረገው ቅናሽ...

ኢትዮ ቴሌኮም ዛሬ ከጥዋት 4:00 ጀምሮ ደንበኞቹ እና አጋሮቹ እየተሳተፉበት የሚገኝ ልዩ ዝግጅት እያካሄደ ይገኛል።

በዚህም ፕሮግራም ላይ የብሮድባንድ ኢንተርኔት ላይ የታሪፍ ቅናሽ ማድረጉን አሳውቋል። በፕሮግራሙ ላይ የተገኙ የቤተሰባች አባላት የተደረገውን ስለተደረገው የታሪፍ ቅናሽ መረጃ እንዲኖራችሁ ከላይ እንደምትመለከቱት በፎቶ እያጋሯችሁ ይገኛሉ።

#TikvahFamily [Andinet]

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሪያድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ፦

• ደመወዝ ያልተከፈላትን ኢትዮጵያዊት 13, 000 ሣ.ሪ. እንዲከፈላት አድርጓል።

• ቀሪውን ደመወዟን 13,000 ሣ.ሪ. በቀጣዩ ሳምንት እንድታገኝ እደሚያደርግ አሳውቋል።

በቤት ሠራተኝነት በሳዑዲ አረቢያ ስታገለግል የነበረችው ኢትዮጵያዊት ጠይባ ከአሠሪዎቿ ጋር ስትሰራበት የነበረውን ደመወዝ ሳይከፈላት ይቀራል። የዜጎችን መብትና አያያዝ የሚከታተለው የኢፌዲሪ ኤምባሲ እህት ጠይባ የለፋችበትን እንዲሁም በአሰሪዎቿ ያልተከፈላትን የሥራዋን ዋጋ አስራ ሶስት ሺህ (13, 000 ሣ.ሪ.) እንዲከፈላት ማድረግ ተችሏል።

እህታችን ላለፉት ሁለት ኣመታት ከሁለት ወር በአንድ ሺህ ብር ደመወዝ ስትሰራ የቆየች በመሆኑ፣ አሰሪዋ በቀጣዩ ሳምንት ግማሹን ማለትም ቀሪውን አስራ ሶስት ሺህ የሳኡዲ ሪያል ቃል በገቡት መሰረት ገንዘቡን ለዜጋችን የሚያስረክቡ ይሆናል። ኤምባሲው እህት ጠይባ በቅርቡ ወደ አገር እንድትገባ የጉዞ ሰነድ እና ሌሎችንም ድጋፎች የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መልስ ያላገኘው የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ...

ታገቱ የተባሉ የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጉዳይ አሁንም በግልፅ ምላሽ አላገኘም። በተማሪዎቹ ጉዳይ ይፋዊ መረጃም አልተሰጠም።

ትላንት ከቪኦኤ ጋር ቆይታ ያደረጉት የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ለታ ተስፋዬ ተማሪዎቹን የማፈላለግ ጥረት መቀጠሉን ገልፀው፤ ተገኝተው ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ታገቱ የተባሉ ተማሪዎችን በተመለከተ ይገኙ አይገኙ እስካሁን ከቤተሰብም ሆነ ከመንግሥት የተሰጠ መግለጫ እንደሌለ ይታወቃል።

#VOA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Audio
በደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት ያለፋቸውን የትምህርት ክፍለ-ጊዜ ለማካካስ ዩኒቨርሲቲው ድጋፍ እያደረገላቸው መሆኑን ገልጿል።

ተማሪዎቹ ከተቋረጠ ከወር በላይ የሆነው የኢንተርኔትና ስልክ አገልግሎት እንዲመለስላቸውም ጠይቀዋል።

የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ለታ ተስፋዬ “ዩኒቨርሲቲው ወደ ቀድሞ መረጋጋቱ ተመልሶ በዚህ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎችን ለማስመረቅ እየሰራን ነው” ብለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

በዘንድሮው ዓመት በሀገሪቱ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በተፈጠሩ ግጭቶች ሳቢያ ትምህርታቸውን ጥለው ወደቤተሰቦቻቸው የተመለሱ በርካታ ተማሪዎች እንደነበሩ ይታወቃል።

አሁንም ድረስ ወደ ትምህርታቸው ያልተመለሱ ተማሪዎች እንዳሉ ተረድተናል። እነዚህ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ሳይመለሱ የዓመቱ ትምህርት ዘመን ሊጠናቀቅ ጥቂት ወራት ቀርቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አሰላ ቲክቫህ ቤተሰቦች፦

ዛሬ በአሰላ ከተማ ለዶክተር አብይ አህመድ እና የልወጥ አመራሩ እንዲሁም ለብልፅግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ ላይ የተገኙ የቲክቫህ ቤተሰቦች የሰልፉን ድባብ በስልካቸው ፎቶ በማንሳት አካፍለዋል።

#Yafu
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
'ኃይለጊዜ' አልበም ለአድማጮች ቀረበ!

'ሞሰብ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን' በኢትዮጵያ የሙዚቃ መሳሪያዎች ብቻ የተሰራ አልበም ለአድማጮ ማቅረቡን የሙዚቃ ቡድኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

አልበሙ በተለያዩ ሙዚቃ ቤቶች፣ የመፅሃፍት መደብሮች እና ከአዟሪዎች እጅ ላይ ማግኘት እንደሚቻል ተገልጾልናል። በተጨማሪ በሞሶብ የዩትዩብ ገፅም አልበሙ እንደሚገኝ ተነግሮናል https://www.youtube.com/channel/UCOERexu9unOQE_ZPx2e8GDw

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE በቢሾፍቱ በሚገኘው የኢፌዴሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በዛሬው ዕለት 106 ለሚሆኑ ከፍተኛ መኮንኖች ሹመት እንደሚሰጥ ታውቋል። በተጨማሪም በዛሬው ዕለት ላለፉት 6 ወራት በስልጠና ላይ የቆዩ የአየር ኃይል ወታደራዊ ፖሊስ አባላት ምረቃ እንደሚኖር ተገልጿል። የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ይልማ መርዳሳ ሹመቱን እንደሚሰጡ ተጠቁሟል። የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር…
#UPDATE

የኢፌዴሪ አየር ኃይል ለከፍተኛ መኮንኖች የማዕረግ እድገት ሰጥቷል። አየር ኃይሉ በዛሬው እለት በቢሾፍቱ በሚገኘው የኢፌዴሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ባካሄደው ስነ ስርዓት ላይ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ምክትል ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ እና የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በስነ ስርዓቱ ላይ 106 ለሚሆኑ መኮንኖች በአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ የተለያዩ የማዕረግ እድገቶችን ሰጥተዋል። ከዚህ ባለፈም ላለፉት 6 ወራት በስልጠና ላይ የቆዩ የአየር ኃይል ወታደራዊ ፖሊስ አባላትም በዛሬው እለት ተመርቀዋል። በተጨማሪም ባለፉት ስድስት ወራት በተቋሙ ከፍተኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ሰራተኞችም የእውቅና እና ሽልማት አሰጣጥ ስነ ስርአት ተካሄዷል።

#FBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ዛሬ ክሳቸው ከተቋረጠላቸው 63 ግለሰቦች መካከል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊው ክርስቲያን ታደለ፤ ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ እና ኤርሚያስ ጠቅል አመልጋ ይገኙበታል፡፡ [አሐዱ ቴሌቪዥን] @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኤርሚያስ አመልጋ ከእስር አልተፈቱም!

[ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8]

መንግስት ክሳቸው አንዲቋረጥ ካደረገላቸው 63 ተከሳሾች ውስጥ እስካሁን ያልተፈታው ኤርሚያስ አመልጋ ብቻ መሆኑ ተገለጸ።

ክሳቸው ከተቋረጠላቸው ሰዎች ውስጥ እስካሁን 62ቱ ከእስር መለቀቃቸውን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 አስታውቋል። ኤርሚያስ አመልጋ ምህረት ከተደረገላቸው ሰዎች መካከል አንዱ ቢሆኑም እስካሁን ከእስር አልተፈቱም።

ያልተፈቱበት ምክንያት ደግሞ የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ለቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ኤርሚያስ አመልጋ ከአስር እንዲፈቱ ደብዳቤ ባለመጻፉ ምክንያት መሆኑን በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ገረመው አያሌው ተናግረዋል።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱኑ በበኩላቸው የአቶ ኤርሚያስ አመልጋ ጉዳይ በመንግስት በኩል ለውጥ የለም፣ ይፈታሉ ብሏል ደብዳቤውም ለማረሚያ ቤቱ ይላካል እስካሁንም የዘገየው የሚጣሩ ጉዳዮች ስላሉ ብቻ ነው እንጂ መፈታታቸው አይቀርም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

#ኢትዮኤፍኤም #ሳሙኤልአባተ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ሳዑዲ ዓረቢያ ወደ መካ የሚደረጉ ጉዞዎች ላይ እገዳ መጣሏን አስታውቃለች። የጉዞ እገዳው ሐይማኖታዊ እና መደበኛ ተጓዦችን የሚያካትት ሲሆን፥ የስርጭት አድማሱን እያሰፋ ካለው የኮሮና ቫይረስ ጋር የተያያዘ መሆኑንም ተሰምቷል።

ይህን ተከትሎም ወደ ሳዑዲ ለሐይማኖታዊ የፀሎት ስነ ስርአትም ይሁን ለጉብኝት የሚደረጉ ጉዞዎች መታገዳቸውን ገልጻለች። ከዚህ ባለፈም የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ከተገኙባቸው ሃገራት የሚነሱ መንገደኞች ወደ ሳዑዲ እንዳይገቡም እገዳ ተጥሏል።

አመታዊው የሃጅ እና ዑምራ ጉዞ ከአምስት ወራት በኋላ ይካሄዳል፤ በአመታዊው ሃይማኖታዊ ስነ ስርአት ላይ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች ወደ መካ ያቀናሉ። የአሁኑ የጉዞ እገዳ እስከ ሃጅ ዑምራ ጉዞ ስለመቆየት አለመቆየቱ ግን የተባለ ነገር የለም።

#አልጀዚራ #ኤፍቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
'የጋዜጠኞች ወግ' መፅሀፍ የካቲት 21 ይመረቃል!

'የጋዜጠኞች ወግ' መፅሃፍ የፊታችን የካቲት 21 በባህር ዳር አቫንቲ ብሉ ናይል ሪዞርት እንደሚመረቅ የመፅሃፉ ፀሃፊ ጋዜጠኛ ግዛቸው አሻግሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል። ከመፅሃፍ ምርቃው በተጨማሪ ልዩ የኪነ ጥበብ ዝግጅት እንደተዘጋጀም ተገልጾልናል።

በዕለቱ አንጋፋው ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ ከረጅም ጊዜ በሗላ መድረኩን እንደሚቆጣጠር የተነገረን ሲሆን ብርቱካን፣ ሀረገወይን፣ ጌጡ ተመስገና እ መሳይ ወንድሜነህ ደግሞ የመድረኩ ፈርጦች ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የቲክቫህ ኢትዮጵያ ባህር ዳር ከተማ ቤተሰቦችም የካቲት 21 በአቫንቲ ብሉ ናይል ሪዞርት በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ እንድትገኙ በክብር ተጋበዛቸሗል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SolveITAccelerator

5 ሚሊዮን ብር ለሥራ ጀማሪዎች ማጠናከሪያ!

iCog labs,JICA ከኩዱ ቬንቸር በተገኘው የ5,000,000 ብር [አምስት ሚሊዮን ብር] የገንዘብ ድጋፍ ሥራ ላይ ያሉ እና ምርትና አገልግሎታቸውን ማሳደግ ለሚፈልጉ እንዲሁም በቴክኖሎጂ ላይ ለተሰማሩ ሰባት ድርጅቶች የአቅም ማበልጸግ ፣ የገበያ ትስስር መፍጠር እና በትንሹ 250,000 ብር ከፍ ካለ እንደ ፕሮጀክቱ ታይቶ የሚጨመር ድጋፍ ለመስጠት ጀምሯል።

የፕሮጀክቱ ማናጀር የሆኑት አቶ ህሩይ ፀጋዬ እንደገለጹት ሥራ ጀማሪዎቹ ከፕሮግራሙ ጋር በሚኖራቸው ቆይታ ማርኬቲንግ እና ቢዝነስ ፕላናቸውን ይበልጥ እንዲያሻሽሉ የሚደረግ ይሆናል።

ከ7ቱ ፕሮጀክቶች መካከል 5ቱን በመውሰድ 10 ቀን የሚቆይ የውጭ ሀገር ልምድ ልውውጥ እና የሚያስፈልጋቸው የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ገበያው እንዲገቡ ይደረጋል ብለዋል፡፡

"ይህንን መሰሉን ሥራ ስንሰራ በዋናነት ማወቅ የምንፈልገው የቴክኖሎጂው ዘርፍ በኢትዮጵያ ምን አይነት ደረጃ ላይ ደርሷል የሚለውን ነው" ያሉት አቶ ህሩይ "የወጣቱን አቅም ማጎልበትና ትርፋማ ማድረግም ሌላው ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ነው" ብለዋል፡፡

በዚህ ስራ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ፣ የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲና ጥቃቅ እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ በአጋርነት ይሰራሉ ተብሏል፡፡

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በSolve IT Accelerator ለሚሳተፉ ቤተሰቦቹ ምን ምን ሟሟላት እንዳለባቸው አዘጋጆቹን ጠይቆ ተከታዩን መልስ አግኝቷል፡፡

በመጀመሪያ የራሳቸውን ሥራ የጀመሩ ፣ ሥራ ለመስራት ዝግጅት ጨርሰው በሙከራ ደረጃ የሚገኙ ለምንሰራው ሥራ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ፣ የልምድ እና የገበያ ትስስር የሚፈልጉ መመዝገብ ይችላሉ የተባለ ሲሆን ከሰባቱ ውስጥ ለመካተት ደግሞ የሚከተሉት መስፈርቶች ይታያሉ፡-

- በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ

- ምርታቸው በገቢያ ውስጥ ገብቶ ውጤታማ መሆኑ ከታመነበት

- የተጠቀሙት ቴክኖሎጂ፣ ያላቸው የማደግ ፍላጎት፣ ህጋዊ ጉዳዮች፣ ለውጥ ማምጣት የሚፈልጉበት ዘርፍ ታይቶ ከሰባቱ ውስጥ ይካተታሉ፡፡

እስካሁን ከሃያ በላይ ሥራ ጀማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን አሁንም በዚህ እድል መጠቀም ለሚፈልጉ ምዝገባው ለተከታታይ 20 ቀናት ክፍት መሆኑን ተገልጿል፡፡

Apply Online https://www.icog-sa.com

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመጪው ምርጫ ፓርቲዎችን ብቁ የማድረጉ ሥራ ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ ለመመዝገብ እና ለምርጫ ለመወዳደር የሚፈልግ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ወይም የግለሰቦች ስብስብ እንዲሁም ግንባር/ቅንጅት መፍጠር የሚፈልጉ ፓርቲዎች፣ አስፈላጊ ሰነዶቻቸውን እስከ የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለቦርዱ እንዲያስገቡ ጥሪ አቅርቧል።

ቦርዱ ባስተላለፈው ጥሪ መሠረት ከተቀመጠው ጊዜ ገደብ በኋላ የሚመጡ የምዝገባ ማመልከቻዎች በተለመደው አግባብ የሚስተናገዱ ቢሆንም፣ ያለው የአሠራር ሂደት ከሚወስደው ጊዜ አንጻር መጪው ብሔራዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ የማይችሉ መሆኑን ገልጿል።

ምንጭ:-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#GAMBELA

በጋምቤላ ክልል በኑዌር ብሄረሰብ ዞን በቀበሌ ሊቀመንበር መገደል ምክንያት የተቀሰቀሰ ግጭት ለ12 ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑ ተነገረ።

ቀስ በቀስ ወደ ጎሳ ግጭት የቀየረው በዚህ ሁከት 21 ሰዎች ሲቆስሉ፣ 400 ቤቶች ተቃጥለዋል፤ ከ300 በላይ የቤት እንስሳቶችም ተዘርፈዋል። በተጨማሪ የግጭቱ ሰለባ የሆኑ የ5 ቀበሌ ነዋሪዎች [7 ሺህ ሰዎች] ተፈናቅለዋል።

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትግራይ ክልል መንግስት 2 ሺህ 332 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ወሰነ!

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት 2 ሺህ 332 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን የክልሉ ጸጥታና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።

ታራሚዎች ይቅርታ የተደረገላቸውም የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) 45ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ነው ተብሏል።

#ኤፍቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia