ከቲክቫህ ቤተሰቦች፦
ቆሬ አከባቢ የሚገኘ የቲክቫህ ቤተሰቦች ዛሬ ከሰዓት አንድ የጭነት መኪና መንገድ ስቶ ገብቶ ከታች በነበሩ መኖሪያ ቤቶች ላይ በመውደቅ አሳዛኝ አደጋ መድረሱን ገልፀዋል። በአደጋው የ4 ሰው ህይወት ሳያልፍ እንዳልቀረ ገልፀዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#UPDATE
በሺህዎች የሚቆጠሩ የሀላባ ዞን ነዋሪዎች በሀላባ ቁሊቶ ስቴዲየም ተሰብስበው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን መቀበላቸው ተገልጿል። የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጉብኝት በማስመልከት እና መደመርን በማክበር ማኅበረሰቡ 120 በሬዎችን እና 3 ግመሎችን አሰልፈው አምጥተው በስጦታነት ማበርከታቸውም ተነግሯል።
ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት

የሆስኒ ሙባረክ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ!
የቀድሞ የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ስርዓተ ቀብር በወታደራዊ ስነስርአት በክብር ተፈፀመ፡፡
የቀብር ስነ-ስርዓቱ በካይሮ ከተማ በፊልድ ማርሻል ታንታዊ መስጂድ ሲፈፀም በስፍራው የወቅቱ ግብጽ ፕሬዝዳንት አብዲል ፈታ አልሲሲ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የሟች ቤተሰቦች እና ደጋፊዎቻቸው ተገኝተዋል፡፡
የፕሬዚዳንቱ አስከሬን የቤተሰባቸው የመቃብር ቦታ ላይ እንደሚያርፍ የተገለፀ ሲሆን የግብጽ መንግስትም የሶስት ቀን ብሔራዊ የሀዘን ቀን አውጇል፡፡
[#ቢቢሲ #ሮይተርስ #ኢቢሲ]

#GONDAR
በጎንደር ከተማ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸውን መድሃኒቶች በአንድ ትምህርት ቤት ሲያሰራጩ የተገኙ 15 ግለሰቦችን መያዙን ፖሊስ አስታውቋል።
የከተማው 3ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ደሳለኝ አበራ እንደተናገሩት ትናንት ከቀኑ 8 ሰአት መድሃኒቶቹን ሲያዘዋውሩ ከተያዙት ግለሰቦች መካከል 13ቱ የውጭ ሃገር ዜግነት ያላቸው ሲሆኑ ሁለቱ ኢትዮጵያዊያን ናቸው።
#ኢዜአ

"ተጠርጣሪዎቹ ምንም ዓይነት የህክምና ፍቃድ የላቸውም" - ፖሊስ
በጎንደር ከተማ ጌዜ ያለፈባቸው መድሃኒቶችን ሲያሰራጩ የተያዙት ተጠርጣሪዎች ምንም ዓይነት የህክምና ፈቃድ እንደሌላቸው ተገልጿል።
ተጠርጣሪዎቹ ማራኪ ክፍለ ከተማ ልኡል አለማየሁ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚገኙ ተማሪዎች የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸውን መድሃኒቶች ሲያሰራጩ ነው የተያዙት።
ፖሊስ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ባደረገው ክትትል ግለሰቦቹ በትምህርት ቤቶቹ ለሚገኙ 20 ተማሪዎች ያሰራጯቸውን ከሁለት እስከ 10 አመት የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸውን መድሃኒቶችም መያዝ ተችሏል።
በአንድ የጥርስ መንቀያ መሳሪያና በአንድ መርፌ በርካታ ህጻናት ተማሪዎችን ጥርስ ሲነቅሉና ሲያክሙ መያዛቸውም ተገልጿል።
በተለያዩ ግለሰብና ድርጅቶች ስም ይንቀሳቀሱ እንደነበሩ የተገመቱት የውጭ ሃገር ዜጎቹ እስከ አሁን ያዘዋወሩት መድሃኒት መጠ እና ያደረሱት ጥፋት እየተጣራ ነው።
[የጎንደር ከተማ 3ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ፣ ኢዜአ]

ሌ/ኮሎኔል ቢንያም ተወልደ ከእስር ተፈተዋል...
የቀድሞ የኢንፎርሜሽንና መረብ ደኀንነት ኤጀንሲ(ኢንሳ) ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ሌተና ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር እንዲፈቱ ከተወሰኑት 63 ሰዎች መካከል የነበሩ ሲሆን በመዝገብ ቁጥር ስህተት አለመፈታታቸው የተነገረ ቢሆንም ዛሬ የካቲት 18/2012 ከሰዓት በኋላ መፈታታቸውን ጠበቃቸው ኃይለ ሥላሴ ገብረ መድሕን ለአዲሰ ማለዳ ጋዜጣ ገልፀዋል።
ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ

የብሮድካስት ባለስልጣን ማስጠንቀቂያ...
የብሮድካስት ባለሥልጣን በኢኦተ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ለኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ማስጠንቂያ ሰጠ። ባለስልጣኑ ጣቢያው በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅና፣ በተመጣጣኝ ስፋት እና በተመሣሣይ የሥርጭት ሰዓት የቤተክርስቲያኗን ቅሬታ እንዲያስተላልፍም አዟል።
ባለስልጣኑ ውሳኔውን ያስተለፈው፣ ኃሚካኤል ታደሰ የተባሉ ግለሰብ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ በፍቸና በገብረ ጉራቻ ከተሞች ባዘጋጃቸው መድረኮች የተናገሩትን ንግግር ጣቢያው ማስተላለፉን ተከትሎ ነው።
ደብዳቤውን ከላይ ተመልከቱ!
#EotcTV #ELU

በትግራይ በሚገኙ 36 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለተጀመረው የተማሪዎች የምግባ ፕሮግራም ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መመደቡን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ።
በቢሮው የምገባ ፕሮግራሙ አስተባበሪ አቶ አፅብሃ ሃይለዝጊ እንዳሉት ፕሮግራሙ የተጀመረው የምግብ ዋስትና ችግር አለባቸው ተብለው በተለዩ የሀውዜን፤ ክልተኣብላዕሎ እና አፅቢወንበርታ ወረዳዎች ውስጥ ነው።
በወረዳዎቹ ውስጥ ከሁለተኛ የትምህርት መንፈቅ ዓመት ጀምሮ መካሄድ ለጀመረው የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም ከ40 ሚሊዮን ብር በጀት መመደቡን አስታውቀዋል።
#ENA

አቶ ዮሃንስ ቧያለው ሹመቱን አልቀበልም ብለዋል!
አቶ ዮሃንስ ቧያለው የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ፕሬዘዳንትነት ሹመትን እንደማይቀበሉት አስታወቁ።
የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት በትናንትነው ዕለት አቶ ዮሃንስ ቧያለውን የመለስ ስራ አመራር አካዳሚ ፕሬዘዳንት እንዲሆኑ መሾሙ ይታወሳል።
ይሁንና አቶ ዮሃንስ ከአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ ሹመቱን እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል።
#ኢትዮኤፍኤም #አብመድ

#KFO
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ «ኦፌኮ» ወደ 70 የሚሆኑ አባሎቼ በኦሮምያ ክልል ታስረዉብኛል ሲል ገለፀ። ፓርቲዉ ይፋ እንዳደረገዉ ጽ/ፈት ቤት መዝጋትና ስብሰባና እንዳናካሂድ ማድረግ በተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋዉረን እንዳንሰራ መከልከል የመሳሰሉ ችግሮች ፓርቲዉ እየተጋፈጠዉ ያለዉ ኩነት ነዉ ብሎአል።
#DW
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

#AccessNow
ባለፈው የፈረንጆች ዐመት ኢትዮጵያ እና አልጀሪያ ኢንተርኔትን በመዝጋት ከአፍሪካ ቀዳሚ እንደሆኑ ብሉምበርግ Access Now የተሰኘውን ድርጅት ጠቅሶ ዘግቧል። ኢትዮጽያ 4 ጊዜ፣ አልጀሪያ 6 ጊዜ ዘግተዋል።
#wazemaradio

#NEBE
የኢትየጵያ ምርጫ ቦርድ በአሁን ወቅት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) እየተገለገለባቸው የሚገኙትን ሦስት ጽኀፈት ቤቶች እንዲመልስ ለፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስለመጠየቁ የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ገልጿል።
ምርጫ ቦርድ የሦስቱ ጽኀፈት ቤቶች ባለቤትነት የኢዴፓ መሆኑን ጠቀሶ፣ ለፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በየካቲት 17/2012 በጻፈው ደብዳቤ ላይ ከኢዜማ በማስመለስ ለፓርቲያችን እንዲያስረክብ ተጠይቋል ሲሉ የኢዴፓ ፕሬዝዳንት አዳነ ታደሰ ገልጸዋል።
አዳነ፣ ምርጫ ቦርድ አስቀድሞ ይህን ነገር መፍታት ሲኖርበት ዘግይቶም ቢሆን ተገቢ እርምጃ መውሰዱን በመልግለፅ ቀጣዩ ስራችን የቤቶች ኮርፖሬሽን አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወስድ መጠየቅ ነው ብለዋል። ኢዴፓ በኢዜማ ላይ መስርቶት የነበረውን ክስ ጽኅፈት ቤቶቹ መመለሳቸውን እርግጠኛ ሲሆን ክሱን ሊያቋርጠው እንደሚችል ጠቁሟል።

አሳዛኙ የአዲስ አበባ ቆሬ አካባቢ አደጋ፦
[ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1]
- አደጋው የደረሰው 5:30 አካባቢ ከብስራተ ገብርኤል ወደ ጀሞ ሲሄድ የነበረና አጠና የጫነ IVECO ግልባጭ መኪና ቆሬ ዓለም ሰላም ድልድይ ውስጥ ባሉ ቤቶች ላይ ወድቆ ነው።
- በአደጋው የሶስት ሰዎች ህይወታቸው አልፏፋ። በአንድ ሰው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል። ከሟቾች ውስጥ የ11 ወር ህፃንና ንፍሰጡር ሴትም ይገኛሉ። ነፍሰጡር ሴቷ የ25 ዓመት ወጣት እና የህፃኑ አክስት እንደሆነች ተገልጿል።
- የ28 ዓመት ወጣት የሆነው አሽከርካሪም በአደጋው ህይወቱ አልፏል።
- የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።
#ShegerFM #EliasMeseret

አቶ ዮሃንስ ቧያለው ለምን ሹመቱን አልተቀበሉትም?
አቶ ዮሃንስ ቧያለው ለአማራ ቴሌቪዥን በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት የተሰጣቸውን ሹመት የማይቀበሉበትን ምክንያት እንዲህ አስረድተዋል፦
"በአሁኑ ጊዜ እራሴን ሳዳምጠውና ስመረምረው በዛ ተቋም መስራት ቢኖርብኝ እንኳን አሁን ባለው ብራንድ መስራት ምችልበት ሁኔታ ስላልሆነ የቀረበውን ሹመት ለመቀበል ያስቸግረኛል። ስለሆነም የኢትዮጵያን ህዝብ ትግል ፣ የአማራን ህዝብ ትግል በተለያየ መልኩ አስተዋፅኦ በማድረግ የፓርቲያችን ጉዞም እንዲጠናከር በማድረግ በተለየ ቦታ ብመደብ፣ ወይም ይሄ የተለየ ብራንድ ቢሰጠው ላገለግል እችላለሁ እንጂ አሁን ባለው ስያሜና ብራንድ በዛ ተቋም ለማገልገል ዝግጁ አለመሆኔን ገልጫለሁ በተለይም ለቦርዱ ሰብሳቢ። ትላንት ከሰማሁኝ በኃላ ዛሬ ጥዋት ምደባውን እንደማልቀበል ሪፖርት አድርጊያለሁ።"

#YohannesBuayalew
አቶ ዮሃንስ ቧያለው አማራ ክልል በስልጣን በቆዩባቸው ዓመታት ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ድጋፍ እንደነበራቸው ዛሬ ከአማራ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።
አሁንም ቢሆን ለአማራ ክልልም ሆነ ለመላ ኢትዮጵያውያን ሰላም፣ ነፃነትና ብልፅግና እንደሚሰሩ አብራርተዋል፡፡
አዲስ የተሸሙ የአማራ ክልል አመራሮች እውቀትና ልምድ ያላቸው ታታሪ አመራሮች በመሆናቸው ህዝቡ ድጋፉን እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
አቶ ዮሃንስ ቧያለው አማራ ክልል በስልጣን በቆዩባቸው ዓመታት ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ድጋፍ እንደነበራቸው ዛሬ ከአማራ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።
አሁንም ቢሆን ለአማራ ክልልም ሆነ ለመላ ኢትዮጵያውያን ሰላም፣ ነፃነትና ብልፅግና እንደሚሰሩ አብራርተዋል፡፡
አዲስ የተሸሙ የአማራ ክልል አመራሮች እውቀትና ልምድ ያላቸው ታታሪ አመራሮች በመሆናቸው ህዝቡ ድጋፉን እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#PHOTO : ዛሬ ከእስር የተፈቱት የቀድሞ የኢንፎርሜሽንና መረብ ደኀንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ሌተናል ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአቶ ንዋይ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፅሟል...
ለረዥም ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው ያገለገሉት አቶ ንዋይ ገብረአብ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፅሟል። የቀብር ሰነ ስርዓታቸው ቤተሰቦቻቸው ፣ የቀድሞ የስራ ባልደረቦቻቸው ፣ አድናቂዎቻቸው በተገኙበት ነው በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የተፈፀመው።
ከ1970ዎቹ ጀምሮ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና በፕላን ኮሚሽን ውስጥም ለረዥም ዓመታት አገልግለዋል። አቶ ንዋይ ከኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪነታቸው ባለፈ የኢትዮጵያ የልማት ጥናት ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል።
#FBC