TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#COVID19

በኢራን በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የተጠቁ ዜጎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ ቱርክ፣  አፍጋኒስታን እና ፓኪስታን ከሀገሪቱ የሚያዋስናቸውን ደንበር መዝጋታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

#ኤፍቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በኮሮና ቫይረስ ስጋት ያየለ ይመስላል...

ከ13 በላይ የሚሆኑ ሀገራት በኮሮናቫይረስ ስጋት የተነሳ ከደቡብ ኮሪያ የሚመጡ ሰዎች እንዳይገቡ ገደብ መጣላቸው ተገልጿል፡፡

እንደ ሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ገለፃ ከሆነ እስራኤልን ጨምሮ ፤ ባህሬን ፤ አሜሪካና እንግሊዝ ይህን እርምጃዎች ከወሰዱ ሀገራት መካከል ይገኙበታል ተብሏል፡፡

እስራኤል እንዳስታወቀችው ከደቡብ ኮሪያና ከጃፓን ለጉብኝት የሚመጡ ዜጎች ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ ከሰኞ ጀምሮ የጉዞ እቀባ ተግባራዊ ማድረጓን የአገሪቱ ዜና አውታሮች ዘግበዋል፡፡

ባህሬንም ከአርብ ጀምሮ ተመሳሳይ እርምጃ መውሰዷ ታውቋል፡፡ የእስራኤል ውሳኔ የተላለፈው ባለፈው ቅዳሜ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ወደ ደቡብ ኮሪያና ጃፓን የሚያደርጉትን በረራዎች እንደሚያግዱ ከተገለፀ በኋላ ነው፡፡

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የገቢዎች ሚኒስቴር በኤክሳይስ ታክስ አዋጅ አፈፃም ዙሪያ ከአስፈፃሚ አካላት ጋር ተወያየ!

የገቢዎች ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ከፌዴራል፣ ከክልል እና ከከተማ አስተዳደር የገቢው ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሂዷዳ። የውይይቱ ዋና አላማ አዋጁን የሚያስፈጽሙ አካላት ጋር የጋራ መግባባት ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች ከአፈፃፀም ጋር በተያያዘ ግልጸነት የሚያስፈልጉ ጉዳዮችን በማንሳት ከመድረክ ላይ ሰፊ ማብራራያ ተሰጠዋል፡፡

አዋጁን ለማስፈጸም የገቢዎች ሚኒስቴር በሚያደርጋቸው ዝግጅቶች፣ ኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ምርቶች ለማምረት የፈቃድ አሰጣጥ ሂደት፣ ከማምረቻዎች ጋር ተያይዞ የታክስ ግዴታ የሚጀምርበት ጊዜ፣ ቀድሞ ስለተከፈ ታክስ ተመላሽ የሚደረግበት ስርዓት በተመለከተ በገንዘብ ሚኒስቴር የታክስ አማካሪ አቶ ዋሲሁን አባተ የውይይት መነሻ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

እንዲሁም የአክሳይስ ታክስ የተጣለበት ያልተጣለበት ዕቃዎች፣ የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ ለማስፈጸም በገቢዎች ሚኒስቴር ስር አዲስ አደረጃጀት እንደሚያፈልግ እንዲሁም በአዋጁ ውስጥ የተካተቱት ውሳኔዎች ለወደ ፊት መሻሻል ሲያስፈልግ በምን መልኩ መሆን እንዳለበት ከአስፈፃሚ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡

ምንጭ፦ የገቢዎች ሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ቻይና የዱር እንስሳት ንግድን ልታግድ ነው!

የቻይና ከፍተኛው የህግ አውጪ ኮሚቴ እንዳስታወቀው የዱር እንስሳት መነገድም ሆነ መመገብ ለአዲሱ የኮሮና ቫይረስ በሽታ መነሻ ናቸው በሚል ድርጊቱን ለመቆጣጠር ረቂቅ አዋጅ አዘጋጀ፡፡

ለብሄራዊ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ (NPC). የተመራው ረቂቅ ህግ የትኛውንም የዱር እንስሳት መመገብም ሆነ መነገድን የሚከለክል ሲሆን ይህም የህብረተሰቡን ጤና ከመጠበቅ አልፎ ብዝሀ-ህይወትን ለመታደግ ያስችላል ነው የተባለው፡፡

ቋሚ ኮሚቴው 3ሺ የብሄራዊ የህዝብ ምክር ቤት አባላትን ሲወክል ኮሚቴው በመጪው ወር በሚያደርገው ስብሰባ አዋጁን እንደሚያጸድቀው ቢጠበቅም በሀገሪቱ የተከሰተው የጤና ቀውስ እንደሚያዘገየው ከወዲሁ ተገምቷል፡፡

የቻይና የጤና ባለሞያዎች የኮሮና ቫይረስ በውሀን ግዛት የመከሰቱ መነሻ የዱር እንስሳት ገበያ እንደሆነ ግምታቸውን አስቀመጠዋል፡፡

የቻይና ወግ አጥባቂዎች ጤንነታቸው ያልተረጋገጠ የዱር እንስሳት ሲሸጡ ቻይና ዝም በማለቷ ለተከሰተው የጤናና ኢኮኖሚዊ ቀውስ ሀላፊነቷን አልተወጣችም በማለትም ሲወቅሷት ሰንብተዋል፡፡

#AFP #ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አቶ ንዋይ ገብረዓብ ማረፋቸው ተሰማ!

የቀድሞዎቹ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትሮች መለስ ዜናዊ እና ሃይለማርያም ደሳለኝ የኢኮኖሚ አማካሪ የነበሩት አቶ ንዋይ ገብረዓብ አረፉ።

የትግራይ ክልል የመንግስት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው የቀድሞዎቹን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትሮች የኢኮኖሚ አማካሪ የነበሩት አቶ ንዋይ ገብረዓብ ዛሬ ረፋድ ባደረባቸው ህመም ምክንያት አርፈዋል።

አቶ ንዋይ ኢትዮጵያ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጋር ጥሩ ግንኙነት አንዲኖራት፣ኢትዮጵያ ከአገራት ጋር የምታደርጋቸውን ኢኮኖሚያዊ ስምምነቶችን እና ሌሎች አገራዊ ጉዳዮች ላይ መሪዎቹን ሲያማክሩ ቆይተዋል።

አቶ ንዋይ ከሁለት ዓመት በፊት የአፍሪካ ህብረት የኢኮኖሚ ኮሚሽነር ለመሆን የኢትዮጵያ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው ቢቀርቡም በመጨረሻው ዙር በካሜሩን እጩ መሸነፋቸው አይዘነጋም።

#ኢትዮኤፍኤም107.8 #ሳሙኤልአባተ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሟሟላት የሚገባቸውን ዝርዝር ጉዳዮች እስከ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ/ም እንዲያሟሉ አሳስቧል።

በፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ምርጫ አዋጅ ቁጥር 1162 / 2011 መሰረት በቦርዱ ሀገር አቀፍ እና የክልል ፓርቲዎች ማሟላት ያለባቸውን ግዴታዎች ለማስፈጸም የወጣው መመሪያ ቁጥር 3/2012 መሰረት የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ማሟላት የሚገባቸውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያስረዱ ሰነዶች ማዘጋጀቱ እና ለፓርቲዎች እንዲደርሳቸው ማድረጉ አስታውሷል፡፡

ለእያንዳንዱ ፓርቲም በደብዳቤ ማሟላት የሚገባቸውን ሁኔታዎች ሁሉ እስከ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ/ም ድረስ አሟልተው እንዲያቀርቡ ቦርዱ አስታውቋል። ቦርዱ እስካሁን ሰነዶቻቸውን ያስገቡ ፓርቲዎች ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑን በዛሬው ዕለት ገልጿል።

በመሆኑም ማሟላት የሚጠበቅባቸው ዝርዝር ሁኔታዎችን የሚያስረዱ ሰነዶች የደረሳቸው የፓለቲካ ፓርቲዎች በሙሉ መጋቢት 3 ቀን 2012 ከመድረሱ በፊት ማሟላት የሚገባቸውን በሙሉ አሟልተው የምዝገባ ስርአቱን እንዲጀምሩ አሳስቧል።

ምንጭ፡-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በሶማሌ ብ/ክ/ መንግስት በውጫሊ መግቢያና መውጫ ድንበር ላይ የኮሮና COVID -19 ን ለመከላከል እየተደረገ ያለው ቅድመ ጥንቃቄ ስራ ተጎበኘ።

ከኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር እና ከክልሉ ጤና ቢሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በተገኙበት በሶማሌ ብ/ክ/ መንግስት የውጫሊ መግቢያና መውጫ ድንበር ላይ የኮሮና COVID -19 ን ለመከላከል እየተደረገ ያለው ቅድመ ጥንቃቄ ስራ የተጎበኘ ስሆን እስካሁን ከበሽታው ጋር የተያያዘ ያጋጠመ ምልክት የለም።

በሽታው ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ በአከባቢው ላይ የተጀመረው የልይታ ስራ አበረታች ቢሆንም ጊዜያዊ የመለያ ጣቢያን ከማዘጋጀት ጀምሮ አስፈላጊው የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች ትኩረት አግኝተው ሊሰሩ እንደሚገባ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰሃረላ አብዱላሂ አሳስበዋል።

ምንጭ፦ ጤና ሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያግዙ የህክምና ቁሳቁሶችን ከተለያዩ ሀገራት ወደ ቻይና እያጓጓዘ እንደሚገኝ ገልጿል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የኢትዮጵያ መንግስት ለ60 ጉዳያቸውን በህግ ሲከታተሉ ለነበሩ ተጠርጣሪዎች ምህረት ማድረጉን በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክረተሪ አቶ ንጉሱ፦

"መንግስት በቻይነት እና በሆደ ሰፊነት የተለያዩ ጥያቄዎች በመኖራቸው እና ትምህርት ስለተወሰደበት ለ60 ዜጎች ክሳቸው እንዲቋረጥ ወስኗል።"

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በኦሮሚያ ክልል አባ ቶርቤ የሚባልና 'ጽሑፍ ያለው ወረቀት እየበተነ  አስጠንቅቆ  ሲያበቃ ቀጠሮ ሰጥቶ የሚገድል' የተባለ አካል የክልሉን ሰላም እያወከ መሆኑን የክልሉ የኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

አቶ ጌታቸው ባልቻ ለዶቼ ቬለ የተናገሩት፦

ትናንት በአምቦ ከተማ ለመንግሥት ድጋፍ የወጡ ሰዎችን እንቅስቃሴ ለማስቆም  ያሰበ ግን ያልተሳካ ያሉት የቦንብ ጥቃት ተሰንዝሮ 29 ሰዎች ተጎድተዋል። ከተጎጂዎቹ  አንዱ ብቻ አሁንም በህክምና ላይ እንደሚገኝ ቀሪዎቹ ግን ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል።

በጉዳዩ በአካል ተሳትፈዋል በሚል እጃቸው እንዳለበት የተጠረጠሩ ስድስት ሰዎች እጅ ከፈንጅ የተያዙ ሲሆን ክትትሉ ቀጥሏል። ራሱን በድርጅትም ይሁን በቡድን ደረጃ እንዲህ ነኝ ብሎ የሚጠራ አካል ባይኖርም ግድያ እየፈጸመ ፣ ዜጎችን እያፈናቀለ ፣ ጉዳት እያደረሰ ያለው «አባ ቶርቤ» የሚባል አካል ነው።

ባለፈው ዓርብ የተገደሉትን የቡራዩ ከተማ ፓሊስ አዛዥ በተመለከተም ክትትሉ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ሕዝቡን የማረጋጋት እና አጥፊዎቹን ወደ ሕግ የማቅረብ ሥራ በተጠናከረ  ሁኔታ  እየተከናወነ ነው። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም 18 ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል።

መከላከያ ሠራዊት በተለይም በምዕራብ የክልሉ ክፍል ከክልሉ የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ጸጥታ የማስከበር ሥራ እየሠራ ነው። በሞያሌ ተመሳሳይ ጥቃት በጸጥታ አካላት ላይ ተፈጽሟል ስለሚባለው፤ እስካሁን የጠራ መረጃ የለኝም።

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ምህረት የተደረገላቸው 60 ዜጎች ክሳቸው የተቋረጠበትን የሕግ አግባብ እና የስም ዝርዝራቸውን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ነገ ዝርዝር መረጃን ይሰጣል።

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TPLF

የህወሓት ስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ድርጅታቸው በርካታ ስራዎችን በመስራት ጊዜውን እያሳለፈ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

አቶ ጌታቸው ረዳ 'እንኳን ሌላ ጉዳይ ውስጥ ገብተን ልንፈተፍት ቀርቶ ሙሉ ትኩረት ሰጥተነውም ቢሆን ሙሉ በሙሉ አልፈታነውም እንጂ የወጣቶችንን ችግር ለመፍታት እየተንቀሳቀስን ነው ያለነው' ሲሉ ገልፀዋል።

አክለውም ህወሓት ለበርካታ አስርት አመታት የሕዝብን አቅም ተጠቅሞ ለውጥ እያስመዘገበ የመጣ ድርጅት ነው፤ ለሰላም፣ ለዲሞክራሲ፣ ለልማት አርአያ መሆን የሚችል ተግባር ያከናወነ ድርጅት ነው ሲሉም ተደምጠዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የአክሲዮን ገበያዎች በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ስጋት ውስጥ ወድቀዋል ተባለ። የእንግሊዙ ሳምንታዊ የዋጋ መመዘኛ ባወጣው መረጃ መሰረት የአክሲዮን ዋጋ በ3 በመቶ ቀንሷል፣በአብነትም በጣሊያኗ ሚለን የአክሲዮን ገበያ 4.5 በመቶ ቀንሷል፡፡

የአክሲዮን ማህበራት የዋጋ ድቀት ከደረሰባቸው አየር መንገዶች ከፍተኛውን ድርሻ ሲይዙ በተቃራኒው የወርቅ ገበያ ባለፉት ሰባት ዓመታት ከነበረው የ2 በመቶ እድገት አሁን የባለ 28 ካራት ወርቅ ዋጋ 1,680 ዶላር ደርሷል፡፡

አየር መንገዶች የገቢ ቅናሽ ካሳዩት የኢንግሊዙ ኢሲጄት ከነበረው የበረራ ገቢ 14 በመቶ ሲያሽቆለቁል የቱይ እና ብሪቲሽ አየር መንገዶች 8.5 በመቶ ቅናሽ አሳይተዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስ [#COVID19] ፈጣን ስርጭት ያስከተለውን ኢኮኖሚያዊ ቀውስ በመፍራት አብዛኞቹ ባለሀብቶች ስጋት ውስጥ መግባታቸውን በቢሲ ዘግቧል፡፡

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በኢጣልያ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 5 ደረሰ። በቫይረሱ 5 ሰዎች መሞታቸውን ዛሬ የተናገሩት የኢጣልያ ባለሥልጣናት ተህዋሲው የተገኘባቸው ቁጥር ደግሞ ከ200 በላይ መሆኑን አስታውቀዋል።

ከመካከላቸው 3ቱ ሮም መሆናቸው ተገልጿል። የሟቾቹ እድሜ ከ68 ዓመት በላይ ነው ተብሏል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በተህዋሲው የተያዙ የተገኙት በሰሜን ምዕራብ ኢጣልያዋ ክፍለ ግዛት ሎምባርዲ እና ቬኒስ አቅራቢያ በምትገኘው በቬኔቶ ክፍለ ግዛት ነበር።

አሁን ግን የሁለቱ ግዛቶች አጎራባች በሆኑት በሰሜናዊው ክፍለ ግዛት በኢሚልያ ሮማኛ እና ፒድሞንት በተባለችው በሰሜን ምዕራብዋ ግዛትም ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ተገኝተዋል።

የኢጣልያ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት እስከ ዛሬ እኩለ ቀን ድረስ በሎምባርዲ ግዛት 167፣ በቬኔቶ 27 በኢሚልያ ሮማኛ 18 እንዲሁም በፒድሞንት 4 ኮሮና ቫይረስ ያለባቸው ሰዎች ተገኝተዋል።

በዚሁ መሠረት ኢጣልያ በኮሮና ቫይረስ በተያዙ ሰዎች ብዛት ከቻይናና እና ከደቡብ ኮሪያ ቀጥሎ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። የኢጣልያ መንግሥት ባለፈው ቅዳሜ ሎምባርዲ የሚገኙ 10 ከተሞችን ለመዝጋት ወስኗል።

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሜቴክና አብን አመራሮች ከእስር ከሚለቀቁት ውስጥ ናቸው! ነገ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአንባቢያን የምትቀርበው "ሲራራ" ጋዜጣ በፊት ለፊት ገጿ ላይ ተከታዩን መረጃ ይዛለች፦ ከሰሞኑን ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ ከለውጡ በኃላ በተለያዩ አካባቢዎች በወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩትን የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ሲባል ጉዳያቸው በአግባቡ በህግ ታይቶ እንዲለቀቁ አቅጣጫ መቀመጡን መግለፃቸው አይዘነጋም። ጠቅላይ…
#UPDATE

የኮሎኔል ቢንያም ተወልደ ክስ ይቋረጣል!

የኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ ጠበቃ የሆኑት አቶ ኃይለሥላሴ ገብረመድህን ዛሬ አመሻሽ ላይ ለቢቢሲ የዜና አውታር በሰጡት መረጃ ፤ ኮሌኔል ቢኒያም ተወልደን ጨምሮ የሜቴክ ተከሳሾችም ክሳቸው ይቋረጣል የሚል መረጃ እንደደረሳቸው ጠቁመዋል።

ከትላንት በስቲያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአንባቢያን የቀረበችው 'ሲራራ ጋዜጣ' ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር ከሚፈቱት ዜጎች መካከል የሜቴክ እና የአብን አመራሮች እንደሚገኙበት ገልፃ ነበር። መረጀውን ከላይ ተመልከቱ።

#BBC #ሲራራ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የቲክቫህ ወጣቶች ጥያቄ፦

ስራ...ስራ...ስራ...ስራ...ስራ...ስራ!

ዩኒቨርሲቲ ጨርሻለሁ ፤ አሁን ድረስ በተማርኩት ትምህርት የስራ እድሎችን ማግኘት አልቻልኩም። አሁን ሀገራችን ላይ ስራ የሚባለውን ነገር እየሞተ ነው። በተለይ በዚህ ዓመት ደግሞ ብሶበታል።

የፖለቲካው ጉዳይ በሚመስል መልኩ የስራ ቅጥር በክልል ከተሞች ላይ አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል። የግል ድርጅቶች እራሱ ሰራተኛ ከመቅጠር ወደመቀነስ እየሄዱ እንዳለ እያየን ነው። የሀገራችን ያለመረጋጋት ሁኔታ፣ የሰላም መደፍረስ፣ የፖለቲካው አለመረጋጋት ትልቅ ተፅእኖ እያሳደረ ነው።

ፖለቲከኞች ለስራ አጥነት፣ለወጣቶች ተጠቃሚነት ሳይሆን ለራሳቸው ጥቅም ብቻ ነው እየሰሩ ያሉት። ፖለቲካው ሙሉ በሙሉ የወጣቱን ጉዳይ፣ የህይወት ማሻሻል ረስቶት በተለያየ ነገር ተጠምዷል። ጭራሽ ስለዚህ ጉዳይ አያነሱም!

ቢያንስ ፖለቲከኞች ይህን ኃላፊነታቸውን ቢወጡ ሰላም እንዲሰፍን ፣ የወጣቶችን ችግር የሚፈታ የስራ ሃሳብ ቢያቀርቡ አሁን ያለው ሁኔታ ይቃለላል። እኛ ስራ መስራት ባለመቻላችን እናዝናለን። ፖለቲከኞች ይህን ጉዳይ የማስተካከል ስራን ቢሰሩ ጥሩ ነው። ሁሉም የሚጮኸው ለራሱ ነው።

ፖለቲከኞች ለወጣቶች የስራ እድል በስፋት እንዲፈጠር የመገፋፋት፣ ወጣቶች እንዲሰሩ፣ የስራ ሃሳቦች በማቅረብ ላይ ቢረባረቡ፣ አሁን ያለውን ነገር ለመቀየር ቢሰሩ መልካም ነው። አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ተዘዋውረን ለመስራት እንኳን ይከብዳል፣ የስራ እድሎችን የተለያዩ ቦታዎች ላይ እንዳንሞክር አስቸጋሪ ነው፤ ከአንዱ ክልል ወደ ሌላው ክልል በነፃነት ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ ነው፤ ከየት ነው የመጣኸው የሚል አካልም ብዙ ነው ይህ ነገር ቢስተካከል ጥሩ ነው።

#TM

መልዕክት መቀበያ : @tikvahethiopiaBot

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ 250 ሚሊዮን ብር እንዲሰጠው ጠየቀ። ኢንስቲትዩቱ በበሽታው መከላከል እና መቆጣጠር ዙሪያ ዛሬ ረፋድ መግለጫ ሰጥቷል።

በዚህም ቫይረሱ እስካሁን በኢትዮጵያ ያልተከሰተ ሲሆን ከ324 ሺህ በላይ መንገደኞች ምርመራ ያደረገ ሲሆን ቫይረሱ ካለበት አገራት የመጡ 829 ዜጎች ላይ ባሉበት ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ኢንስቲትዩቱ ገልጿል።

ኢንስቲቲዩቱ በአገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ባዘጋጀው የለይቶ ማቆያ ክፍል ውስጥም የገባ ተጠርጣሪ አለመኖሩም ተጠቁሟል።

የኮሮና ቫይረስ እስካሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ81 ሺህ በላይ ዜጎችን ያጠቃ ሲሆን 2 ሺህ 698 ሰዎችን ደግሞ ገድሏል።

የቫትረሱ ስርጭት እየጨመረ በመሆኑ በኢትዮጵያ የመከላከል ስራውን ለማጠናከር መንግስት 250 ሚሊዮን ብር እንዲመድብ ጥያቄ ማቅረቡን ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል።

ምንጭ ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE - የሟቾች ቁጥር 2,619 ከፍ ብሏል - በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 79,565 ዛሬ ባገኘነው ሪፖርት በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2,619 የደረሰ ሲሆን 79,565 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 25,084 ደርሰዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

- የሟቾች ቁጥር 2,706 ከፍ ብሏል
- በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 80,248

ዛሬ ባገኘነው ሪፖርት በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2,706 የደረሰ ሲሆን 80,248 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 27,768 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የዓለም ጤና ድርጀት ኮሮና ቫይረስ [COVID-19 ]በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊስፋፋ ስለሚችል አገራት በሚገባ እንዲዘጋቹ አሳስቧል። ምንም እንኳ አሁን ባለው ሁኔታ ኮሮናቫይረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወረርሽኝ ሆኗል ብሎ ለማወጅ ገና ቢሆንም አገራት ግን በቂ ዝግጅት የማድረግ ሂደት ውስጥ መሆን ይገባቸዋል ብሏል ድርጅቱ።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia