TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#BreakingNews »» Loading
#BreakingNews »» Loading
#BreakingNews »» Loading
አቶ በረከት ስምኦን #BreakingNews »» Loading
አቶ ለማ መገርሳ #BreakingNews »» Loading
#BreakingNews »» Loading
#BreakingNews

የአይኤስ-አይኤስ መሪው አቡባክር አል-ባግዳዲ ሶሪያ ውስጥ በተደረገ ኦፕሬሽን ሳይገደል እንዳልቀረ ተሰምቷል። አሜሪካ በትላንትናው ዕለት ሶሪያ ውስጥ የISIS መሪውን ኢላማ ያደረገ ጥቃት ሰንዝራ ነበር።

#CNN

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BreakingNews

የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳድ ሀሪሪ ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ገለፁ። በዋትስ አፕ ላይ የተጣለ ታክስን በመቃወም ተጀምሮ በሀገሪቱ አለ የተባለውን የፖለቲካ ሙስና እና የኢኮኖሚ ቀውስን ወደ መቃወም በተቀየረ አመፅ ሀገሪቱ ስትናጥ ቆይታለች። አመፁ ከተቀሰቀሰ ጀምሮም ሊባኖስ ለ13 ቀናት ሙሉ በሙሉ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዋ ተዘግቶ፣ ባንኮች እና ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ሌሎች እንቅስቃሴዎች ተቋርጠውባት ሰንብታለች።

https://telegra.ph/LBN-10-29

ምንጭ፦ አልጀዚራ( ኤፍ ቢ ሲ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BreakingNews

የፀጥታ አካላት ሀላፊነት መውሰድ ካልቻሉ የ2012 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እና የእግር ኳስ ውድድሮች ላይካሄዱ ይችላሉ ተብሏል፡፡ ውድድሮቹ ሚካሄዱ ከሆነ ግን በዝግ እንዲደረጉ እንቅስቃሴ መጀመሩን የስፖርት ጋዜጠኛው ቴዎድሮስ ታከለ(ቴዲ ሶከር) አገኘሁት ባለው መረጃ ጠቁሟል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BreakingNews

በነገው ዕለት በሚካሄደው የኢህአዴግ ምክርቤት ስብሰባ ላይ ህወሓት እንዳይማይሳተፍ ውሳኔ አሳለፈ!

የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባላት ነገ በሚጀመረው የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንደማይሳተፉ የህወሓት ፅሕፈት ቤት ገለፀ፡፡ ህወሓት በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ በኩል ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው የኢህአዴግ ውህደት በግንባሩ ሥራ አስፈፃሚ ደረጃ ይሁን ምክር ቤት ስብሰባ ሊወሰን የማይችል መሆኑ ጠቅሶ አባላቱ ነገ በሚጀምረው የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንደማይሳተፉ ዐስታውቋል፡፡

አራቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች እያንዳንዳቸው 45 ተወካዮች የሚያሳትፉበት የኢህአዴግ ምክር ቤት ከነገ ጀምሮ ስብሰባ እንደሚያካሂድ ግንባሩ በዛሬው ዕለት ገልፅዋል፡፡ «የህወሓት እጣ ፈንታ ሊወሰን የሚችለው በየደጃው ውይይት ከተደረገበት በኋላ በህወሓት ጉባኤ ብቻ በመሆኑ በአሁኑ ሰአትስብሰባ ላይ ለመሳተፍ የማንችል መኾኑን እናሳውቃለን» ይላል የህወሓት መግለጫ።

ከኢሕአዴግ ምክር ቤት 180 አባላት መካከል 45ቱ የህውሓት አባላት ናቸው፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በግንባሩ ውህደት ዙርያ የቀረበው የጥናት ውጤት በአብላጫ ድምፅ ማፅደቁ ይታወሳል፡፡ ጉዳዩ በግንባሩ ምክር ቤት ደረጃ እንደሚታይም ተገልፆ ነበር፡፡

(DW)

PHOTO-TPLF

@tsegabwolde @tikvahethiopia